ኃይል የተቋረጠባቸውን የአፋር ክልል ወረዳዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የመሰረተ-ልማት የመልሶ ግንባታ ሥራ ተጠናቀቀ

አሸባሪው የህወሃት ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው የቆዩ ከወልዲያ ተንቀሳቃሽ የማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ያገኙ የነበሩ የአፋር ክልል ወረዳዎችን እንደገና ተጠቃሚ ለማድረግ የኤሌክትሪክ መስመር የጥገና፣ የመልሶ ግንባታና የአዲስ መስመር ዝርጋታ ሥራ መጠናቀቁን የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል፡፡

በጥገና ስራው 52 ነጥብ 36 ኪሜ የዝቅተኛ መስመር፣ 120 ነጥብ 35 ኪሜ የመካከለኛ መስመር እና 21 ትራንስፎርመሮች የመትከል ስራ ተሰርቷል፡፡

ሆኖም ተቋሙ ጥገናውን ቢያጠናቅቅም በህወሃት ተዘርፎ በተወሰደው ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ምክንያት በክልሉ ዞን አራት ስር የሚገኙት ጭፍራ፣ እዋ፣ ከልዋንና አውራ ወረዳዎች እስካሁን ኤሌክትሪክ ሳያገኙ ቆይተዋል፡፡

ስለሆነም የሚገነባው ተለዋጭ የማከፋፈያ ጣቢያ ሲጠናቀቅ እነዚህ ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል አብኣላ፣ በራህሌ፣ ኮነባ፣ ኢረብቲ እና መጋሌ የሚባሉ የአፋር ክልል ዞን አንድ ወረዳዎችን ዳግም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ የጉዳቱ መጠን ለማጥናትና ወደ ጥገና ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

በሁሉም የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ውድመት የደረሰበትን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት የፍተሻ ስራውን በማጠናቀቅ ወደ ጥገና መገባቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

See also  ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና በድርጊቱ የተሳተፉትን ለህግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

Leave a Reply