አሰሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተጠረጠረችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

 በአዲስ አበባ የገዛ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ወንጀል የተጠረጠረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

ወንጀሉ የተፈጸመው ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10:45 ሰዓት ሲሆን÷ ቦታው ደግሞ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አስኮ ሊዝ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

ተከሳሽ በቤት ሠራተኝነት ከቀጠረቻት ወ/ሮ ፋሲካ ተሾመ ጋር በመሃላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ሟችን በቡና ዘነዘናና በስለት የተለያዩ የሰውነት አካላቸው ላይ ጉዳት በማድረስ በመግደል ወንጀል መጠርጠሯ ን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ፖሊስ መረጃው ከህብረተሰቡ ከደረሰው በኋላ በአደረገው ብርቱ ፖሊሳዊ ክትትልና ምርመራ ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ከፈጸመች ከሦስት ቀናት በኋላ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ የቤት ሠራተኞችን ሲቀጥር በቂ ዋስትና ማቅረብ እንዳለባቸው ጭምር ሊያስገድድ እንደሚገባም ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

VIA FBC

See also  ደረሰኝ ሻጮቹና አገናኙ ደላላ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

Leave a Reply