ናይሮቢ የአገር መከላከያ ሰራዊትና የትህነግ አማጺ ቡድን ወታደራዊ አመራሮች

የትጥቅ ማስፈታቱ ስራ በይፋ ተጀመረ፤ በቀናት ውስጥ ስብሰባው መቀለ ይደረጋል

በዋናው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት ትጥቅ የማስፈታቱንና ተመሳሳይ ተግባራትን ለማከናወን ናይሮቢ ለተገኙት ለኢትዮጵያና ለትህነግ ልዑካን አባላት ኦባሳንጆ “ለንግግር እዚህ መገኘታችሁ የስምምነቱ ተፈጻሚነት አዎንታዊ አቅጣጫ ላይ እንዳለ የሚያሳያ ነው ” ሲሉ ንግግሩ በታለመለት ግብ አማካይነት እየሄደ እንደሆነ እመልክተዋል።

በሰላም ስምምነቱ በአምስት ቀናት ውስጥ ወታደራዊ አመራሮች እንዲገናኙ የመልክቷል። ወታደራዊ ባለስልጣናቱም ወደ ናይሮቢ ያመሩት በዚሁ መሠረት ነው። ስምምነቱ ሁለቱ አካላት የሚሰበሰቡበትን ቀን የወሰነው “በአንድ አገር አንድ የመከላከያ ሰራዊት ብቻ ሊኖር ይገባል” በሚለው ገዢ መግባባት ላይ ተንተርሶ የትሀንግ ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን፣ ወደ መክለላከያ የሚጠቃለሉትን፣ ወደ መደበኛ ህይወታቸው የሚመለሱትን ለይቶ ወደ ተግባር ለመግባት ነው።

በፕሪቶሪያ የተጀመረውንና በውጤት የተጠናቀቀውን ንግግር በማንሳት አድናቆት የሰጡት የቀድሞ የኬንያ መሪ ኡሁሩ ኬንያታ “ዛሬ አንድ ስንዝር ተቃርበናል” ሲሉ ናይሮቢ የሚደረገውን ውይይት የአዲስ አበባ መገናኛ መንደርደሪያ እንደሚሆን አስታውቀዋል። የናይሮቢው ውይይት ሲጠናቀቅ በቀጣይ በመቀለ እንደሚሆን ትልቅ ተስፋ እንዳላቸውም አመልክተዋል። ኡሁሩ በንግግራቸው መቋጫው በአዲስ አበባ እንደሚከበር፣ የሁሉም ጸሎትናና ተስፋችን እንደሆነ በውይይቱ መጀመሪያ ላይ ኦባሳንጆን ተከትለው ተናግረዋል።

“ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ባሉት አምስት ቀናት የሁለቱ አካላት ከፍተኛ የጦር አመራሮች በአካል ተገናኝተው ትጥቅ የማስፈታት ሂደትን በተመለከተ ይነጋገራሉ” በሚለውና ” ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል” ሲል ስምምነቱ ባስቀመጠው መሰረት ከዛሬ ውይይት ሁለት ቀን በሁዋላ መከላከያ ወደ መቀለ የሚገባበት አግባብ ይመቻቻል ተብሎ ይጠበቃል።

“ቀደም ባሉት ጊዝያት ትሀንግ በትግራይ ሕዝብ ዘንዳ በህጋዊ ምርጫ የተመረጠ ድርጅት ነው” ሲሉ የነበሩ የትህነግ ልሳን ሚዲያዎች ዛሬ ለሰላም የተወሰደውን እርምጃ እየተቃወሙ ነው። ትህነግን በየትኛውም ደረጃ ይጠሉታል የሚብሉ አካላት እንኳን ባላደረጉት መልኩ በስድብና በክህደት እየወነጀሉ ያሉ የቀድሞ የድርጅቱ ልሳኖች ጥቅ መፍታቱን ቢቃወሙም ሰሚ ያገኙ አይምስልም።

ውጭ ሆነው የሰላም ሂደቱን እየተቃወሙን ካሉት በተቃራኒ በትግራይ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች፣ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፣ እንዲሁም መላው ዜጎች የተደረሰውን ሰላም እንደሚደግፉ የውጭና የአገር ውስጥ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።

See also  «የተጀመረው ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል» ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት

የመንግስት ሚዲያ እንዳለው ውይይቱ በመልካም ሁኔታ እየሂደ ነው። ከስምምነቱ በሁዋላ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ወታደራዊ ባለሙያዎች እንደሚመክሩ፣ በአምስት ቀን ውስጥ የትጥቅ ማስፈታቱን ሂደት እንደሚያከናውኑ፣ በአስር ቀን ውስጥ የከባድ መሳሪያ ማስፈታት እንደሚጀመርና በቀጣይ ሰላሳ ቀን ውስጥ ሁሉ ጉዳይ እንዲጠናቀቅ ነው ከስምምነት የተደረሰው። ከስር የትህነግን የሰላም አቋም በመቃወም ለመስማት በሚከብድ ሁኔታ ” አቋም መግለጫ” በሚል ትህነግ ላይ የተሰንዘረ ሰይፋ ነው

አሜሪካ የሰላም ሂደቱን በሚያውኩና በማይቀበሉት ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ማ

  1. ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤
  2. ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤
  3. የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤
  4. ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤
  5. በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤
  6. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።
  7. የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
  8. ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል።

የአፍሪካ ሕብረት መግለጫ‼

ሕብረቱ በኢፌዴሪ መንግሥትና በህወሓት ታጣቂ ወታደራዊ አዛዦች መካከል ስለሚካሄደው ንግግር ከናይሮቢ መግለጫ አውጥቷል። ውይይቱ ተጀምሯል። በመሆኑም የህወሓት ታጣቂ ትጥቅ ስለሚፈታበት፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ስለሚሳለጥበትና በትግራይ የተለያዩ አገልግሎቶችን ስለሚመለሱባቸው ሁኔታዎች ከውይይቱ ውጤት እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

See also  ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ለማጓጓዝ የሞከሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ገለፀ

Leave a Reply