የንግግር ሂደቱ “ብዙ ጣልቃገብነት” እንዳጋጠመው ጠ.ሚ ዐቢይ ገለጹ

የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ያሉ አየርመንገዶችንን እና የፌደራል መሰረተ ልማቶችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ማለቱ ይታወሳል

ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት በፌደራል መንግስት እና በህሓት መካከል እየተካሄደ ያለው ንግግር ጣልቃገብነት እንዳጋጠመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ

በአፍሪካ ህብረት መሪነት በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ባለፈው ሳምንት ሰኞ በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ድርድር እንቀጠለ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሲጂቲኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ግጭቱን በሰላም የመፍታቱ ሂደት “ብዙ ጣልቃገብነት” እንዳጋጠመው ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት “ህወሓት ህገመንግስቱን እንዲያከብር እና ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ክልል” እንዲንቀሳቀስ ለማሳመን ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ህወሓት “ፍላጎችንን መገንዘብ የሚችሉ ከሆነ እና የራሱን ህገመንግስት የሚያክብር እና በህጉ መሰረት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ሰላም ይሰፍናል ብየ አስባሁ” ሲሉ ተናግረዋል ጠቅላይ ሚስትሩ፡፡

በኢትዮጵያ ጉዳይ “በግራ በቀኝ ብዙ ጣልቃገብነት” መኖሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያውያን መረዳት ያለባቸው የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን መፍታት አንደምንችል” ነው ብለዋል::

 የሰላም ንግግሩ ቢጀመርም ጦርነቱ አሁንም እየቀጠለ ነው፡፡

በድጋሚ ነሀሴ አጋማሽ ላይ በተቀሰቀሰው ጦርነት የህወሓት ሃይሎች እስከ ቆቦ ድርስ መግባት እና የተወሰኑ ቦታዎች መቆጣጠር ችለው የነበረ ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት መልሶ መቆጣጠር ችሏል፡፡

ጦርነቱ አሁን የቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ሽሬ፣አላማጣ እና ኮረምን እና ሌሎች ቁልፍ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠር መቻሉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

መንግስት ህወሓት ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በማበር የሀገር ሉአላዊነት እንዲጣስ ስላደረገ፣ በትግራይ ያሉ አየርመንገዶችንን እና የፌደራል መሰረተ ልማቶችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ሲል መግለጹ ይታወሳል፡፡

መንግስት በትግራይ ያሉ አየርመንገዶችንን እና የፌደራል መሰረተ ልማቶችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ማለቱ በጦርነቱ እንደሚገፋበት አማለካች ነው፡፡

 በህወሓት አስቸኳይ ተኩስ አቁም የድርድሩ ቀዳሚ አጀንዳ እንዲሆን እንደሚፈልግ መግለጹ ይታወሳል፡፡ የፌደራል መንግስት ያለቅድመ ሁኔታ እንደሚደራደር ከመግለጽ ባሻገር ፍላጎቱ ምን እንደሆነ በግልጽ አላስቀመጠም፡፡

VIA – አል-ዐይን

See also  ገላሳ ዲልቦ አረፉ

Leave a Reply