ለጀግናው ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ሃውልት…

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት መገባደድን ተከትሎ የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግስታት በከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ጦራቸውን እንዲቀላቀል ሲጠይቁት እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት ከበርካታ ጥቅማጥቅም ጋር የቀረበለትን የዜግነት ጥያቄ ሳይቀበል ቀርቷል።

በአዲስ አበባ በሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ስም የተሰየመው ትምህርት ቤት ለጀግናው ክብር እና ስም በሚመጥን መልኩ ታድሶ ተመረቀ

በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ የተገነባው የጀግናው የሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ሃውልትም ተመርቋል።

ገና በ14 አመቱ የኢትዮጵያን ጦር የተቀላቀለው ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ጣልያን ኢትዮጲያን በወረረችበት ጊዜ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ በጠላት እጅ ወድቆ አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት ውስጥ የቁም እስረኛ ተደርጎ ግፍን ተቀብሏል።

ወደ ጣልያን ሲሲሊ ተወስዶ የጦር እስረኛ ቢደረግም አብዲሳ መሸነፍን አይወድምና በልዩ ጥበብ ከእስር ቤት በማምለጥና ሌሎች እስረኞችንም ነጻ በማውጣት የኢትዮጵያውያንን ጀግንነት በዓለም አደባባይ አስመስክሯል።

ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት መገባደድን ተከትሎ የእንግሊዝ፣ የካናዳ እና የአሜሪካ መንግስታት በከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ጦራቸውን እንዲቀላቀል ሲጠይቁት እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት ከበርካታ ጥቅማጥቅም ጋር የቀረበለትን የዜግነት ጥያቄ ሳይቀበል ቀርቷል።

አዲስ አበባ የሃገርን ክብር በዓለም አደባባይ ላስመሰከረው የኢትዮጵያዊያንን ጀግንነት ከፍ አድርጎ ለዘመረው አይረሴ ጀግና ለስሙ መጠሪያ ለሃገር ፍቅሩ መገለጫ ይሆን ዘንድ ትምህርት ቤት ሰይማለታለች ሃውልትም ቀርፃ በክብር አቁማለታለች።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አደነች አቤቤ ትምህርት ቤቱን መርቀው ከፍተዋል።

በመርሃግብሩ ላይ የኮሎኔል አብዲሳ አጋን ቤተሰቦች ጨምሮ አባት አርበኞች እና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በካሳሁን አንዱዓለም

See also  በአባቷ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለጓደኛዉ የታገቢኛለሽ ወይ? ጥያቄ ያቀረበዉ ግለሰብ አነጋጋሪ ሆኗል

Leave a Reply