የአገር ጥሪ ተቀብለው መከላከያን የተቀላቀሉ የኢትዮጵያ ልጆች

“ታላቁን ተቋም” ሲሉ ዜጎች ክብርና ፍቅር፣ እንዲሁም ድጋፋቸውን የሚያጎርፉለት የአገር መከላከያ ከለውጡ በሁዋላ እጅግ መዘመኑ በየመድረኩ እየተገለጸና ምስክርነት እየተሰጠው ነው።

ከቢሮው ጀመሮ በሰፋፊ አደረጃጀቶችና የሙያ መስኮች ራሱን መልሶ ያደራጀው መከላከያ ዛሬ ላይ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም እየሆነ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። “በዘር ፖለቲካና አወቃቀር እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ በእናንተ እጅ ናት” በሚል ሰፊ አደራ የተረከበው የአገር መከላከያ ሰራዊት በቅርቡ ከአፍሪካ ቀዳሚ ለመሆን እየተንደረደረ ያለ የአየር ሃይልም ገንብቷል። ባህር ሃይሉም ዘመናዊ የጦር መርከቦች ባለቤት ሆኖ ኢትዮጵያን በውሃ ላይ ሳይቀር ለመጠበቅ እየተንደረደረ ነው።

ዘመናዊ አደረጃጀት ብቻ ሳይሆን ዘመናዊና ወቅቱ የሚጠይቀውን የወታደራዊ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ባለቤት እንደሆነ አመራሮቹ በግልጽ ለህዝብ “አትስጉ እኛ አለን” ሲሉ የገለጹለትን መከላከያ ሰራዊት ይበልጥ ለማጠናከርና መላ የአገሪቱን ድንበር ከሚሞከሩና ከሚታሰቡ ጥቃቶች ለመታደግ የአዳዲስ ምልምል ወታደሮች ቅጥር ሰሞኑንን ተካሂዶ ነበር።

ጥሪውን ተቀብለው ከመላው ኢትዮጵያ ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነፃነት ዘብ ሊቆሙ ከፊት የቀደሙ የኢትዮጵያ ልጆች በኢትዮጵያዊነት ስሜት ብቻ ስልጠና ወስደው አገራቸውን ለማገልገል ልምምድ መጀመራቸውን የሚያሳይ መረጃና ስዕል ይፋ ሆኗል።

“ክብርና ታላቅነት ለቁርጥ የኢትዮጵያ ልጆች” በሚል ምስጋና እየቀረበላቸው ያሉት የኢትዮጵያ ልጆች፣ ጥሪውን ተከትሎ “ምርት አትሰብስቡ፣ ስራ አትቀጠሩ …” እያሉ ሲቀሰቅሱ የነበሩ እንዳሰቡት ሳይሆን፣ ወላጅ ፈቅዶና ወዶ ወደ ስልጠና የሸኛቸው መሆናቸውን ምልመላው በተካሄደባቸው አካባቢዎች ሁሉ የታየው የሽኝትና የቤተሰቦች ስንብት ህያው ምስክር ነው።

ኢትዮጵያ በክህደት አንገቷን ታንቃ ስትቃትት ነቅለው ወደ ማስልጠኛ በመግባት የታደጓትና ህይወታቸው ያለፉ የሚታወሱበት፣ ክብር የሚያገኙበት፣ መታሰቢያቸው ከፍ ብሎ የሚቆምበት፣ ቤተሰቦቻቸውን አገር በአደራ የምትረረከብበት፣ እውቅና የሚሰጥበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ኢትዮጵያን መጠበቅ የትውልዱ ሁሉ አደራ ነው!!

See also  "በተደራጀ ሌብነትና ሙስና ላይ የተጀመረው እርምጃ ሀገርን ከዘረፋ የማዳን ህዝባዊ ትግል ነው"

Leave a Reply