ሰባት የአዋሽ ባንክ ሰራተኞች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተ

በህይወት የሌሉና በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በባንክ ያላቸውን ሂሳብ ደንበኞቹ እንዳሉና አስመስለው ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የተባሉ ሰባት የአዋሽ ባንክ ሰራተኞች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተ፡፡

የተሰጣቸዉ ሥልጣንና ኃላፊነት አላግባብ በመገልገል በህይወት የሌሉ ደንበኞችን ጨምሮ የሂሳብ ባለቤቶቹ ሳይቀርቡ እንደቀረቡ በማስመሰል ሂሳቡን ተንቀሳቃሽ በማድረግ አጠቃላይ ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ወስደዋል በሚል ዐቃቤ ህግ 4 ተደራራቢ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ (9)(2) ላይ የተደነገገውን መተላለፍ በፈፀሙት በሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል በ4 ተደራራቢ ክሶች ተከሰዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ህግ ክስ ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ያደረገ ሲሆን ክሱን ለማንበብ ለጥቅምት 8/2015 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ፍትህ ሚኒስቴር ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio

See also  የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ሰራተኞች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተ

Leave a Reply