ወለፈንድ ፖለቲካ !

ዲያስፖራ የከተመውን ጽንፈኛ የአማራ ብሄረተኛ የሚስተካከል የፖለቲካ ደና##ርት ያለ አይመስለኝም። ምክንያቴን ላስረዳ :

፩. ወያኔ በዕብሪት ተወጥሮ ወረራ ሲጀመር እነ እንቶኔ ” ጦርነቱ በህወሃትና ብልጽግና መሀከል ነው አማራ አይመለከተውም የሚል ተንበርካኪ ስብከት ጀመሩ። ጀንፈሎቹን ይሄን ስብከት ሲዘምሩ ህወሃት አፋርና አማራ ክልል ገብታ ሆስፒታልና ት/ቤት እያወደመች ፣ ሴቶችን እየደፈረች ይቃወሙኛል ብላ የምታስባቸውን ወጣቶች እየገደለች ነበር። ይህ ብቻ አይደለም የጦርነቴ ግብ ወልቃይትን ራያና በትግራይ ክልል ማቆየት ነው ስትል አቋሟን ግልጽ አድርጋለች።

፪. ጀንፈሎቹ በዚህም አላበቁም መከላከያ ጸረ ህወሃት ዘመቻውን ለማጠናከር የወታደር ምልመላ ሲያደርግ ” የአማራ ወጣት መከላከያን አትቀላቀል ” ዘመቻ ጀመሩ። ህወሃትም ይህንን እንደምትል ልብ ይሏል። ይህ ብቻ አልበቃም ከብርሃኑ ጁላ እንስቶ ፣ አበባው ታደሰና የሰራዊታችን አባላት ጃንፈሎቹ ባቋቋሟቸው ሚዲያዎች ይሰደቡ ጀመር ፣ ህይወቱን ገብሮ ሀገር የታደገው ሰራዊት በአደባባይ ” ፈርጣጭ ፣ ኦነግ ” የሚል ዘለፋ ተለጠፈበት።

፫. የጀንፈሎቹ ነውር በዚህ አያበቃም። ሰራዊታችን እነ ቆቦን ፣ አዳርቃይን ነጻ ማውጣት ሲጀምር የድሉ ባለቤት እኛ ነን ማለት ጀመሩ።

፬. ትናንት እንደሰማነው የዲያስፖራ ጀንፈል ከሽብር ሀይሉ ጋር በሚደረገው ድርድር አማራ መወከል አለበት ሲሉ ‘ ተወካዮቻቸውን’ መርጠዋል። በድርድሩ አማራ ይወከል ከተባለ የኢትዮጵያ 85 ብሄረሰቦችም ሊወከሉ ይገባል። ለስሙ ” አንድ አማራ ለሁሉም ሁሉም አማራ ለቅብጥርሶ ” የሚለው ስብስብ የኢትዮጵያ መንግስት ድርድር ቡድን ውስጥ ያሉትን እነ ደመቀ መኮንን ፣ ተመስገን ጥሩነህ አማሮች አይደሉም እያለን ነው። እነ ደየስአለኝ ጫኔ ምርጥ አማሮች ናቸው ነው ነገሩ።

፭ . ጀንፈሉ ዲያስፖራ የአማራ ክልልን የትርምስ ቀጣና ከማድረግ ያለፈ አላማ የለውም። ትናንት አሳምነው ጽጌን አሟሙቁ የክልሉን ልሂቃን ማስጭልፍጨፉን ረስቶታል ከዚህ ስህተቱም ሊማር አይፈልግም። በዚህ ሰሞን ጥቂት ዶላሮች ልኮ 12ሺህ ተማሪዎች ፈተና ጥለው እንዲወጡ አድርጎ ብህይወታቸው መቀለዱን ጀንፈሉ ዲያስፖራ ዛሬም ሊማርበት አይፈልግም። መሬት ላይ እዚህ ግባ የሚባል ድርጅት የሌለው ጀንፈል ፓርቲ በፌቡ አድማ ያፈርሳል ፣ በሳል ምሁራንን አንገት ያስደፋል የገቢ ምንጭ የሌላቸውን እነ ጄነራል ተፈራ ማሞን አይነት የዋሆች ደሞዝ እየቆረጠ ስድስት ድስት ያስጥዳቸዋል ፣ ወላፈኑ ሲመጣ ጥሏቸው ዞር ይላል።

See also  ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ

ለማጠቃለል ይሄ ጦርነት የተካሄደው መንግስታዊ ስልጣንን በሽብር እቆጣጠራለሁ ባለው ህወሃትና የፌዴራል መንግስቱ መሀከል ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ዘር ሀይማኖት ሳይቆጥር ልጆቹን ለመከላከያ ሰራዊቱን የሰጠው የሀገሪቱን ሉዐላዊነት እንዲከበር እንጂ በብሄር ድርጅቶች መሀከል ድርድር እና የስልጣን ክፍፍል እንዲካሄድ አይደለም። የመጪው ድርድር አላማ ህወሃት ትጥቅ ፈቶ አለኝ የሚለውን የፖለቲካ ጥያቄ በሀገሪቱ ህጎችና ተቋማት ማዕቀፍ ለውይይት እንዱያመጣ ለማስገደድ ነው። ድርድሩ የብሄር ልሂቃን የስልጣን ክፍፍል መድረክ አይደለም ሊሆንም አይገባውምም።

By Samson michaliolovich

Leave a Reply