ባለቤቱን ገድሎ ሊያመልጥ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በትላንትናው ዕለት ቱሉዲሚቱ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ከባለቤቱ ጋር በነበረው ግጭት ምክንያት ባለቤቱን ገድሎ ሊያመልጥ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽ እና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በረከት በቀለ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት፤ ግለሰቡ ከባለቤቱ ጋር በትዳር አብረው የቆዩና ኹለት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም የውጪ አገር ዜግነት ያለው መሆኑ ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ በንብረት ውርስ ክፍፍል ምክንያት በመካከላቸው ጸብ ተፈጥሮ የነበረ መሆኑን የገለጹት በረከት፤ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ፈፅሞ ሊያመልጥ ሲሞክር በቁጥጥር ሥር መዋሉንም ለሬዲዮ ጣቢያው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

See also  እነ ስብሃት ነጋና ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤት " የፍርድ ሂደት ለማጓትት ነው" ሲል ጣለው

Leave a Reply