ለገዢው ፓርቲ ከምጠይቀው አንዱ |

በምእራባዊያን NGO የተተበተበ ነበር። በዚህ ተጨባጭ ውስጥ ሆነው አሜሪካን እያጣጣሉ፤ ምእራባዊያንን እቀወቀሱ፤ ለሩሲያና ቻይና ድጋፋቸውን በቅን የሉአላዊነት ስሜት ሲገልፁ ነበር። ይህ ግን አይሰራም። ጉዳዩ መንግስታዊ ግልፅ ፖሊሲ ይጠይቃል፤
“አናጎነብስም!”ቅድሚያ ለሀገር ክብር የሚል መሪ አዲስ ፖሊሲ ቀርፆ ክፍተቶች እስኪስተካከሉ በሚኖሩት ጥቂት አመታት ከዜጎች ጋር ተቀናጅቶ መፅናት የሚጠይቅ ሲሆን፤
በምእራባዊያን ተረጂነቲ ስር የሆነ መንግስት ሰጥ ለጥ ብሎ ለነሱ መታዘዙ፣ ቢያንስ ቢያንስ “አገር አገር እየፎከሩ ሕዝቡን እንደ ኢምራን ካሃን ደጋፊዎች ቆሽት ከሚያደብን ጣጣ ይታደጋል።


የዓባይ፡ልጅ

▪️የውጭ NGOዎች እና አለም አቀፍ የድጋፍ ትብብሮችን የሚመለከቱ ህገ-ደንቦች እንደገና ይፈተሹ፤ ሉአላዊነትና ደህንነትን እንዲያስከብሩ ሆነው ይዘጋጁልን። ይህ መሰረታዊ ጉዳያችን ነው!!
የሀገሬ ልጆች ሆይ ይህ የውጭ መዳፍ በህግ እስካልተገደበ ድረስ አብዮት ብታደረግ ትርፍህ ዘጭ-ዘጭ “የግብፅ አብዮት” አይነት ነው መጨረሻው..። (የምእራባዊያን) ተረጂ መሪ የቱንም ያህል ህዝብ ቢወደው ተሳስቶ “እንከባበር” ባለበት ማግስት እንደ ኢምራም ካን ሲያደርጉት ትመለከታለህ ማለት ነው።

