ከአሸባሪው ነፃ የወጡ የህብረተሰቡ ክፍሎች እፎይታ

መከላከያ ሠራዊታችን በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ሠላም በማስጠበቅ እና ህብረተሠቡ በሰላም የተረጋጋ ኑሮውን አንዲኖር እየሠራ ነው ሲሉ የዛታ ወረዳ አስተዳዳሪ ቄስ ከበደ ብርሀኑ ተናግረዋል።

የዛታ ከተማ አስተዳደር በበኩላቸው ፣ አሸባሪው የህውሃት ቡድን ለራሱ አላማ ሊገለገልበት ያከማቸውን የአለም አቀፍ የእርዳታ እህል በጀግናው ሠራዊት ከባድ ምት ሲያርፍበት ትቶት በመፈርጠጡ ለደሀው ማህበረሰብ እርዳታውን ተደራሽ ማድረግ ችለናል ብለዋል።

አስተያየታቸውን ከሰጡት የዛታ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ሞገስ አበበ እና አቶ ደባሽ አለሙ አሸባሪው ህውሃት የስልጣን ፍላጎቱን ለማሳካት ሲል በግፍ ቀንበር ስር ሆነን ነፃነታችን ተነፍጎ ቆይተናል ያሉ ሲሆን መከላከያ ሠራዊታችን ከገባ ጊዜ ጀምሮ በሠላም ወቶ መግባት እና ሰርቶ መኖር እንደቻሉም ገልፀዋል።

የዛታ ወረዳ ሠላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታወይ አለሙ በበኩላቸው በሠራዊታችን ድል የተሠማቸውን ደስታ ገልፀው፣ በቀጣይም ህዝባችን ለአሸባሪው ህውሃት ፕሮፖጋንዳ ሳይሸበር ከፀጥታ አካላት ጎን ሆኖ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እና የተፈናቀሉ ወገኖችም ወደ ቀያቸው እንዲመለሡ ጥሪ አቅርበዋል።

ታድላ መላኬ
ፎቶ ግራፈር ልመንህ ሻውል ENDF Facebook

See also  በትግራይ የዕለት ደራሽ እርዳታ የማድረስና ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ስራዎች ቀጥለዋል – የሠላም ሚኒስቴር

Leave a Reply