ህገ መንግስት

የሰላም ስምምነቱ እና ቀጣይ ሁኔታዎች! የኢፌድሪ ሕገ-መንግስት እንደ ዳኛ ?

1. ፈር መያዥያ !

በትላንትናው ዕለት በደቡብ አፍሪቃ በኢትዮጵያ መንግስትና በ ሕወሀት መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት፤ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ያስደሰተ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ይህ የሰላም ስምምት የሁለት አመቱን ሁለንተናዊ እልቂት ያስቆመ ከመሆኑም በላይ፤ በተለይም ደግሞ በሀገራችን ላይ ተደቅኖ የነበረውን የህልውና አደጋ በወሳኝነት የቀረፈ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ በዚህ የሰላም ስምምት በዋነኛነት አሸናፊዋ ኢትዮጵያ ናት፡፡ የትግራይ ህዝብ ደግሞ በብዙ መስፈርቶች ከዚህ የሰላም ስምምነት ቀዳሚው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ብቻ በአጭሩ የሰላም ስምምነት ላይ መደረሱ እጅግ አስደሳችና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታን ይዞ የሚመጣ እንደሆነ እሙን ነው፡፡

አሁን ጥያቄው ይህ የሰላም ስምምነት ምን ያክል ተግባራዊ ይናል? ተፈራራሚ ወገኖችስ ምን ያክል ለቃላቻው ይገዛሉ? የሚለው ነው፡፡ በእኔ እምት የሰላም ስምምነቱ በበርካታ ምክንያቶች የተነሳ ተግባራዊ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ ጉዳዩን ከመንግስት አንጻር ካየነው፤ የስምምነቱ አንቀጽ 7(2) ያስቀመጠው የመንግስት ግዳጅ የሚከተሉት ናቸው፡-

1) The Government of the FDRE shall:

a) Halt military operations targeting the TPLF combatants;

b) Expedite and coordinate the restoration of essential services in the Tigray region within agreed timeframes;

c) Facilitate the lifting of the terrorist designation of the TPLF by the House of Peoples’ Representatives;

d) Mobilize and expedite humanitarian assistance for all those in need in the Tigray Region and other affected areas, and ensure unhindered humanitarian access.

ስለዚህ እነዚህን የሰላም ግዳጆች ለመፈጸም በመንግስት በኩል አንዳችም ማመንታት ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ በአንቀጹ 7(2)(c) ላይ የተቀመጠው ግዳጅም ቢሆን፤ ፓርላመንታዊ የመንግስ ስርአት ለምትከተለው ኢትዮጵያ ከባድ አይደለም፡፡ በአጠቃላይ መንግስት የገባቸው ግዳጆች ያለምም ማመንታ ሊከወኑ የሚችሉ ናቸው ብየ አምናሉ፡፡

ጉዳዩን ከሕወሀት አንፃርም ቢሆን ስንገመግመው ስምምነቱ የመፈጸም እድሉ ትልቅ ነው፡፡ እውነት ነው ሕወሀት በአንቀጽ 7 (1) መሰረት የገባበቸው ግዳጆችን ስንመለከት፤ መንግስ ከገባበቸው ግዳጆች አንጻር ካነፃፀርናቸው ጠንከር ያሉ ናቸው፡፡እነዚህን የሰላም ግዳጆች እንመልክታቸው፡-

1) The TPLF shall:

a) Respect the constitutional authority of the Federal Government, all constitutional bodies and organs of the Federal Government, including but not limited to the authority of the Federal Government to control all federal facilities, institutions, and the international boundaries of the country;

b) Refrain from aiding and abetting, supporting, or collaborating with any armed or subversive group in any part of the country;

c) Respect the constitutional mandate of the Federal Government to deploy the Ethiopian National Defence Force as well as federal security and law enforcement agencies to discharge their responsibilities under the Constitution, relevant laws, and regulations;

d) Refrain from conscription, training, deployment, mobilization, or preparation for conflict and hostilities;

e) Halt any conduct that undermines the sovereignty and territorial integrity of Ethiopia, including unconstitutional correspondence and relations with foreign powers;

f) Cease all attempts of bringing about an unconstitutional change of government.