ሀገራችን ከዚህ እስር ቤት እስካላወጣች ድረስ ልፋታችን ሁሉ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው። ሕዝቡ አብዮት አድርጎ ስርአት ቢለውጥ ተመልሶ ከምእራባዊያን አዘቅት ይዘፈቃል። ሕዝብ የወደደውን ሰው መርጦ መሪ ማድረክ ቢችልም እንኳ ተመፅዋች ነውና “ቅድሚያ ለዜጎቼ፤ ለሉዓላዊነታችን” በሚል ሰአት የለጋሽ አለቆቹ አይኖች ይጉረጠርጡበታል። ወደ አለቆቹ ሲዞር ደግሞ አገር ሻጭ ይሆናል/ይባላል።
ብዙ በተባለለት የግብፆች አብዮት ሆስኒ ሙባረክን ፈንቅሎ በአብላጫው ዜጋ ሙሐመድ ሙርሲን ወደ ስልጣን ቢያመጣውም፤ ግብፅ በሁሉም ዘርፍ ተረጂ ናትና ህዝባዊው ሙርሲ ገና ስልጣን እንደጨበጠ ነበር በሀገሪቱ የነዳጅና ምግብ እንዲሁም የሸቀጦች እጥረት፣ ግሽበት ወዘተ…የተንሰራፋው። አልሲሲ ወደ ስልጣን እንደመጣ ታዲያ የጠፋው ሁሉ ተትረፈረፍ ይሉናል።(መጨረሻ ላይ ካስቀመጥኩት የቪዲዮ ሊንክ ስለጉዳዩ መስማት ትችላላችሁ..)
አል-ሲሲ በፈረንጆች 2013 በመፈንቅለ መንግሰት ሲመጣ ወደ ስልጣን ሲመጣ ዴሞክራሲ ተደፈረ ብሎ የሚቆጣው ሀገር አልተመለከትንም። አልሲሲን በመቃወም በተደረጉ ተከታታይ ሰልፎች የተገደሉ ግብፃዊያን በግብፅ አብዮት ከሞቱት የበለጠ አሃዝ ያስመዘገበው በአልሲሲ የመጀመሪያዎቹ 4 የስልጣን አመታት ብቻ ነበር። አሁን ላይ ከ 60 ሺህ በላይ ግብፃዊያንን እስር ቤት ወርውሯል። የአልሲሲ ስልጣን ግን ቀጥሏል። የአሜሪካ የቢሊዮን ዶላሮች ድጋፍና የዘመናዊ ጦር መሳሪያ ድጋፍ አሁንም አልተለየውም። የግብፃዊያን አብዮት መሪውን ቢያነሳም ከምእራባዊያን መዳፍ ነፃ አልነበረምና ግቡን አልመታም። ጭራሽ የአል-ሲሲ አገዛዝ ነው የመጣባቸው። ይህ አጋርነት ኖሮት እንኳን አልሲሲ ከምእራባዊያን ጫና ግን መቶ በመቶ አልተላቀቀም። እስከ አምስት ለሚደርሱ የአሜሪካ Lobby ድርጅቶች በዬወሩ ለያንዳንዳቸው በሚከፍለው እስከ 180 ሺህ ዶላር ዳረጎት የስልጣኑን ክፍተቶች እየደፈነ ቀጥሏል። መንግስት ነው ሉአላዊ አይባልም ትንሽ ዞር ልበል ካለ ያልቅለታል፤ ግብፃዊያን ከሙባረክ የባሰ አንባገነናዊ ስርአት ስር ቢሆኑም መሪው አል-ሲሲ ከዜጎች በላይ በሆነው የዋሽንግተን አምባገነንነት ስር ጥሩ አጎንባሽ መሆን ችሏልና ነገሩ እዚህ ስር ተቀብሯል..።
በስሪላንካ የራጃፓእሳ መንግስት እንዲሰናበት ተጨባጩ ምክንያት ከአሜሪካ ተረጂነት ሳይወጣ ፀረ አሜሪካ ፖሊሲ ልከተል ማለቱ ነበር። ሀገሪቱን የኢኮኖሚ bankruptcy ላደረሰው ሙስና ዜጎች መቃወማቸው ሽፋን እንጂ ጉዳዩን የቋጨው በሀገሪቱ ቢሮዎች ያሏቸው USAID NED እና መሰል NGOs ነበሩ። የዜጎች ድምፅ ለውጥ ቢያመጣማ ኖሮ ለፓኪስታኑ ኢምራን ካሃን ነበር የሚሆነው።

See also  የመንግስት ምስረታው እና ከፊቱ የተቀመጡ ከበባድ የቤት ሥራዎች

ጣልቃ ገብነትን ሲያወግዝ የሚገኝ የኔ አይነት የሀገሬ ልጅ፣ ይፋዊ አስተያየቱ እንደ ሀገር በህጋዊ አሰራር እስካልተደገፈ ድረስ ውጤቱ የግል ጠላቶቹን ማብዛትና ተጎጂ መሆን ብቻ ነው። አንዳንድ ሀገራት ይህን መሰል ህገ-ደንብ ሲያወጡ ተከትሎ የሚመጣ ምጣኔ ሐብታዊና የዲፕሎማሲ ጫና ቢኖርም፣ ከምእራባዊያን ውጭ አማራጭ የአጋርነት ዕድል ከፈጠሩ ሀገራት ላይ የሚገኙ እድሎችን በመፈተሽ፣ የውስጥ ንግግሮችን ቀደም ብለው በመጀመር ነው ክፍተት እንዳይፈጠር የሚያደርጉት።

