በካይሮ የተዘረጋው ሰሞነኛ ሴራ ይፋ መሆኑ ጩኸት አስነሳ

Esleman Abay

“የህወሃትን የመሳሪያ ድጋፍ ያወገዘው የአማራ አክቲቪስት” ሲል ነው የካይሮ ኔትወርክ ልሳን የሆነው የሱዳን ወታደራዊ የመረጃ ድር ኢሳሌማን ( የአባይ ልጅ) ላጋለጠው ጽሁፍ አይን ያወጣ ምላሽ የሰጠው። ይህ ታታሪ ኢትዮጵያዊ በርካታ ጉዳዮችን ከሱዳንና ግብጽ እየጨለፈ ስለሚያጋልጥ ” አማራ” ሲል ፍርጆታል። የትህነግ አማራ ጠል ቅሰቀሳ በሚቀልባቸውና በሚታዘዛቸው አገራት ድረስ ዘልቆ እንደሄደ ይህ ጥሩ ማሳያ ነው። ኢሳሌማን የጻፈውን ከታች ያንብቡ


በሱዳን መከላከያ ውስጥ ለአልቡርሃን ክንፍ ልሳን የሆነው ዌብሳይት ለህወሃት የሚደረገውን ድጋፍ የተመለከተ መረጃ ሲያሰራጭ የመጀመሪያው አይደለም። የአልቡርሃን ቡድን በአልፋሻጋ ይህን አደረገ፤ አቀደ፤ መሬት ተወሰደበት፤ መልሶ ወሰደ ወዘተ…እያለ ሲፅፍ ይታወቃል። የህወሃት ቡድን ተተኳሽ አገኘ፤ ፈረጠመ በማለት ፎቶዎችን መለጠፍ አጀንዳው ሲሆን Sudan military capabilities የተባለ ድረ ገፅ ማእከላዊው ቋቱ ነው። የዌብሳይቱ የፌስቡክ ገፅ ከመቶ ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ከሱዳን ወታደራዊ አቋም ውጪ መግለጫ ሲሰጥ እንደነበር ( https://www.facebook.com/100003626461788/posts/2643621692435354/ )


እንዲሁም ባለፈው ሐምሌ፣ ኢትዮጵያን የተመለከተ ወታደራዊ ዘገባዎቹ የሱዳን ባለስልጣናትን አቅጣጫ ማክበር አለበት በሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው ይታወሳል።

ይኸው ገፅ በትላንትናው እለት ለፅሁፌ ምላሽ ሰጥቶ ነበር። በካይሮ የተደራጀ ፀረ ኢትዮጵያ እቅድ ከሱዳን እስከ ሩዋንዳ ስለመዘርጋቱ የገለፅኩበትን መረጃ ስክሪንሻት አድርጎ አጋርቷል፤ የፅሁፉ መደምደሚያ ያደረገውም ያንቱ ለህወሃት የሚደረገውን የውጭ አካላት የመሳሪያ አቅርቦት ተገቢ ነው የሚል ነበር።


በካይሮ የተዘረጋው ሰሞነኛ ትህነጋዊ ሴራ

የአሁኑ የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት የቀድሞ በ CIA እና MI6 የሰለጠነው ፖል ካጋሜ አቀነባብሮ በመራው መፈንቅለ መንግስት የዩጋንዳው ሚልተን ኦቦቴ ለስብሰባ ወደ ሲንጋፖር በተጓዙበት ከስልጣን ወርደዉ ዩዌሪ ሙሴቬኒ ወደ ስልጣን ሊወጡ ችለዋል፡፡ ሙሶቬኒ 1986 ላይ ስልጣን ከጨበጡ በኋላ የካጋሜን ውለታ ለመመለስ የሩዋንዳ አማፂ ግንባር የተባለ ጦር እንዲያቋቁም በማድረግና ትጥቅና ስንቅ በማቅረብ ያኔ ሥልጣን ላይ የነበረውን በሁቱዎች የተዋቀረውን መንግሥት 1994 ላይ ተክቶ ወደ ሥልጣን እንዲወጣ አድርጎታል። ህወሃት ሃውዜን ላይ እንደፈፀመው…


የካይሮ እና አልቡርሃንን ኔትወርክ የተመለከተ አጀንዳ የሚያስነብበው ፌስቡክ ገፅ ስለጉዳዩ ምላሽ የሰጠበት ፅሁፉ “ከኢትዮጵያ አክቲቪስቶች አንዱ አማራ ነው” ሲል ይጀምራል፤(የፈረደበት አማራ..)። ፅሁፉ “በአሁኑ ወቅት ግብፅ የምታስተባብረው ኢትዮጵያ ላይ የሚፈፀም ነው ያለውን ዓለም አቀፋዊ ሴራ ይዞ ወጥቷል።” ያለ ሲሆን “በሱዳን ድንበር የህወሃት ታጣቂዎችን በስደተኞች ካምፖች አሰጠልጥነው የጦር መሳሪያ አስታጥቀው ወደ ኢትዮጵያ ያዘምታሉ ብሎናል። በሱዳን ድንበር ምእራብ ትግራይ በኢትዮጵያ ኃይሎች ተዘግቷል። የአማራ ኃይሎችና የኤርትራ ጦር ቦታውን ከዘጉት አመት አልፎታል።” ይላል።
በመቀጠል የሰጠው መደምደሚያ ላይም ተከታዩን አስፍሯል፣
“42 ቀናህ በላይ ባስቆጠረው ሶስተኛው ዘመቻውን አብይ አህመድ በጦር አይሮፕላን በድሮኖች፣ በ SU 27፣ በ MIG-23፣ ድብደባ እያካሄደ ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ጦር አሰማርቶ በትግራይ ከበባ እያደረገ ይገኛል። በዚህ ወቅት ህወሃት ከውጭ አካላት ድጋፍ ማግኘቱ ተገቢ ነው።”
ብሎናል።
እናም… እነማን ምን እያሴሩ ነው? የመግቢያ ክፍተቶችስ?
ካይሮ ስለ ኢትዮጵያ መቼም አትተኛም

See also  የሞተች ልጇን ይቅር እንድትል የተጠየቀችው እናት አሻፈረኝ አለች!

የዓባይልጅ

በአረብኛ ያሰፈረው ፅሁፍ ኮመንት መስጫ ስር ⬇️

Leave a Reply