ተከዜን ወደ ሳዑዲ ማሻገር ?

የዓባይ፡ልጅ

ይህ የሳዑዲ ምኞት ሳይሳካ ይቆይና በተለይም ኢትዮጵያ በተከዜ ወንዝ ላይ የገነባችውን ግድብ ተከትሎ ህልም ሆኖ ነበር የቆዬው። ታዲያ ሳዑዲ ይህን ወይም ይህን መሰል ፕሮጀክት ለመገንባት ምቹ አጋጣሚ እየተጠባበቁ ቢሆን እኝጂ ከመጋረጃው ጀርባ ማቀድና ማለማቸው የማይቀር ነው የሚለው የበርካቶች እሳቤ ነበር። ምክንያቱም ሳኡዲ አረቢያ ከየትኛውም ሀገር በላይ ውሃ ያስፈልጋታልና።

▪️طريق بورتسودان جدة قريبا ▪️

ለሳዑዲ አረቢያ አስፈሪ ስጋቷ ውሃ ጥም ነው፤ ከነዳጅም ሆነ ከወርቅ በላይ ውሃ ትፈልጋለች። ሪያድ ለገጠማት የውሃ ችግር እግሯ የሚወስዳት ወደ ወንዙ ሳይሆን የውኃ ደላሎች፣ ወደ ባንዳዎች እና ወደ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች መሆኑ ያስገርማል። በቀደሙት ዘመናት ከዓባይ ውሃ የመጠቀም ሙከራዎቿ ከኢትዮጵያ ጋር ከመተባበር ይልቅ ካይሮ ካርቱም ጋር መዶለት ነበር ምርጫዋ የነበረው።

ሪያድ የተከዜ ወንዝ ውኃን በሱዳን በኩል ወደ ሳዑዲ ምድር ለማድረስ ያደረገችው ሙከራ ከብዙ አንዱ ምሳሌ ነው። ይህ የሳኡዲ አረቢያ እቅድ የተሞከረው ከሶስት አስርት አመታት በፊት ሲሆን ፕሮጀክቱ በምኞት ብቻ ነበር የቀረው። ከሰሞኑ የሚወጡ መረጃዎች ደግሞ ያንኑ ፕሮጀክት የመተግበር እንቅስቃሴ ላይ መሆኗን ያመላክታል። ይኸውም ከፖርት ሱዳን ወደ ጂዳ የሚዘረጋ ባህር-አቋራጭ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት የሚል ስም የተሰጠው ነው። ፕሮጀክቱ የመንገድ ትራንስፖርት ነው በማለት ዋነኛውን አላማ ለመሸፈን ሙከራ አድርገዋል። በቅርብ ጊዜ ውስጥም ፕሮጀክቱ እውን ይሆናል እያሉ ናቸው። ሳኡዲ የኢትዮጵያን ውኃ በሱዳን በኩል ጠልፋ የመውሰድ ነባር ምኞቷን በታሪክ ወደኃላ ተመልሰን ብንመለከት ተከታዩን እናገኛለን።

ሳዑዲ አረቢያ ከናይል ዋነኛ ገባሮች መካከል የሆነውን የተከዜ-አትባራ ወንዝን በመጥለፍ በቀይ ባህር በኩል ወደ ሪያድ ለማሻገር አቅዳ የነበረው በሳዑዲ መሪዎች ምኞት እና በካይሮ ማን አለብኝነት ሲሆን፤ ጊዜው ደግሞ የ 1980ዎቹ መጨረሻ ነበር..። በሀገራችን ምሁር 1999 እ.ኤ.አ ላይ የወጣ መረጃም ይህንኑ የሚያስረግጥ ነበር።

▮…በሰዓት 4.5 ሚሊዮን ሊትር የሚሆን ውሃ ከአትባራ (ተከዜ) በመጥለፍ ወደ ቀይ ባህሯ የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ከዚያም ወደ ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ በቀይ ባህር በኩል ለማሻገር በግብጽ ሙሉ ድጋፍ የ2 ቢሊዮን ዶላር ስራ በአርቃቂዎች ተጀምሮ ነበር፡፡ እንደ እቅዱ ከሆነ ሱዳን በሁለት መልኩ የምትጠቀም ሲሆን አንድም ከአትባራ (ተከዜ) በስተምስራቅ የሚገኘውን ጠፍ መሬት ለማልማት የሚያስችላት ሲሆን እንዲሁም በቀይ ባህር ዳርቻ ያሉ ፏፏቴዎችን በመጠቀም በሰዓት ከ7000 ኪሎዋት በላይ ኤሌክትሪክ ለማምረት ያስችላታል፡፡ ሳዑዲዎቹም ግብፅን እና ሱዳንን (በዚህ ፕሮጀክት ምክንያት) ለሚያጡት የመስኖ ውሃ በግብርና ካፒታል ኢንቨስትመንት እና በኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ያካክሱታል..▮
~ዳንኤል ክንዴ፣ 1999 እ.ኤ.አ~

See also  Passwords for social media accounts could be required for some to enter country


