የሩሲያው ስፑትኒክ ዜና አገልግሎት አዲስ አበባን ጨምሮ አስራሁለት አፍሪካ አገራት ስራ ሊጀመር ነው

የሩሲያው ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ ዜና አገልግሎትና ሬዲዮ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ12 የአፍሪካ አገራት ጋዜጠኞች የዜና አገልግሎት እንደሚጀምር ታወቀ። ዓላማው አፍሪካዊያን የተጣራ እውነተኛ መረጃ እንዲያገኙ ታስቦ ነው። በሌላ አነጋገር በምዕራብ አግተራትና በአሜሪካ ቅጥረኞችን በማዘጋጀት አፍሪካውያን በራቸው ልጆች አገራቸው ላይ የሚረጭባቸውን ዜና ለማመጣጠን ነው። ለዚህም በመረጃ ማጣራት፣ በዜና አፃፃፍ፣ በፎቶና ምስል ቀረፃ ዙሪያ በሞስኮ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ቫሲሊ ፑሽኮቭ፤ ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የሚዲያ ስራ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

አፍሪካውያን የሩሲያን አቋምና እውነታ ለመረዳት የሌሎች ምዕራባውያን ሚዲያ መጠበቅ ስለሌለባቸው የሩሲያው ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ ዜና አገልግሎትና ሬዲዮ ይበልጥ ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም ሩሲያና አፍሪካውያን የተጣራና እውነተኛ መረጃ ከመነሻው ማግኘት እንዲችሉ ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ ዜና አገልግሎትና ሬዲዮ በአፍሪካ ቢሮ ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡም ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ ሊከፍቱ እንደሆነ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የሚከፈተው የስፑትኒክ ዓለም አቀፍ ዜና አገልግሎትና ሬዲዮ ማስተባበሪያ ቢሮ በአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋዎች፣ በአማርኛና በሌሎችም ሀገርኛ ቋንቋዎች አገልግሎት ይጀምራል ብለዋል።

ኤጀንሲው በአፍሪካ ያለውን የመረጃ ተደራሽነት ለማስፋፋት በሌሎች አገሮችም ቢሮ የሚከፍትበት አጋጣሚ እንደሚኖር ነው የጠቀሱት።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ አፍሪካውያን የሩሲያን ትክክለኛ አቋም ከሌሎች ምዕራባውያን ሚዲያዎች ሳይሆን ከራሷ ሚዲያዎች መረዳት እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የሚከፈተው የስፑትኒክ ዓለም አቀፍ ዜና አገልግሎትና ሬዲዮ ማስተባበሪያ ቢሮም መረጃን ከምንጩ ለማግኘት ያስችላል ብለዋል። የጀርመን ድምጽ፣ አሜሪካ ሬዲዮና ቢቢሲ አማርኛ በ”ኢትዮጵያዊያን” ኢትዮጵያ ላይ ሚዛኑንን የሳተና የሚዲያዎቹ ቀለብ ሰፋሪዎችን ዓላማ የሚያሳካ ቅስቀሳ ሲያስተላለፉ ማየት የተለመደ ነው። በተለይም ያለፉት ሶስትን ዓመታት ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ከፍተው ሲወጓት ከነበሩት መካከል የተጠቀሱት ሚዲያዎችና አብዛኞቹ ሰራተኞች በገሃድ ግብራቸው መታየቱ የሚካድ አልነበረም። አሁንም በዛው እንደቀጠለ ነው።

See also  በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተፈጸመ ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ

ዜናው የኢዜአ ሲሆን መጠነኛ አሳብ ተጨምሮበታል።

Leave a Reply