የስንዴ አብይዮት፣ የትውልድ ማሳ

ስንዴም ሕጻናትም ማሳ ይፈልጋሉ

ሰሞኑንን አስደማሚ መረጃዎች በቪዲዮ ተደግፎ እየተሰራጨ ነው። ስንዴ የሚወቃ ኮምባይነር ሲርመሰምስ እየታየ ነው። ይህ ያልተለመደ አስገራሚ ትንግርት በወጉ የሚያደንቀው ባያገኝም ዜጎች ግን መገረማቸውን እያሳዩ ነው። ስንዴ ብቻ ሳይሆን የልጆች መዋያ ማሳ ግንባያውም ከሳይንሱ ማበልጸጊያ ጋር እያበበ ነው።

ኢትዮጵያ አባይን ገድባ ስትጨርስ “ኒኩሌር ታጠቀች” ተባለ። ዛሬ ደግሞ የአፋር፣ የሶማሌ በረሃና አማራና ኦሮሞኢያ ደቡብ በስንዴ ምርት አብዮት ላይ መሆናቸውን ያዩና ውጤቱ የገባቸው ” ኢትዮጵያ ሁለተኛውን አደገኛ ኒኩሌር ልትታጠቅ ነው” እያሉ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ክብርንና ሉ ዓላዊነትን የሚጋፋው ባፍጢሙ ልመና ሊደፋ ነው። ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት እያሳየች ያለው እመርታ ዓለም በገሃድ ስሜቱን ባይገልጽም ይዞት የሚመጣው ክብርና የነጻነት ስሜት ስጋት ፈጥሯል። አፍሪካ ኢትዮጵያን ተከትላ ሆዷን ከሞላች አዲዮስ።

ቀደም ሲል ኪስ ቦታ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችና መናፈሻዎች ይቸበቸቡ ነበር። ጉልበተኞች በር ያሻቸውን እያጠሩ ሸጠዋል ወይም ገንብተውበታል። ዛሬ ደግሞ በየቦታው መዝናኛ እየተከፈተ ነው። አዲስ አበባ ብቁ ነው ባይባልም አረንጓዴ ሆና በውብ መዝናኛ እየበለጸገች ነው።

“የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ። የወዳጅነት ፓርክ ሁለተኛው ምዕራፍ ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን አብስረዋል። ፓርኩ ስፖርትን፣ ጨዋታንና ማኅበራዊ መስተጋብርን ያቀናጀ መሆኑን አስረድተዋል።

ልጆች እየተጫወቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ይለማመዳሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርኩ ወጣቶች መጽሃፍት ያነባሉ፣ ስፖርትም ይሰሩበታል ። ወላጆችና አያቶች ከልጆቻቸው ጋር መጥተው ማኅበራዊ ልምዳቸውን ይለዋወጡበታል።

አዲስ ተጋቢዎች በሠርግ ዐጸዱ ጋብቻቸውን ይመሠርታሉ ሲሉም ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን ሲሉ ነው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያስታወቁት ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ቁጥር ሁለት ወዳጅነት አደባባይን ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሲሆን ነው ይህን ያሉት።

See also  በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የዜጎችን መፃኢ ዕድል ለመወሰን

Leave a Reply