ይህ የሳዑዲ ምኞት ሳይሳካ ይቆይና በተለይም ኢትዮጵያ በተከዜ ወንዝ ላይ የገነባችውን ግድብ ተከትሎ ህልም ሆኖ ነበር የቆዬው። ታዲያ ሳዑዲ ይህን ወይም ይህን መሰል ፕሮጀክት ለመገንባት ምቹ አጋጣሚ እየተጠባበቁ ቢሆን እኝጂ ከመጋረጃው ጀርባ ማቀድና ማለማቸው የማይቀር ነው የሚለው የበርካቶች እሳቤ ነበር። ምክንያቱም ሳኡዲ አረቢያ ከየትኛውም ሀገር በላይ ውሃ ያስፈልጋታልና።
ሪያድ በገጠማት የከፋ የውሃ ቀውስ ሳቢያ በተለያዩ አገራት ከገዛችው ውሃ-ገብ የእርሻ መሬት በተጨማሪ የባህር ውሃን ለማጣራት በከፍተኛ በጀት ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ማስገባት ከጀመረች አመታት ተቆጥረዋል። ጨዋማ የባህር ውሃን አጣርታ ለመጠቀምም በዬአመቱ 3 ቢሊዮን ዶላር እያወጣች ነው የምትገኘው። በአለማችን ከሚደረገው የባህር ውሃ የማጣራት ስራ ግማሹን መጠን የሚሸፍነው የሳዑዲ ዲሳሊኔሽን ነው። ይሁንና ይህ አቅርቦት ለሳኡዲ አረቢያ ግዙፍ ገንዘብ የሚጠይቃት እንጂ የሚያስገኝላት የውሃ መጠን ከሀገራዊ ፍላጎቷ አንፃር ትንሹ ነው።

በአንድ ወቅት 500 ቢሊዮን ሜኪዩብ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችት የነበራት ሳዑዲ አረቢያ 98 በመቶ የውሃ አቅርቦቷን ከዚሁ የውሃ ሐብቷ ነበር የምታገኘው። የዜጎቿ ዕለታዊ የውሃ ፍጆታ ከአውሮፓ ስታንዳርድ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን፤ በዛ ላይ ደግሞ በ 1980ዎቹ ጀምሮ አገሪቱን የሩዝና የእርሻ ደሴት ለማድረግ የተጀመሩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች የከርሰ ምድር ውሃዋን አሟጠጠውና ነገሮችን ከባድ እንዳደረገባት ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም 2015 ላይ 80 በመቶው የሳዑዲ የከርሰ ምድር ውሃ ማለቁን ጥናቶች አረጋገጡ። ናሽናል ጂኦግራፊ ይህንኑ ጥናታዊ ሪፖርት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፤ የሳዑዲ አረቢያው King Faisal ዩኒቨርሲቲ 2016 ላይ ያወጣው ሪፖርትም የሀገሪቱ የከርሰ ምድር ውሃ በ 13 አመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያልቅ ደምዳሜውን ይፋ አድርጎ ነበር። ሳይንቲስቶች ከሚገምቱት ስሌት በከፋ ፍጥነት እየተከሰተ ካለው አለማቀፍ የውሃ አካላት የመድረቅ አሳሳቢ ክስተት አንፃር ሲገናዘብ ሳዑዲ ከአምስት ባልበለጡ አመታት ውስጥ “Zero-Water” የምትሆንበት አደጋ እንደተደቀነባት የሚጠቁም ይሆናል።

ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በቀጣይ 10 አመታት የፖለቲካ እና ማህበራዊ ቀውስ መንስኤ ጦርነት ወይም ሽብርተኝነት ሳይሆን ውሃ ጥም መሆኑ የተገለፀው ቀደም ካሉ አመታት ጀምሮ ነበር። ለአብነትም ከአስር አመታት በፊት Jon B. Alterman ይፋ ያደረጉት ጥናት “Clear Gold” በሚለው አርዕስቱ “የመካከለኛው ምስራቅ ቀጣዩ ስትራቴጂክ ከባድ ካርድ ውኃ ነው” በማለት ከነዳጅም በላይ የሚወደድ፣ የሚያሳስብና የሚያናክስ ጉዳይ ይሆናል ሲሉ ነው ያሰመሩበት።
እናም..! በአረቡ ዓለም የማህበራዊ መገናኛዎች በኩል ሰሞኑን በስፋት ሲሰራጭ የታዘብነው “ፖርት ሱዳንን ከሳዒዲዋ ጂዳ የሚያገናኘው የመንገድ ፕሮጀክት በቅርብ እውን ይሆናል” የሚለው ዘመቻ ዋነኛ አላማው ውኃ መሆኑ ለማንም የተደበቀ አይሆንም። የመንገዱ ግንባታ ለባቡር፣ ለተሽከርካሪ፣ ነዳጅን ጨምሮ ለፈሳሽ ማስተላለፊያ አንድ ላይ ለመስራት የሚያስችል ነው የሚሆነው። ለሳዑዲ አንገብጋቢው ጉዳይ ውሃ እና ውኃ መሆኑን እዚጋ ልብ ይሏል..። ምን አስበው ይሆን?
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች
Esleman Abay✍️ #የዓባይልጅ

See also  የካይሮ የ 'ኢንዱስትሪ -ድርቅ' ትርክት

Leave a Reply