ዐቃቤ ሕግ በእነ ሙሉ ሐጎስ ላይ አቅርቦት የነበረው ክስ በችሎት ተሰማ

በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ስማርት ሳምሰንግ ጋላክሲ ሞባይሎችን እና የሞባይል ቻርጀሮችን በህገ-ወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ በማስገባት የኮንትሮባንድ ወንጀል ፈፅመዋል ባላቸው ሙሉ ሐጎስ እና ክብሮም ገብረ-ሚካኤል የመሰረተው ክስ በችሎት ተነቧል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾች ቀርበው የተከሰሱበትን ክስ ካዳመጡ በኋላ የክስ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን ዐቃቤ ህግም በክስ መቃወሚያቸው ላይ መልስ ለመስጠት ለህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ተከሳሾች ተገቢውን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሳይፈፀምባቸው ወደ አገር ውስጥ የገቡ መሆናቸውን እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸው 1ኛ ተከሳሽ የዋጋ ግምታቸው 10 ሚሊዮን 847 ሺ ብር የሚያወጡ 715 ስማርት ሳምሰንግ ጋላክሲ ሞባይሎች እና 815 የሞባይል ቻርጀሮችን ከሞያሌ አጓጉዞ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በማስገባት በ2ኛ ተከሳሽ የመኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ በቤታቸው ውስጥ እና ግቢ ላይ ቆሞ በነበረ መኪና ንብረቶቹን አስቀምጠው የተያዙ በመሆኑ በፈፀሙት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የገባን ዕቃ ማጓጓዝና ይዞ መገኘት የኮንትሮባንድ ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተባቸው ከዚህ ቀደም ባጋራነው መረጃ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

የዚህን መዝገብ የክርክር ሂደት ተከታትለን መረጃ የምናጋራችሁ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Ministry of justice

See also  የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ 100 ጉቦ በመቀበላቸው ከስራ ተሰናበቱ

Leave a Reply