ፖለቲካ – የትህነግ ወኪሎች ስካይ ላይን ናቸው ፤ ጌታቸው ረዳ ወደ ኮሙኒከሽን ?

እነ አቶ ጌታቸውና የቀድሞ ጀነራል ጻድቃን እንዲሁም ሌሎች የትህነግ ወኪሎች አዲስ አበባ ስካይ ላይት መሆናቸው ተረጋግጧል። ይዘዋቸው የመጡት የቀድሞ የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩትና አሁን በደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ሆነው እየሰሩ ያሉት ሙክታር መሀመድ ናቸው። ከትህነግ ሰዎች መካከል አቶ ጌታቸው በቀደመው ሞያቸው ፌደራል መንግስቱን የዶክተር ለገሰ ቱሉ ረዳት ሆነ በህዝብ ግንኙነት እንዲያገለግሉ መታጨታቸው ተሰምቷል።

በስካይ ላይ እንግዳ መቀበያ እነ አቶ ታከለ ኡማ፣ አቶ ግርማ ብሩና ሌሎች የቀድሞ ባለስልታኖች መታየታቸውን ተባባሪያችን ከአዲስ አበባ አመልክቷል። ይህም ስምምነቱ በመለካም መንገድ እየሄደ መሆኑንን የሚያሳይ እንደሆነ ተደርጎ ተውስዷል። እንደተሰማው ከሆነ በስምምነቱ ዋና ነጥብ መሰረት ትጥቅ የሚያስፈታውን ገብረ ሃይል ተደራጅቶ በነገው ዕለት ይፋ እንደሚሆን ነው።

ከዚህ ባለፈ ግን ነገሮችን ባስቸኳይ ለማሳለጥና ወደ ሙሉ መልሶ ግንባታ ለመግባት የቀድሞ ባለስልጣናት የአመቻቺነት ስራ እየሰሩ መሆኑንን ለጊዜው ስማቸውን ያልጠቀሱ ለኢትዮ12 አመልክተዋል። ይህም የሆነው በብልጽግናና በትህነግ ሰዎች መካከል መተማመንን ለማጎልበት በሚል ነው።

ወደ ደቡብ አፍሪካ ትህነግን ወክለው ለመሄድ ከቀረቡ ውስጥ መንግስት ” አይሆንም፣ እነዚህ ከአገር እንዲወጡ አልፈቅድም” በማለቱ መቀለ እንዲቀሩ የተደረጉ መኖራቸውን ሚስጢር ብለው እኚሁ ሰው ነገረውናል። ምክንያቱን ግን አላስረዱም።

ቲዲኤፍ የሚባለውና ዲያስፖራ የትግራይ ተወላጆች ” ብሶት የወለደው” የሚሉት ታጣቂ ሃይል “እንዴት ትጥቅ ይፈታል” በሚልና ” እስካልነኩን ደረስ ቢፈታ ምን ችግር አለው? ከነኩን እንደገና ይነሳል” በሚል ሁለት ክንፍ፣ ትጥቅ መፍታት መዋረድ እንደሆነ ጠቅሰው ” ተሸንፈናል” በሚል የተዥጎረጎረ አመለካከት የትህነግ ደጋፊዎች እሰጥ እገባ ውስጥ በገቡበት በአሁኑ ወቅት የትህነግ አመራሮች አዲስ አበባ ስካይ ላይት ያለ ደጋፊና አንጋች መገገኘታቸው ” ነገሩ ያበቃለት” እንደሆነ አመልካች ተደርጎ ተውስዷል።

በዲያስፖራ ያለው የትህነግ ደጋፊና የፊት ሰዎች በተለያየ አቋም ቢነታረኩም፣ የጀርመን ድምጽ ያነጋገራቸው የመቀለ ከተማና የተለያዩ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሰላም ስምምነቱ መደሰታቸውን፣ በመልካም እንደሚያዩት ሲገልጹ፣ የኤርትራ ወታደሮችን ትግራይ ውስጥ መቆየትን አስመልክቶ በግልጽ የተባለ ነገር አለመኖሩ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

See also  “ለኢትዮጵያ የተዘረጋው ወጥመድ ከወዲሁ እየተበጣጠሰ ነው”

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ቃል ሳይመርጡ በየቀኑ ሲሳደቡና አስረው ለፍርድ እንደሚያቀርቡ በተደጋጋሚ ሲያሳውቁ የነበሩት የትህነግ አፈቀላጤና የንግግር ቡድኑ መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ የፌደራል መንግስት ውስጥ በህዝብ ግንኙነት ስራ መሰማራት እንደሚፈልጉ ተሰምቷል።

ወደ ትግራይ የመመለስና ከተሰጣቸውም ሃላፊነት ወስደው የመስራት ፍላጎት እንደሌላቸው የሰሙ ፣ እንዳሉት አቶ ጌታቸው ብልጽግናና መሪው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚያከናውኗቸውን ተጋባራትና ስኬት በማስተዋወቅ ረገድ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ከገሰ ቱሉ ረዳት የመሆን እድል እንዳላቸው የወሬው ምንጮች አመልክተዋል።

አቶ ጌታቸው ሆኖ የፕሮፓጋንዳ ስራ ውስጥ ከገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሲያገኑ፣ ሲያስተዋውቁና ቀደም ሲል “ፋሽስቱ” ሲሉ የነበሩትን ቀይረው ” ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ” በሚል ተክተው ስኬታቸው አሽሞንሙነው ማውራት ይጀምራሉ።

የዜናው ምንጮች “ፖለቲካ ነው። ካድሬ የዛሬውን እንጂ የትናንቱን አያስብም” ሲሉ አቶ መለስ ህይወታቸው እስካለፈ ድረስ 18 ጊዜ ስልታን እንደሚለቁ መናገራቸውን ዋቢ አድርገዋል።

Leave a Reply