እንግዲህ ከሕወሀት የከረመ ጥሩ ያልሆነ ባህሪ ተነስተን እነዚህን የስላም ግዳጆች ስንመለከት ለሕወሀት እጅግ አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጅ ወቅቱ እነዚህን የሰላም ግዳጆች ተቀብሎ ከመፈጸም ውጭ ለሕወሀት ሌላ የተሻለ አማራጭ ስለሌለው፤ ሕወሀት በስምምነቱ መሰረት የመፈጸም እድሉ ከፍተኛ ይሆናል ብየ አምናሁ (90 %):: ይሄን ስልም የትገራይ አክራሪ ብሄርተኞች ሕወሀት በስላም ስምምነቱ እንዳይገዛ ሊፈጥሩበት የሚችሉትን አሉታዊ ተጽእኖ ግምት አስገብቸ ነው፡፡ ይሄም ሆኖ መቸም ጦርነቱ አልቋል፤ ድርድር ከማን ጋር? ወዘተ… እያለ ደብረሲና ደርሶ የተመለሰና፤ ወቅታዊ ቁመናው ደግሞ በመቀሌ ዙሪያ ብቻ ታጥሮ፤ በአለም አቀፉ ማህበረስብ ድጋፍ ሕይወቱን ያተረፈው ሕወሀት፤ቢያንስ ከአጭር ጊዜ አኳያ፤ የተሰጠውን በሂዎት የመቆየት እድል ከመጠቀም ውጭ ሌላ ነገር ያስባል ተብሎ ብዙም አይገመትም፡፡ ስለሆነም ሕወሀት ይሄንን የሰላም ስምምነት ተቀብሎ የመፈጸም እድሉ ስፊ ነው ብሎ መገመት ስህተት አይሆንም፡፡

See also  ወልቃይት-ጠገዴ እና ጠለምት፤ ዐማራጭ የመፍትሔ ሀሳቦች!

2. ቀጣይ ሁኔታዎች!

አሁን በፌደራሉ መንግስትና በሕወሀት መካል የተደረሰው ስምምነት አጠቃላይ የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ ሲሆን፤ ትኩረቱም በዋነኛነት የአገራችንን የህልውና ስጋት ከማስወገድ ጋር ተያይዞ የሚታይ ነው፡፡ ይሄም ማለት በዚህኛው የስላም ስምምነት ማዕቀፍ የማይስተናገዱና ገና በሂደት መልስ የሚሹ አገራዊም ሆነ ክልዊ አጀንዳዎች መኖራቸውን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ሁላችንም ከሰላም ስምምነት ሰነዱ መገንዘብ እንደቻልነው፤በቀጣይ የሚኖሩት ጉዳዮች የሚስተናገዱት የኢፌድሪ ህገ-መንግስትን መሰረት አድርገው ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብቻ መኖርና ቲዲፍ የሚባልን ሕወሀት ሰራሽ ሰራዊት ትጥቅ ማስፈታ፤ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ የተካሄደን የትግራይ ምርጫ መሰረዝና አዲስ ጊዚያዊ አስተዳር መመስረት፤ የወሰንና ማንነት ውዝግብ ያለባቸውን አካባቢዎች መፍትሄ መስጠት፤ወዘተ…የሚሉት ጉዳዮች ህገ-መንግስቱን መሰረት ተደርጎ መፍትሄ እንደሚሰጣቸው ተመላክቷል፡፡ በዝች አጭር ጽሁፍ ለማንሳት የፈለግኩት አወዛጋቢ አካባዎችን መፍትሄ ለመስጠት ስለተቀመጠው መፍተሄ ነው፡፡

3. ስለ ወሰንና የማንነት ጥያቄዎች አፈታት የመፍትሄ ሃሳቦች!

