የስኳድ ሰነድ – ፩

ጎንደሬን ማግለል የፖለቲካ ስልት ተደርጎ ተቆጠረ — “የሰሊጥ ፖለቲከኞች”፣ “ስኳድ” ፣ “የሻዕቢያ ተላላኪዎች”፣ “የአምቻ ፖለቲከኞች”… ወዘተረፈ የሚል ዘመቻ በስፋት ተከፈተ። መቀሌ፣ ጁባ፣ ናይሮቢ፣ አዲስ አበባና ባህር ዳር የተዋቀረው የጥፋት ኮሚቴ የጥፋት ተልዕኮ ተከፋፍሎ በጎንደሬ ላይ ኀልቆ መሳፍርት የሌለው ዘመቻ ከፈተ። በስኳድ አባላት የተጻፈ በሚል የተሰራጨውን ሰነድ የባህር ዳሩ ክንፍ አዘጋጅቶ አሰራጨው…

በ ረ/ፕ ጌትነት አልማው ጥሩነህጌትነት አልማው ጥሩነህ የተከተበ መራራ ሐቅ ነው!!!

የስኳድ ሰነድ ጸሐፊው የባህር ዳሩ ክንፍ ነው!!

የአሸባሪው ትህነግ የተዝካር ጥሩምባ የተነፋው በአባጃሌው አገር እምዬ ጎንደር ነው – ሐምሌ 05/2008 ዓ.ም

የመይሳው ካሳን ልጅ እጅ ይዘው ከመቀሌ ሲከንፉ በአባጃሌው መናገሻ ጎንደር የገቡ ጉዶች ጎንደር ላይ ወደ አመድነት ተቀየሩ። ኮረኔል ደመቀ የአባቱን ታሪክ በመድገም የትህነግን የውድቀት ታሪክ ማስጀመሪያ ሻማ ለኮሰ!! ኮረኔሉ እንደነቶኔ “ማንም እጄን አይጨብጥም” ብሎ ማይክራፎን ጨብጦ አልተንዘረዘረም፤ ምላጭ እየሳበ ላጫቸው እንጂ — የአባጃሌው ልጆች ለሥራ እንጂ ለወሬ ቦታ የላቸውም!!

አሸባሪው ትህነግና ጁኔየር ፓርትነሮቹን ዘመኑን በሙሉ የታገላቸውም የጎንደር ሕዝብ ነው። ትህነግም የከፋ በትሯን ያሳረፈችበት፣ የዘር ማጥፋት የፈጸመችበት፣ ከርስቱ በማፈናቀል መጻተኛና ያደረገችውና በኢኮኖሚ ያደቀቀችው በጥቅሉ ማኀበራዊ ካፒታሉን ሙሉ ለሙሉ በሚቻል ደረጃ በመናድ ለአገሩ እንግዳ ያደረገችው ጎንደሬን ነበር።

ሐምሌ 05 ጎንደር ላይ የትዝካር ጥሩምባዋ የተነፋላት ትህነግ በሁለተኛው ዙር ወረራ አራት አርሚ አሰልፋ አማራን አንገት አስደፍታ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ስትገሰግስ ምርጥና አለኝ የምትለውን ተዋጊና አዋጊ (elite force) አርሚ አንድ የሚል ሥም በመስጠት ያሰለፈችው በማይጠምሪ ግንባር (ጎንደር) ነበር። ማይጸምሪ ==> አዳአርቃይ==> ዛሬማ==> ዳባት==> ጎንደር ==> መተማ በማድረግ ጎንደሬን አዋርዶ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን በማስለቀቅ ከሱዳን የሚገናኝበት በር ለማስከፈት በማቀድ። የሰው ማዕበል አሰልፎ ሲከለፈለፈ በተናዳፊ ተርቦች ምድር ጭና (ጎንደር) ምድር የገባው ተዋጊ ጭና ላይ ለታሪክ ነጋሪ ሳይቀር ተላጨ – ይህ ታሪክ ሲከወን እኔ በዚያው ነበርኩ!!

ከአርሚ ሁለት ተዝካሩ የተነፋለት በቴዎድሮስ ቀኝ እጅ የገብርዬ ቀዬ አጋንንት በሚያስወጣው ጋይንት እና በማማው ደብረ ታቦር ነበር – እየዋጀጀ ነው ብለው እረመረሙት!!

ሁለተኛውን ዙር ወረራ ለመቀልበስ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲፋለም የአንድ መንደር ጉዶች ባህር ዳርን ስለመረከብ ይመክሩ ነበር፤ ትህነግ በምትመሰርተው የሽግግር መንግሥት ተወካይ ለመሆን ድርጅት ምሥረታ ላይ ነበሩ። በኢትዮጵያዊያን ሕብረት በጠነከረው የጎንደሬ መዋደቅ (ጎንደር አትደፈርም እያሉ በባዶ እጃቸው ከወራሪው ጋር እየተናነቁ ያለቁ የዳባት፣ የደባርቅ፣ የጃኖራ፣… ወጣቶች ምስል እንሆ በእዝነ-ልቦናዬ ይመላለሳሉ) ኅልማቸው ከንቱ ሆነ።

እንሆ ከአሳዳጊያቸው ትህነግ የወረሱት ጎንደሬ ጠልነት በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መስዋዕትነት በጎንደሬ የላቀ ጀግንነት የሽግግር መንግስት አካል ሆነው የመዝረፍ ምኞታቸው ከንቱ ሆኗልና ጎንደሬን መጥላት ጎንደሬን ማግለል የፖለቲካ ስልት ተደርጎ ተቆጠረ — “የሰሊጥ ፖለቲከኞች”፣ “ስኳድ” ፣ “የሻዕቢያ ተላላኪዎች”፣ “የአምቻ ፖለቲከኞች”… ወዘተረፈ የሚል ዘመቻ በስፋት ተከፈተ። መቀሌ፣ ጁባ፣ ናይሮቢ፣ አዲስ አበባና ባህር ዳር የተዋቀረው የጥፋት ኮሚቴ የጥፋት ተልዕኮ ተከፋፍሎ በጎንደሬ ላይ ኀልቆ መሳፍርት የሌለው ዘመቻ ከፈተ። በስኳድ አባላት የተጻፈ በሚል የተሰራጨውን ሰነድ የባህር ዳሩ ክንፍ አዘጋጅቶ አሰራጨው…

፪…፫…፬…፭…ይቀጥላል!…

የአገር ካስማ የሆነው ጎንደር ሲነካ ያመኛል!…

You may also like...

Leave a Reply