የምንገኝበት ጦርነት መቋጨቱ አይቀርም( ወይም በቅርብ ይቋጫል)። ሀገራችን ተረጂ ናትና የሷ ጦርነት ከራሷ ለጋሾች (ከምእራባዊያን hybrid war) ጋር የተቀየጠ ነው። በጦር ሜዳ ካሸነፈች በድህረ ጦርነት ጣጣዎች ይመጡባታል። (በተለይም) የምእራባዊያን የእዳ ጫና አብሮ ሲመጣ ከሰብአዊ መብት ጩኸቶች ጋር አጣምረው ለማስጨነቅ የተመቸ ይሆንላቸዋል። እዚህ ላይ በተዛባ መረጃ የጥላቻ ንግግር ዘመቻን ያክሉበታል። ስሐ ውስጠዊ ችግራችን ከፍየሏ በላይ ይጮሃሉ፤ ዶላር እያፈሰሱ ዜጎችን በውል ባልገባቸው ጉዳይ ያስጮኃሉ። በዚህም ሀገሪቱ ያልተገባ/የማትሻቸውን የስምምነት ፊርማዎች ለማኖር ትገደዳለች።
ከዚህ አዙሪት ለመውጣት መወሰን ካልተቻለ በዬ አስር አመቱ ጦርነት በዬ አምስት አመቱ የማእቀብ ናዳ ሲያስጎነብሰን የምንቀጥል ይሆናል።
ህንድ ይህን ታሳቢ ያደረገ ህግ አውጥታ ተግብራ፤ በማሪያ ቴሬዛ ስም የተቋቋመውን ፋውንዴሽን ጨምሮ እንዲዘጉ የወሰነችባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ NGOs ደርሰዋል። የህ ለምን ይመስልሃል። ቻይና ቀደም ብላ ነበር አስተማማኝ የህግ አጥር ያበጀችው። ኤርዶጋን ከመፈንቅለ መንግስቱ ማግስት ጀምሮ ነበር። በዬአመቱም እንደሁኔታው ተጨማሪ ነገሮችን እየተገበሩ ናቸው። ባሳለፍነው ሳምንትም አዲስ የሲቪክ ተቋማት ህግ በማፅደቋ NGOs እና ምእራባዊያን እየተንጫጩ ነበር። ከሚያንጫጩ ቢንጫጩ አይሻልምን?

ወደ ሲሪላንካው ራጃፓክሳ እና የፓኪስታኑ የኢምራን ካሃን መንግስት በምእራባዊያን NGO የተተበተበ ነበር። በዚህ ተጨባጭ ውስጥ ሆነው አሜሪካን እያጣጣሉ፤ ምእራባዊያንን እቀወቀሱ፤ ለሩሲያና ቻይና ድጋፋቸውን በቅን የሉአላዊነት ስሜት ሲገልፁ ነበር። ይህ ግን አይሰራም። ጉዳዩ መንግስታዊ ግልፅ ፖሊሲ ይጠይቃል፤
“አናጎነብስም!”ቅድሚያ ለሀገር ክብር የሚል መሪ አዲስ ፖሊሲ ቀርፆ ክፍተቶች እስኪስተካከሉ በሚኖሩት ጥቂት አመታት ከዜጎች ጋር ተቀናጅቶ መፅናት የሚጠይቅ ሲሆን፤
በምእራባዊያን ተረጂነቲ ስር የሆነ መንግስት ሰጥ ለጥ ብሎ ለነሱ መታዘዙ፣ ቢያንስ ቢያንስ “አገር አገር እየፎከሩ ሕዝቡን እንደ ኢምራን ካሃን ደጋፊዎች ቆሽት ከሚያደብን ጣጣ ይታደጋል።

See also  BRICS አዳዲስ አባል ሀገራትን በይፋ መቀበሉን አስታወቀ፤ ውሳኔው ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ውጤት ነው ተብሏል

ሺዎች ከሞቱለት በኋላ ህልማቸው በጣል ቃገብነት እንደተጠለፈባቸው የግብፅ አብዮተኞች “ከንቱ ሟች” ከመሆን ያድናልና ተረጂ እንደ ተረጂ አክት ማድረግ የብፁዕነት ያህል ነው!

ብልፅግና ፖርቲ ሆይ የዜጎችን ድካም ዋጋ ስጠው!
#የዓባይልጅ Esleman Abay

https://eslemanabay.com/regime-change-role-of-international-republican-institute-iri-in-sri-lanka/
https://youtu.be/kHqUQf-5QRA

Leave a Reply