የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደህሚት አንዳንድ ቦታዎችን መያዙ ተሰማ

  • ትህዴን / ደህሚት መነሻው ኤርትራ ሲሆን በቅርቡ ዳግም ራሱን ማደራጀቱ ተሰምቶ ነበር

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሚለውና የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን በትጥቅ ትግል ሲታገል ቆይቶ ጥበመንጃውን ማውረዱን አስታውቆ ነበር። እ.አ.አ ድርጅቱ በጁን 2018 የትጥቅ ትግል ማቆሙን ከማስታወቁ በተጨማሪ የውቅቱ መሪው የነበሩት የተወሰኑ ወታደሮቹን በመያዝ ከኤርትራ በረሃ ወደ ትግራይ መግብታቸው ይታወሳል።

ድርጅቱ የተወሰኑ ወታደሮቹን ይዞ ወደ ትግራይ ከገባ በሁዋላ የተገባለት ቃል እንዳልተከበረለት ሲያስታውቅም እንደነበር ይታወሳል። በአንድ ወቅት ከግንቦት ሰባት ጋር ግንባር ገጥሞ የነበረውና ሰፊ ሃይል እንዳለው ሲነገርለት የነበረው ይህ ድርጅት ከወሬ ያለፈ ፋይዳ የለውም የሚሉ በርካታ ናቸው። አንዳንድ የትህነግ ቅርቦች “ወያኔ ኢሳያስ ውስጥ የወሸቀውና ለስታራቴጂ ሲባል ተቃዋሚ የሆነ ድርጅት ነው። የእኛው ነው” በማለት ልጥፍ ድርጅት እንደሆነም ሲገልጹት ቆይተዋል።

ስለድርጅቱ ጠንቀቀው እንደሚያውቁ የሚገልጹ ወታደር ቀመስ ሆነው በስደት አውሮፓ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ደግሞ ” የደህሚት ሃይል የኢሳያስ ጠባቂዎች ናቸው አማራዎችም አሉበት” በሚል ከላይ የትህነግ ሰዎች የሚሉትን ሲያጣጥሉ መስማት የተለመደ ነው።

መስከረም 2 ቀን 2008 ዓ.ም ፋና እንደዘገበው ራሱን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደህሚት/ በማለት የሚጠራው እና በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጦር ክፋይ ወደ አዲስ አበባ መግባቱን አስታውቆ ነበር። ጦሩ የንቅናቄው መሪ በሆነው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱንና አስከትሎ የመታው ሃይልም ከ700 በላይ እንደሚሆኑ ግምቱን አስቀምጦ ነበር።

የተገመተው የደህሚት ጦር ከነ ሙሉ ትጥቁ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በሁመራና በመተማ አድርጎ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መምጣቱን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያስታወቀው ምንጮች እንደነገሩት አስታውቆ ነው። ሞላ አስገዶም አስከትሎት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሃይል ከሻዕቢያ የተሞከረበትን ውጊያ እየመከተ ወደ አገሩ ምድር መግባቱንም ከለውጡ በፊት በነበረው የመንግስት አቋም የተቃኘ ዘገባ ቢቀርብም ይህ ሃይል በቀጣይ ምን ሲያከናውን እንደነበር ወሬ አልነበረም።

ኢትዮ 12 በደረሰው መረጃ መሰረት ይህ ሃይል ላለፉት ሁለት ዓመታት በትግራይና አጎራባች ክልሎች ተከስቶ በነበረው ጦርነት ስር ሆኖ ጡንቻውን አፈርጥሟል። አሁን ላይ በዝርዝር የማይገልጽ ጥምረትም መፍጠሩ ተመልክቷል። በአዲስ አመራርና አደረጃጀት የተቀኘ መሆኑ የተነገረለት ደህሚት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎችን መቆጣጠሩም ተሰምቷል።

ከየትኞቹ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ጥምረት እንደፈጠረ ሳይገልጹ በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ድርጅቱ በሚታወቁና በተገፉ የስፍራው ተወላጆች አማካይነት ደርጅታዊ ሴሉን እየዘረጋ መሆኑን አመልክተዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰፊ ሃይል መሰብሰቡን በመግለጽ ትህነግ የፈረመውን የሰላም ስምምነት ገፍቶበት ወደ ምርጫ የሚሄድ ከሆነ በሰላማዊ መንገድ ምርጫ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን፣ ምርጫ የማይደረግና ትህነግ በጦርነት የሚገፋ ከሆነም ድርጅቱ አጋጣሚውን ለመጠቀም መዘጋጀቱን መረጃውን ያካፈሉን አመልክተዋል።

እንቅስቃሴው ሰፊና ጥንቃቄ የተሞላበት በመሆኑና ድርጅቱ ለትግራይ ህዝብ ብቁ አማራጭ ሆኖ ለመቅርብ እየተዘጋጀ በመሆኑ ዝርዝር ከመናገር የተቆጠቡት የዜናው ክፍሎች ” ሁሉም ጉዳይ የሰላም ሂደቱን ውጤት ተከትሎ ይፋ ይሆናል” ብለዋል። ይህን ዜና አስመልክተን በኦፊሳል ሳይሆን በተዘዋዋሪ ያነጋገርናቸው የትህነግ ደጋፊዎች ” ፍጹም የማይሆን፣ እነ ሊላይ የሚሞክሩት ነገር አለ ይታወቃል” በሚል አታጥለውታል። አቶ ሊላይ የፓርቲያቸውን አቋምና አሁን ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ በትውልድ አካባቢያቸው እንደርታና ዙሪያዋ ( በትህነግ የተገፋና መሬቱን የተዘረፈ ህዝብ ይሉታል) የማደራጀቱን ስራ እየሰሩ መሆናቸውንና ሲሳካላቸው የመለስ ዜናዊን ሃውልት በማፍረስ “ልጃችን” ያሉዋቸውን የአጼ ዮሐንስን ሃውልት በምትኩ እንደሚያቆሙ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን ደህሚት) አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸውን፣ የገቡትም ለውጡን በመደገፍ እንደሆነ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሆኑንን ጸሃፊው አቶ ግደይ አሰፋ ሊትዮጵያ ቴሌቪዥን በመስከረም 12 ቀን 2018 ሲናገሩ ተደምጠው ነበር። እሳቸውም ሆኑ ሌሎቹ አመራሮች አሁን ላይ ከድርጅቱ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ዜናውን ያስታወቁን አላብራሩም።

You may also like...

Leave a Reply