በዚህ የሰላም ስምምነት መሰረት፤ ከወሰንና ማንንት ውዝግብ አንጻር የተቀመጠው መፍተሄ በዋነኛነት በአማራና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን ውዝግብ የተመለከተ ነው፡፡ ይሄም ማለት የወልቃይት- ጠገዴ፤ጠለምት፤ ራያ እና ኦፍላን የሚመለከት ይሆናል ፡፡ ከአማራ ክልል አንጻር እነዚህን አካባቢዎች በሁለት ግንባረ ከፍሎ መመልከት ይገባል፡፡ ግንባርር አንድ፡- ወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት ሲሆን፤ ግንባር ሁለት ደግሞ ራያ፤ኦፍላና አበርገሌን የሚያካትት ነው፡፡ የክልሉ መንግስትም ጉዳዩን በዚሁ አግባብ እያስኬደው ይመስለኛል፡፡

በሁለቱ ወገኖች የተፈረመው የስላም ስምምነት በአንቀጽ 10(4) ላይ በግልጽ እንደተመላከተው፤ አወዛጋቢ አካባቢዎች ሕገ-መንግስቱን መሰረት ተደርጎ መፍትሄ ይሰጣቸዋል የሚል ነው፡፡ እንዲህ ይነበባል፡- “The Parties commit to resolving issues of contested areas in accordance with the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia.”

እንግዲህ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ፤ በተለይም ለአማራና ትግራይ ህዝብ በተለይም ለሁለቱ ኢሊቶች ከባድ የቤት ስራ የሚሆነው ይሄንን የስምምነት ነጥብ አክበረውና መሰረት አድረገው የከረመውን የወሰንና ማንነት ውዝግብ መፍታት መቻል ነው፡፡ ከባድ የቤት ስራ፡፡ይህ የቤት ስራ ክልል፤ዞንና ወረዳ ላይ ቁጭ ተብሎ ውስኪና ቢራ እየጨለጡና ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሲነዙ በመዋል የሚሳካ አይደለም፤ ብዙ ድካምና ውጣ ውረድን ይጠይቃል፤ በተለይም የአዕምሮ ስራ፡፡ በተለይም ከአማራ አንጻር ይሄን የቤት ስራ በቅጡ መስራ አለመቻል፤ በተለይም በየደረጃው ያለውን አመራር ከባድ ዋጋ ያስከፍለዋል፡፡ ከምሬ ነው!

በዚህ በኩል በርካታ ወገኖች በተለይም የአማራ ኢሊቶች የወሰንና ማንት ውዝግቡ ሕገ-መንግስቱን መሰረት ተደርጎ ይፈታ የሚለውን አባበል ለመቀበል ሲቸገሩ እመለከታለሁ፡፡ የነዚህ ወገኖች መነሻ ወልቃይት- ጠገዴ፤ጠለምት፤ራያና ኦፍላ እንዲሁም አበርገሌ፤ ከ1983 ዓ.ም በፊት በሕወሀት በጉልበት(ወረራ) የተወሰዱ ስለሆነ ጉዳዩ መታየትና መፈታ ያለበት በፖለቲካ ነው ይላሉ፡፡ በአንጻሩ ሁሉም የትግራይ ኢሊት ደግሞ ህገ መንግስታዊ መፍትሄ የሚለውን አባበል በደስታ እንደሚቀበለው በተደጋገሚ ነግረውናል፡፡ በነገራችን ላይ ብልጽግና ፓርቲም እንደ ፓርቲ የዚሁ ሃሳብ ደጋፊ ነው፡፡

