ኢትዮጵያ የ24 ስዓት መረጃ – 3

🇪🇹 መረጃ 1 ከኢፕድ የተገኘ

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የእንግሊዝ የዌሴክስ ልዕልትን ተቀብለው በሰብዓዊ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋገሩ

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ እየተዘዋወሩ ያሉትን የእንግሊዝ የዌሴክስ ልዕልት ሶፊ ራይስ-ጆንስን ተቀብለው በተለያዩ ሰብዓዊ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=415942264062568&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 2 ከኢፕድ የተገኘ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ለመታደም ጎንደር ከተማ ተገኝተዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=416219317368196&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 3 ከኢፕድ የተገኘ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ከፎረሙ ጎን ለጎን በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ኢትዮጵያና ሱዳን ረጅም የወዳጅነት ታሪክ ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ተገልጸዋል።

ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን በ10ኛው ጣና ፎረም ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=415947474062047&id=100069403920568
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=415899130733548&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 4 ከኢፕድ የተገኘ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዓባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን ድልድይ የግንባታ ሁኔታ ጎበኙ

በጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ ባህርዳር የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በዓባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን ድልድይ የግንባታ ሁኔታ ጎብኝተዋል።

አዲሱ የዓባይ ድልድይ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት በዓለም አቀፉ የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ እየተገነባ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=415976557392472&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 5 ከኢፕድ የተገኘ

በሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክረው አስረኛው የጣና ፎረም በባህር ዳር ከተማ በይፋ ተከፍቷል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የምክክር መድረኩ ለአፍሪካ ችግር ሀገር በቀል አፍሪካዊ መፍትሄዎች የሚፈለጉበት መሆኑን ተናግረዋል።

አፍሪካ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ያላት አስተዋፅኦ አነስተኛ ቢሆንም በከፍተኛ ሁኔታ ግን ተጎጂ ናት ብለዋል። ውኃ ፣ ሃይልና የዳታ አስተዳደር መንግስት ትኩረት የሰጣቸው መስኮች መሆናቸውን ተናገረዋል።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=416087137381414&id=100069403920568

See also  "የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች ምንም የድርድር ፍላጎት አላሳዩም" - ተመድ

🇪🇹 መረጃ 6 ከኢፕድ የተገኘ

የግዥ እቅድ ያላቀረቡ 60 የፌዴራል ተቋማት ጉዳይ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው

ወቅቱን ጠብቀው የግዥ እቅድ ያላቀረቡ 60 የፌዴራል ተቋማት ጉዳያቸውን ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለፓርላማ ሊያቀርብ መሆኑን የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አስታወቀ። የተቋማቱ ሥም ዝርዝርም በሚዲያ በኩል ይፋ ሊደረግ እንደሚችልም ተጠቁሟል። https://www.press.et/?p=83520

🇪🇹 መረጃ 7 ከኢፕድ የተገኘ

በዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የ12ኛ ክፍል ፈተና አስፈጻሚዎች በአከባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማስፈጸም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመድቡ የፈተና አስፈጻሚዎች በአከባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የ12ኛ ክፍል ፈተና አስፈጻሚዎች የኦሞ ሰው ሰራሽ ሀይቅን ጎበኙ።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=416146837375444&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 8 ከኢፕድ የተገኘ

ቢክ ኢትዮጵያ የ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

የቢክ ኢትዮጵያ በግብርና ቴክኖሎጂና በግብርና ንግድ ዘርፎች የተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማገዝ የአምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።

ፕሮጀክቱ ለተያዘው የሥራ ፈጠራ እቅድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።
https://www.press.et/?p=83539

🇪🇹 መረጃ 9 ከኢዜአ የተገኘ

ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሕግ አውጭዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቀ
በኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሕግ አውጭዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ጠየቁ።

የሀገር አቀፍ፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሕግ አውጭዎች የምክክር መድረክ በጅማ ከተማ ተካሄደ፡፡

🇪🇹 መረጃ 10 ከኢፕድ የተገኘ

ጉዳት የደረሰባቸው ውሃማ አካላት እንዲያገግሙ የሚያስችሉ አበረታች ሥራዎች ተሠርተዋል

በ2014 በጀት ዓመት ጉዳት የደረሰባቸው ውሃማ አካላት እንዲያገግሙ ለማስቻል የተሠሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በተለይም ቀደም ሲል በእንቦጭና በኬሚካል ጉዳት የደረሰባቸው ሐይቆች ላይ የደረሱ ጉዳቶችን ለመቀልበስ ማኅበረሰቡን ያሳተፈ ሥራ ሲከናወን ቆይቷል፡፡
https://www.press.et/?p=83542

🇪🇹 መረጃ 11 ከኢፕድ የተገኘ

በፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ የሳይበር ጥቃት በስምንት እጥፍ ጨምሯል

በ2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ2012 ዓ.ም ከተደረጉ የሳይበር ጥቃቶች ጋር ሲነፃፀሩ የስምንት እጥፍ ጭማሪ ማሳየታቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለፀ።
https://www.press.et/?p=83549

See also  ትግራይ በራች! ደግ ዜና እየተሰማ ነው

🇪🇹 መረጃ 12 ከአሚኮ የተገኘ

10ኛው የጣና ፎረም በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ

10ኛው የጣና ፎረም የደኅንነት ስጋቶችን መቆጣጠር፤ ተጽዕኖዎችን የመቋቋም አቅምን በአፍሪካ ለመገንባት” በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡ ፎረሙ በአፍሪካ የሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል፡፡

🇪🇹 መረጃ 13 ከኢፕድ የተገኘ

የአፍሪካ – ቱርክ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኤክስፖ 2022 በኢስታንቡል ተካሄደ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ የአፍሪካ እና የቱርክ ሞዴሎች የኢትዮጵያን የባህል ልብስ ያስተዋወቁበት የአፍሪካ – ቱርክ ጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኤክስፖ 2022 በኢስታንቡል ተካሄደ።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=416057437384384&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 14 ከጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የአይነት ድጋፍ ተደረገ

ጉምሩክ ኮሚሽን ለደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ሚዛን አማን በመገኘት ለሰብሰዊ ድጋፍ የሚውል ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የአይነት ድጋፍ አድርጓል።

🇪🇹 መረጃ 15 ከኢፕድ የተገኘ

ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡላቸውን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞችን እየተቀበሉ ነው

ጎንደር፣ ወሎ፣ ወልዲያ፣ አዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ፣ ሰላሌ፣ አሶሳና ደንቢ ዶሎ ዪኒቨርሲቲዎች በሁለተኛው ዙር የተመደቡላቸውን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች መቀበል ጀምረዋል፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=416140684042726&id=100069403920568

🇪🇹 መረጃ 16 ከኢዜአ የተገኘ

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የወጣቶችንና ታዳጊዎችን ተሳትፎ ለማጎልበት እየተሰራ ነው

በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የወጣቶችንና ታዳጊዎችን ተሳትፎ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በክረምት ወራት እረፍታቸው ለሁለት ወራት አሰልጥኖ ዛሬ አስመርቋል።

በሳይንስ ሙዚየም በተካሄደው የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio

Leave a Reply