ኢትዮጵያ የ24 ስዓት መረጃ – 2

🇪🇹 መረጃ 1 ከኢፕድ የተገኘ

መንግስት በ2015 በጀት አመት‼️

👉 ግጭቶችን በውይይትና በንግግር ለመፍታት ጥረቱን ይቀጥላል፤

👉 የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋትና ጤናማ የማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ይሰራል፤

👉 ከወዳጅ ሀገራት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ቅንጅት ያጠናክራል፤

በ2015 በጀት አመት ግጭቶችን በውይይትና በንግግር ፈተን የምክክር ኮሚሽኑን ስራ ወደ ፊት በማራመድ ልማታችን በተጀመረው መንገድ እንዲቀጥል ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ሲሉ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

የዋጋ ንረቱን ማረጋጋትና ጤናማ የማክሮ ኢኮኖሚ መፍጠር እንዲሁም ከወዳጅ ሃገራት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከርም የበጀት አመቱ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

🇪🇹 መረጃ 2 ከኢፕድ የተገኘ

መንግስት የአገሪቱን ጥቅም ባስከበረ እንዲሁም ዘለቄታን ባማከለ መልኩ ድርድር እንዲደረግ የተቻለውን ጥረት በማድረግ ይገፋበታል። ነገር ግን ይህንን የሰላም አማራጭ በመርገጥ ለሚደረግ ማንኛውም ትንኮሳ አስፈላጊው የማስተገሻ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ሊሰመርበት እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ገለፁ።
https://fb.watch/g598SSYZ_h/

🇪🇹 መረጃ 3 ከኢፕድ የተገኘ

መንግሥት የሳይበር ደህንነትን ቁልፍ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ አድርጎ እየሠራ ነው

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን፤ በዘርፉ በዩኒቨርሲቲዎች እና በታዳጊ ወጣቶች እየታየ ያለውን ተነሳሽነት አድንቀው መንግሥት የሳይበር ደህንነት ቁልፍ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ አድርጎ እየሠራ ነው ብለዋል።

ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ በዓለም ለ19 ጊዜ እየተከበረ ነው።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=412777267712401&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 4 ከኢፕድ የተገኘ

የትግራይ ተወላጆች የሕዝቡ ሰቆቃ እንዳይቀጥል ከአሸባሪው ሕወሓት በተጻራሪ መቆም አለባቸው

ከትግራይ ክልል ውጭ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ የትግራይ ተወላጆች እየባሰ የመጣውን የትግራይን ሕዝብ ሰቆቃ ላለማስቀጠል ከአሸባሪው ሕወሓት በተጻራሪ መቆም የሚጠበቅባቸው መሆኑን የቀድሞው የትግራይ ክልል የዋጅራት ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገለጹ፡፡
https://www.press.et/?p=83251

🇪🇹 መረጃ 5 ከኢዜአ የተገኘ

የግብር ክፍያ በቴሌ ብር መጀመሩ የብልሹ አሰራር መንስኤዎችን ለመቀነስ አግዟል

የግብር ክፍያ በቴሌ ብር መጀመሩ ፈጣን መስተንግዶ መስጠት ከማስቻሉ ባለፈ የብልሹ አሰራር መንስኤዎችን ለመቀነስ ማገዙን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

See also  ለአማራ ክልል በህቡዕ 450 አመራሮች መመልመላቸው፣ 47 የሽብር ጥቃት ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ ግለሰቦች ከሙሉ ትጥቃቸው ጋር ተያዙ

በቴሌ ብር የግብር ክፍያ ሥርዓት በአዲስ አበባ ከ300 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን መክፈላቸው ታውቋል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በዘንድሮው በጀት ዓመት ከሐምሌ እስከ ጳጉሜ ባሉት ሁለት ወራት 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ግብር ለመሰብሰብ አቅዶ 14 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከዕቅዱ በላይ ማሳካቱ ይታወቃል።

🇪🇹 መረጃ 6 ከኢፕድ የተገኘ

በሁለትዮሽ ውይይት ላይ ለመሳተፍ በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ ዋሽንግተን ዲሲ ገባ

በዓለም ባንክ እና አይ.ኤም.ኤፍ ዓመታዊ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገኖች ውይይት ላይ ለመሳተፍ በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ዋሽንግተን ዲሲ ገብቷል።

🇪🇹 መረጃ 7 ከኢፕድ የተገኘ

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስጣጥን እየጎበኙ መሆኑን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ዘግቧል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=412731397716988&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 8 ከኢፕድ የተገኘ

ከሁለት ወር ዕረፍት በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል

ከሁለት ወር እረፍት ጊዜያት በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም የበጀት ዓመቱን ስራ በይፋ መጀመሩን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ አስታወቁ፡፡

🇪🇹 መረጃ 9 ከኢፕድ የተገኘ

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶች ከኢትዮጵያ አልፈው በአፍሪካም ገበያ ውጤታማ መሆን ይችላሉ

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳሬክተር ጄኔራል ገርድ ሙለር በጽፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚታየውን የማምረት አቅም አጠቃቀም ውስንነት ለማሻሻልና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የውጪ ባለሀብቶች መዋለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ አዋጭ በሚያደርጓቸው ምቹ ሁኔታዎችና አማራጮች ላይ መክረዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=412905177699610&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 10 ከኢፕድ የተገኘ

ኢትዮጵያ በፖን አፍሪካኒዝም ያፈራችውን ልምድ በአረንጓዴ ልማት አሻራ ማስተሳሰር እንደምትችል ተገለጸ

ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመጓዝ አፍሪካዊ ወንድማማችነትን የመትከል አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ያካሂዳሉ።

አፍሪካዊ ወንድማማችነትን የመትከል መርሃግብር ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

See also  መንግስት ከሲሚንቶ ንግድ ወጣ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio

Leave a Reply