አዜብ ኢንተቤ ከትመዋል – ንክኪ ያላቸው “ባለሃብቶች” ቀለበት ውስጥ ገብተዋል

በኢኮኖሚው መስክ የመንግስት የአዲሱ ዓመት ዋና ተግባር “ሌቦች” የሚባሉት ላይ መዝመት፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ማምከንና ወደ አገር ውስጥ የሚገቡትን ምርቶ በአገር ውስጥ ማምረት ላይ መረባረብ፣ እንዲሁም የእርሻ እንዲስቱሪውን በማበልጸግ አምራጭ ተቋማትን ማበርከት እንደሆነ ተደጋግሞ ሲነገር መሰንበቱ ይታወሳል።

በተለይም ከፋይናንስ አሻጥሩ ጋር በተያያዘ የቋሚ ንብረት የውክልና ገበያውን እንጥሉን የሚቆርጥ ውሳኔ ቀደም ብሎ የውሰነው። ባለቤት ሳይኖር በውክልና ሃብት ማዘዋወርና መሸጥን የገደበው መመሪያ በውልና ማስረጃ በኩል መሰማቱ የገንዘብ ማሸሹን እንቅስቃሴ የሚገታ እንደሆነ የገባቸው ወዲያው ሲገልጹና ውሳኔውን ሲያደንቁ ተሰምቷል። የዚያኑ ያህል ደግሞ ውሳኔው ያበሳጫቸው ተንጫጭተዋል።

ከመቼውም ጊዜ በላይ በእውቀት ላይ ተመስርቶ እንደተገነባ የሚነገርለት የፋይናንስ ደህንነቱ የገንዘብ ዝውውርን ስር ተከትሎ ባደረገው ማጥራት ከስድስት መቶ በላይ በወንጀል የሚጠረጠሩ የሂሳብ ቋቶችን ዘግቷል። ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎችን ህግ ፊት አቁሟል። የአገሪቱ ባንክም በዚህ ተግባር የሚሳተፉትን ለሚጠቁሙ ማነቃቂያ ሽልማት እንደሚከፍል ይፋ አድርጎ ህዝብ ዘመቻውን እንዲቀላቀል እያደረገ መሆኑንን አሰምቷል።

ይህ በሆነበት ማግስት ነው የመንግስት መገናኛ ከሆኑት መካከል አንዱ ዋልታ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ሚስት ወይዘሮ አዜብን መስፍንን ጠቅሶ አዲስ መረጃ ያሰራጨው።

በዚሁ መግናኛ ተከታታይ ክፍል ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ በባላቸው ጡረታ ብቻ እንደሚተዳደሩና ምናምንቴ ነገር እንደሌላቸው ያስታወቁት፣ በሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ ቀርበው ይህንኑ ሃሳባቸውን ሲያጠናክሩ የነበሩት ወ/ሮ አዜብ ኡጋንዳ ኢንተቤ መከተማቸው ነው በይፋ የተመለከተው።

ቀደም ባሉት ጊዚያት ወ/ሮ አዜን አሁን ለጊዜው ስማቸው ከማይጠቀስና በቅጽበት ከፍተኛ ሃብት ከሰበሰቡ “ታዋቂ” ባለሃብቶች ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንዳላቸው የተለያዩ ወገኖች ሲያስታውቁ ነበር። የራሳቸው የትህነግ ሰዎችም ቢሆኑ ወ/ሮ አዜብ ባላቸውን ተገን አድርገው ሲመሩት በነበረው ኤፈርት ስም ከፍተኛ ሃብት በውጭ አገር እንዳከማቹ በገሃድ ሲናገሩ ነበር።

የዋልታ መረጃ

አሁን ዋልታ ይፋ እንዳደረገው ሰማህል የምትባለው የወ/ሮ አዜብ ልጅ ሰሞኑንን የኢትዮጵያን መከላከያ ለመዋጋት በረሃ መግባቷን፣ ይህም ለመላው የትግራይ ወጣቶች አርዓያ እንደሆነ ተደርጎ መቅረቡ ሃሰት ነው። ሚዲያው እንዳለው ልጅቷ ሽርጥ ለበሳ ወደ በረሃ መግባቷ ይፋ በሆነ ማግስት ኢንተቤ አየር ማረፊያ ከእናቷ ጋር መታየቷን አስታውቋል።

መረጃው የሰማህልን “በረሃ ናት” ተብላ ኢንተቤ መገኘቷን ሲያውጅ ጎንለጎን ወይዘሮ አዜብን ” የትህነግ ወዳጅ በሆነቸው ኡጋንዳ ከሱዳን ቀጥሎ የሚደራጀውን ወታደር ያደራጃሉ” ሲል ታላቅ ሚስጢር ይፋ አድርጓል።