See also  የትግራይ "አባቶች "ና የአባ ማቲያስ ትህነግን ነጻ የማውጣት ፖለቲካ በጌታቸው ምላስ

በዚህ አጀንዳ ዙሪያ የግልህ ሃሳብ ምድን ነው ካላችሁኝ ደግሞ፤እኔ ውዝግቡ መፈታት ያለበት በህገ መንግስታዊ ማዕቀፍ ስር መሆን አለበት የሚለውን አርጉመንት ተቀብየ፤ መፍትሄው ህገ-መንግስታዊ ነው ስል ግን፤ የወያኔ ኢሊቶችና ብልጽግና ፓርቲ ከሚያስቡት የተለየ ነው፡፡ ምን አልባት በዚህ መፍትሄ ዙሪያ የአማራ ህዝብ በሙሉ፤እንዲሁም አብዛኛው የአማራ ብልጽግና አባልና አመራር እንዲሁም የክልሉ መንግስት የምንጋራው ሃሳብ ይመስለኛል፡፡

ለመሆኑ የወሰንና ማንነት ውዝግቡ በህገ መንግስታዊ ማዕቀፍ ይፈታ ስንል ምን ማለታችን ነው? ከህገ-መንግስቱና እሱን ተከትለው ከወጡት ህጎች መረዳት እንደሚቻለው፤የወሰንና ማንነት ውዝግቦች ባጋጠሙ ጊዜ ህገ-መንግስቱን መሰረት ያደረጉ ሁለት የመፍተሄ አማራጮች እንዳሉ ልብ ልንል ይገባል፡፡ እነሱም፡-

1. በፌደሬሽን ም/ቤት በቀጥታ በሚወሰን ውሳኔ የሚሰጥ መፍትሄ ( በተለምዶና በተሳሳተ መንገድ ፖለቲካዊ መፍትሄ የምንለው)፤

2. በህዝ ውሳኔ የሚሰጥ መፍተሄ ናቸው፡፡

የመጀመሪው መፍትሄ ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች፤ ለፌደሬሽን ም/ቤት ማስረጃቸውን አቅርበውና ተከራክረው ውሳኔ የሚሰጥበት ሂደት ሲሆንን፤ በዚህም የተሻለ ማስረጃ ማቅረብ የቻለ ወገን የውሳኔው አሸናፊ የሚሆን ይሆናል፡፡ ይህ አካሄድ በተለምዶ ፖለቲካዊ መፍትሄ እያልነው የመጣነው አሰራር ነው፡፡ ነገር ግን ፍጹም ስህተት ነው፡፡ ሂደቱ ህገ መንግስትን/ ህግን መሰረት አድርጎ የሚከወን ከመሆኑም በላይ፤ የሚተላፈው ውሳኔም ህጋዊ ስልጣን በተሰጠው አካል የሚሰጥ ውሳኔ ስለሆነ፤ውሳኔው ህገመንግስታዊ/ህጋዊ ነው፡፡

በእኔ እምነት ይህ የመፍትሄ ሃሰብ ተመራጭ ነው፡፡ ተከራካሪ ወገኖችንም ከብዙ ውዝግቦችና ወጭ ያድናል፡፡ ስለዚህ የአማራ ህዝብና ክልላዊ መንግስት በዚህኛው ህገ- መንግስታዊ መፍትሄ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ባይ ነኝ፡፡

ሁለተኛው የመፍትሄ አማራጭ በህዝበ ውሳኔ የሚቋጭ ነው፡፡ በእኔ እምነት ይሄኛው የመፍትሄ ሃሳብ በትግራይና አማራ ክልሎች መካል ለተነሳው የወሰንና ማንነት ውዝግብ ዘላቂና አዋጭ መፍትሄ ያመጣል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሲጀመር ይሄ መፍትሄ ይተግባር ቢባል፤እጅግ መወሳሰቡ አይቀርም፡፡ ለምሳሌ በሪፈረንደሙ ተሳታፊ የሚሆኑት እነማን ናቸው ? ከ1, 000 በላይ የወልቃይት ተዎላጆችን ጨፍጭፈው ወደ ትራይና ሱዳን የኮበለሉ ትግረዋይ ጉዳይ እንዴት ይስተናገዳል? በግጭቱ ምንም ተሳትፎና አበሳ ያልነበራቸው፤ ግን ደግሞ ስጋት አድሮባቸው ከወልቃይት-ጠገዴ የተፈናቀሉ ትግራዋይን ካሉ እንዴት ነው መለትና ወደ ቀያቸው መመለስ የሚቻለው? ላለፉት 30/40 አመታት በወያኔ የግፍ አገዛዝ ከቀያቸው የተፈናቀሉ እስከ 500, 000 የሚደርሱ የወልቃይት-ጠገዴ ተዎላጆች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል ወይ ? ካልተመለሱ እንዴት ነው እነሱ ያልተሳተፉበት ሪፈረንደም ተካሂዶ በቀተናው ዘላቂ ሰላም የሚሰፍነው?

