ሳውዲ አረቢያ አርጀንቲናን በመርታቷ ህዝባዊ በአል አወጀች !!

የሳውዲው ንጉሥ ሰልማን ብሔራዊ ቡድናቸው ሃያሏን የእግር ኳስ አገር አርጀንቲናን 2 ለ 1 መርታቷን ምክንያት አድርገው የነገው ዕለት የዕረፍት ቀን እንዲሆን አወጁ።

ሳውዲ አረቢያ አርጀንቲና ላይ የተቀዳጀቸውን ድል ተከትሎ የነገው ቀን በሀገሪቱ ህዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር መወሰኑ የተገለጸ ሲሆን ንጉስ ሰልማን የነገው ቀን በሀገሪቱ የበዓል ቀን ሆኖ እንዲውል ከልዑል መሀመድ ቢን ሰልማን የቀረበላቸውን ጥያቄ ማፅደቃቸው ታውቋል።

በሀገሪቱ ያሉ ተማሪዎች እንዲሁም የመንግስት እና የግል ሰራተኞች የነገውን ቀን በልዩ በዓልነት በመላው ሳውዲ አረቢያ እንደሚያከብሩ ታውቋል።

ቦጋለ አበበ

ሜሲ ከአስደንጋጩ ሽንፈት በኋላ….

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ አገሩ በአለም ዋንጫ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በሳውዲ አረቢያ የገጠማትን የ2ለ1 ሽንፈት ተከትሎ አስተያየቱን በትዊተር ገጹ አስፍሯል።

ከግማሽ ደርዘን በላይ የባሎን ድ ኦረሰ ሽልማቶችን ጠራርጎ የወሰደው ጥበበኛ አገሩን በአምበልነት እየመራ በገጠመው አስደንጋጭ ሽንፈት የሚሰጠውን አስተያየት የአለም ሕዝብ በጉጉት ሲጠብቀው ቆይቷል።

ሜሲ ካልተጠበቀው ሽንፈት በኋላ

“ምንም ምክንያት ማብዛት አያስፈልግም ።ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንድነታችንን እንቀጥላለን፣ይህ ቡድን ጠንካራ ነው እና ከዚህ በፊት አሳይተናል። በዚህ መንገድ እንጀምራለን ብለን አልጠበቅንም ነገር ግን ነገሮች የሚከሰቱት በምክንያት ነው። አሁን ከማሸነፍ ውጪ ሌላ አማራጭ አይኖርም ሁሉም ነገር በእኛ ላይ የተመሰረተ ነው፣ ደጋፊዎች እንዲያምኑን እጠይቃለሁ… ይህ ቡድን አያሳፍራቸውም።” ብሏል።

በቦጋለ አበበ – (ኢ.ፕ.ድ)

See also  ጆ ባይደን ፑቲን በጦር ወንጀለኝነት እንዲከሰሱ ጠየቁ

Leave a Reply