ትህነግ ለዳግም ወረራ የሰው ማዕበል ለማስነሳት ለሚመለምለውና የሚያፍሰው ሃይል ማነቃቂያ ሲባል “በረሃ ገባች” የተባለችውን ሰማህል መለስ በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት በቪ8 ዘመናዊ ተሽከርካሪ ጦርነቱ ከሚካሄድበት ስፍራ ከአቶ ስብሃት ነጋ ልጅ ጋር መገኘቷን፣ በወቅቱ መሳሪያ፣ የቅሰቀሳ ቁሳቁስ፣ ውድ ዋጋ ያላቸው የመጠጥ አይነቶች፣ ገንዘባና አነቃቂ የሚጨሱ … ሲገኙ ድርጊቱ የአገር ክህደት ቢሆንም መንግስት ሆን ብሎ በቸልታ ማለፉን አቅራቢው አመልክቷል። ያንን በትዕግስት ያለፈውን የአገር መከላከያ ለመውጋት “ሰማህል ጫካ ወረደች” መባሉን አክሎ ” በሚዲያ የማይገልጽ የወረደ ተግባር የምትፈጽመው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ ከሃሺሽ አቅርቦት ውጪ ሌላውን ፍላጎቷን በርሃ እንደማታገኝ እየታወቀ ለዚህ ቅሰሳ መታለል ስላቅ ነው” ሲል ጠቅለል አድርጎ አመልክቷል።

“አንጡር ሃብት የለኝም፣ ጡርተኛ ነኝ” ከሚሉት እናቷ አዜብ ጋር ኡጋንዳ የተንደላቀቀ ህይወት እየመራች ያለችው ሰማህል
በረሃ ነው ያለሁት” ስትል ከዚህ መረጃ መለቀቅ በሁዋላ ስታስተባብል አልተሰማችም።

እናቷ በዩጋንዳ በሃይል አቅርቦት ኢንዘስትመንት እየተሳተፉ እንደሆነ ያመለከተው የዋልታ መረጃ ከሳቸው ጋር ንክኪ ያላቸው ባለሃብቶች ሊመረመሩ እንደሚገባም አመላክቷል። ይሁን እንጂ ፍንጭ ከመስጠቱ ውጭ ንክኪ አላቸው ስላላቸው ባለሃብቶች ዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ደጋሞ “የትህነግ ወዳጅ” እያለ የጠራት ኡጋንዳን የሚመሩት የሙሲቬኒ ልጅና የአገሪቱ ጦር ከፍተኛ የጦር መኮንን ጄኔራል ሙሆዚ ካይኒሩጋባ በተደጋጋሚ በቲውተር ገጻቸው ለትህነግ ፍቅራቸውን ሲገልጹና የትግራይ ነጻ አውጪ መሆናቸውን በተደጋጋሚ የሚያስታውቁት ምን አልባትም ዋላታ እንዳለው አዜን መስፍን ዕዛ ያለውን የትህነግ ሃይል ያደራጃሉ ከመባሉ ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው በይፋ የተባለ ነገር የለም። በግል ግን ግንኙነት እንዳላቸው የኡጋንዳ ምንጮች መናገራቸው፣ አብረው እንደሚታዩም አስቀድሞ መገለጹ ይታወሳል።

ዋልታ ብልጭ ያደረጋትና ከሁሉም በላይ መነጋገሪያ የሆነችው ወ/ሮ አዜብን በውጭ ምንዛሬ አጠባ አንስቶ ከፍተኛ ሃብት ማሸሻቸውን፣ ከሳቸው ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለሃብቶች ላይም ምርመራ ሊደረግ እንደሚገባው መጠቆሙ ነው። ይህ የዋልታ ጥሪ ከቱርክና ከአረብ ኢምሬትስ ጋር ወንጀለኞችን እስከመቀያየር የደረሰ ስምምነት ከመፈጸሙ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ወደ ተጠቀሱት አገራት ማቅናታቸውና በነዚሁ አገራት ከፍተኛ ሃብት መከማቸቱ ከመነገሩ ጋር ነገሩ የተገጣጠመ ይመስላል።

የትህነግ አመራሮችና የንግድ አጋሮችን ንብረት በተጋነነ የሽያጭ ዋጋ በባንክ ብድር አየር በአየር የገዙ “ቅምጥ” የሚባሉ ባለሃብቶችን ሕዝብ በስም የሚያውቃቸው እንደሆነ በተለይዩ ወቅቶች መገለጹ አይዘነጋም።

አዘብ መስፍን በዲሲፒሊን በሚል ከትህነግ አመራርነታቸውና አባልነታቸው መባረራቸው ይታወሳል። እሳቸውም ይህንኑ በይፋ መናገራቸው አይዘነጋም።

You may also like...

Leave a Reply