ለዚህ ነው፤ የወሰንና ማንት ውዝግቦችን ለመፍታት ህዝበ ውሳኔን መሰረት ያደረገው ህገ-መንግስታዊ መፍትሄ አያዋጣም፤ውስብስብና አስቸጋሪም ነው የምለው፡፡ በተለይም ደግሞ የወልቃይትና ጠገዴ፤ጠለምት ተዎላጆቹ ወደ ቀያቸው ሳይመለሱ ህዝበ-ውሳኔ ተካሂዶ ውጤቱ፤ የተወላጆቹን ባለቤትነት የሚያሳጣ ከሆነ ዘላቂ ሰላም አያመጣም ( በዚህ በኩል የራያው ግንባር ብዙም ችግር ያለው ስላልመሰለኝ ነው)፡፡ ስለሆነም ይሄኛው ህገ-መንግስታዊ የመፍትሄ ሃሳብ ቢያንስ እንደ አማራ ክልል ተቀባይነት ባይኖረው እመክራለሁ፡፡ ይሄም ሆኖ የአማራ ክልል መንግስት በፌደሬሽን ም/ቤት አስገዳጅ ውሳኔ ወደ ሁለተኛው ህገ መንግስታዊ የመፍትሄ አማራጭ (ህዝበ ውሳኔ) የሚያመራ ከሆነ፤ ይሄኛውን ህገ-መንግስታዊ መፍትሄ ተቀብሎ ለመተግበር ከሁሉ በፊት ቢያንስ ለዘመናት ከቀያቸው የተፈናቀሉ (የወልቃይት- ጠገዴና የጠለምት ተዎላጆች) ወደ ቀያቸው መመለስ አለባቸው፡፡ ይሄ ቅድመ ሁነታ ባልተሟላበት ሁኔታ ሁለተኛውን ህገ-መንግስታዊ መፍትሄ መቀበል ትክክል ነው ብየ አላምንም፡፡

See also  ወግ አጥባቂው የኦክላሆማ ሴናትር ማ'ናቸው?

እንግዲህ እውነትም አማራነት ተላብሳችሁ፤የአማራ ጉዳይ በተለይም የወሰንና ማንነት ጥያቄዎች አመላስ ያሰጋናል፤በመንግስት ላይ እምነት የለንም የምንል አማራዊያን፤ ጊዜው ደርሷልና ፈረሱም እሄው ሜዳውም አሄው እንላን፡፡ የወልቃይት፡ጠገዴ፤ጠለምትና ራያ እንዲሁም ኦፍላ ጉዳይ የሚፈታው በህገ መንግስታዊ ማእቀፍ ብቻ መሆኑን አውቀን፤ለመፍትሄው በበጋር እንቁም፡፡ በማይሆን ነገር ጊዜን ማባከን እና የ “ብለን ነበር” ፖለቲካ በማራመድ ብቻ፤ ለአማራ ህዝብ አንዳች ጠብ የምትል ነገር አናመጣለትም፡፡ ይልቁንስ ባለን አቅም ሁሉ አስተዋጽኦ በማድረግ የወሰንና ማንነት ጥያቄዎች እውነተኛ የሖነውን የአማራን ጥቅም ባስከበረ መልኩ ምላሽ እንዲያገኙ እንረባረብ፡፡ በዚህ አጀንዳ ዙሪያ የመሳተፍ እውነተኛ ፍላጎት ያለው አማራ ሁሉ ጊዜው አሁን ነው፡፡

4. ሌሎች ጉዳዮች!

