ሳሚ ዶላር ከ25 አጋሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ – “እሪልስቴቶች ዶላር ያጥባሉ ቃኙዋቸው” ሕዝብ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ብርቱ ክትትል በህገ-ወጥ መንገድ መንገድ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር (ከአምስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር) በላይ ሲያንቀሳቅስ የነበረ ግለሰብ ከ25 ግብረ-አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ገለፀ፡፡ ዜናውን የሰሙ ” በነካ እጃችሁ ወኮሎቹ ጋር ጎራ በሉ” ሲሉ ተደምጠዋል።

በወንጀሉ የተጠረጠረው ሳሙኤል እጓለ አለሙ በቅፅል ስሙ ሳሚ ዶላር የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱን በአዲስ አበባ ከተማ በማድረግ ወደ አሜሪካን ሀገር በተደጋጋሚ የሚመላለስ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች፣
የቤት እና የቢሮ እቃዎች
እንዲሁም ተዛማጅ መገልገያዎች የችርቻሮ ንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬና በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ በራሱና ዮዲት እጓለ አለሙ ከተባለች እህቱ ጋር በመሆን በስማቸው በተለያዩ ባንኮች በከፈቷቸው ሃያ አምስት የባንክ አካውንቶች በአንድ ዓመት ውስጥ ከ247 ሚሊየን ብር (ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሚሊየን ብር) በላይ ማንቀሳቀሳቸውን ፖሊስ ደርሶባቸው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ግለሰቡ ከሃያ አምስቱ የወንጀል ግብረ-አበሮቹ ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር (ከአምስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር) በላይ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበር በቅድመ ምርመራ ተደርሶባቸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በሕገ-ወጥ የውጭ ሀገር የገንዘብ ዝውውር፣ በግብር ስወራ ወንጀል እና ከህወሃት የሽብር ቡድን ጋር የግንኙነት መረብ በመፍጠር ከፍተኛ ገንዘብ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በአጠቃላይ በአንድ ዓመት ውስጥ 5,248,000,000 በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቅሱ እንደነበር ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ደርሶባቸዋል ሲል የዘገበው የፌዴራል ፖሊስ ነው።

በተያያዘ ይህን ዜና የሰሙ ራሳቸውን “ባለሃብት” የሚባሉትን፣ ሰው ግን በተለምዶ “ወኪል” እያለ የሚጠቋቆምባቸው በተመሳሳይ ስራ የተሰማሩ ስለመሆናቸው አስታውቀዋል። አቀባባዮቹም እነማ እንደሆኑ ስውር ባለመሆኑ መንግስት በነካ እጁ ጎራ ይበል ሲል ጥቆማ ሰጥተዋል። ዱባይ ላይ ሃብት የከመሩትና እግራቸው አዲስ አበባ የሆነውን፣ ለራሳቸው የውጭ ድርጅት በራሳቸው የአገር ቤት ድርጅት ኤል ሲል እየከፈቱ የሚመዘብሩት በደንብ ስለሚታወቁ መንግስት ዙሩን እንዲያከረው አሳስበዋል።

See also  “ብልህ የፖለቲካ መንገድ…የሰከነ የፖለቲካ ባህልን መምረጥ ያዋጣል" ይልቃል ከፋለ

አሁን ላይ የውጭ ብር መንዛሪዎች አዲስ አበባ ዙሪያና ቅርብ በሆኑ ከተሞች የሚኖሩ እንድ ፍሬ ልጆችን በመቅጠር ነው የሚያሰሩት። በስማቸው ተያዥ አድርገው ገንዘብ በማስገባት በጥቁር ለሚመነዘርላቸው አካላት በአድራሽነትና አስተላላፊነት በወር እስከ 30 ሺህ ብር እንደሚከፈላቸው ብር ተልኮለት የተቀበል ዳያስፖራ ብሩን ከሰጥችው ልጅ መረጃ ማግኘቱን አመልካቶ ነው አሰራሩን ያስታወቀው።

አብዛኞቹ በስም የሚታወቁ የድርጅት ባለ ቤቶችና ሪል እስቴት ስር የሚንቀሳቀሱ በውጭ ምንዛሬ አጠባው ዋና ፊት አውራሪ መሆናቸውን ጥቆማ የሰጡት አመልክተዋል።

እሪልስቴ ዙሪያ ያሉ አብዛኞቹ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚያከማቹትን ሃብት ወደ ውጭ ስለሚያሸሹና በውክልና ድርጅቱን ላቆሙላቸው ዛሬ ላይ ሃብት የሚያስተላለፉትም በውጭ ምንዛሬ ብቻ በመሆኑ ዶላሩን እየለቀሙ ኑሮ እንዲግል፣ ህዝብ እንዲማረርና መንግስት ላይ እንዲነሳ ኢኮኖሚው ላይ ሚስማር የሚመቱት መሆናቸውን ጠቋሚዎቹ ስም ዘርዝረው ልከዋል። ሆኖም አዘግይተነዋል። ዶላር የሚዛወርባቸውን ቤቶችና እናውቃቸዋለን ያሉትን ተሽከርካሪዎች ሳይቀር ጠቁመዋል።

አብዛኞች እንደሚሉት በዚህ ሌብነት የተሰማሩት ቀደም ብለው ከትህነግ ጋር አብረው ሲነገዱና በውክልና “ምስለኔ ሃብታም” የሚባሉት ናቸው። ንብረት በተጋነነ ብር በመግዛት በቋሚ የወኪሎቻቸውን ብር የቻሉትን በውጭ ምንዛሬ፣ ያልቻሉትን በአገር ውስጥ በቋሚ ንብረት ላይ በማስቀመጥ ደሃው ቤት እንዳይገዛ፣ መሬት ወስዶ ጎጆ እንዳይቀይስ ዋጋውን እንዳናሩበት መረጃውን የላኩት አመልክተዋል። መንግስት ቆርጦና ወስኖ እነዚህ አካላት ላይ ከዘመተ ተመሬትና የቤት ዋጋ በቅጽበት እንደሚሽቆለቆል በዕምነት ተናግረዋል።

መንግስት በአዲሱ ዓመት ሌብነት ላይ እንደሚዘምት፣ ዘመቻውንም ለመጀመር ዝግጅት ላይ እንዳለ ዳግም ወረራ መቀስቀሱ ይታወሳል። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ ” ሌባ ሊመነጠር ሲል ጦርነት መክፈት ምንንን ለማሰናከል ታስቦ እንደሆነ ይታወቃል። ሁሉም ጎን ለጎን ይሄዳል” ማለታቸው ይታወሳል።

Leave a Reply