በስላም ስምምነት ሰነዱ አንቀጽ 10(4) ላይ የሰፈረው የወሰን ውዝግቦች ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ መፍትሄ ይሰጣቸዋል የሚለውን ሃሳብ ተከትሎ፤በአንቀጽ 7(2)(c) ሕወሀትን ከሽብርተኝነት ስያሜ ስለማስፋቅ የተደነገገው ድንፋጌ ”Facilitate the lifting of the terrorist designation of the TPLF by the House of Peoples’ Representatives” ፤ እንዲሁም በስላም ስምምነቱ ሰነድ አንቀጽ 10(1) ላይ ሁኔታዎች እስኪስተካሉና በትግራይ ህጋዊ ምርጫ ተካሂዶ ቋሚ የትግራይ ክልላዊ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ በትግራይ የጊዚያዊ አስተዳር እንደሚቋቋም የተቀመጡት ሃሳቦች ”Within a week of the implementation of Article 7 (2) (c) and until elections for the Regional Council and the House of Peoples’ Representatives are held under the supervision of the Ethiopian National Election Board, the establishment of an inclusive Interim Regional Administration will be settled through political dialogue between the Parties“ የሰላም ሂደቱን ወደ ምድር ለማውረድ በሚሞከርበት ጊዜ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ ብዙም ግልጽ አይደለም ባይ ነኝ፡፡

በእኔ እይታ የሰላም ስምምነቱ ወደ መሬት በሚወርድበት ጊዜ ለአፈጻጸም ከሚያስቸግሩ ምን አልባትም በተለይም ደግሞ በትገራይና አማራ ህዝብ ( ኢሊት) መካል መካረረን፤ በመንግስት ላይ ቅሬታ ማንሳትን( ተካድን)፤ ከፍ ሲልም ወደ መለስተኛ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉ ሃሳቦችን የያዙ ድንጋጌዎች ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ለምሳሌ፡-

1. የውዝግብ ቀጠና የሆኑትና በአማራ አስተዳር ስር የከረሙት የወልቃይት-ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ራያ፤ ኦፍላ ወረዳዎች አስተዳደር ጉዳይ እንዴት ነው የሚስተናገደው ?

2. በነዚህ አካባቢዎች ጊዚያዊ አስተዳር እንደ አዲስ የሚቋቋም ከሆነ ተጠሪነታቸው ለማን ነው የሚሆነው ?

3. አካባቢዎቹ በራሳቸው ነፃነታችንን አውጀናል ቢሉ፤ ዘለቄታዊ መፍትሄ እስኪሰጥ ድረስ እንዴት ይስተናገዳሉ?

ብቻ በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ መንግስት ያሰበው ነገር እንደሚኖር ብገምትም፤ ለጊዜው ግን ግልጽ ስላሆነልኝ ጥያቄዎቹን ለማንሳት ተገድጃለሁ፡፡ እነዚህን ለእኔ በሰላም ስምምነቱ አተገባበር ወቅት ስጋት የፈጠሩብኝን ነጥቦች በወጉ ማስተናገድ የሚችል የመፍተሄ ሃሳብ ካለ፤ የሰለም ስምነቱ በታሰበው አቅጣጫ የመተግበር እድሉ አሁንም ትልቅ ሁኖ ይታየኛል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች የሚፈቱበትን ስልት እስኪገባኝ ግን ነገሩ ሁሉ ናፍቆኛል፡፡

ሰላማችንን ያፅናልን!

ክብርና ሞገስ ለመከላከያ ሰራዊታችን!

Chuchu Alebachew FB

Leave a Reply