ፊቤላ ፋብሪካ “ማምረት አቁሟል” የተባለው ውሸት ነው!

ፊቤላ ከነገ ጀምሮ በ8ተኛ ዙር ከ12.5 ሚሊዮን ሊትር በላይ  የፖልም፣ እንዲሁም 7.5 ሚሊዮን ሊትር የሱፍ ምግብ ዘይት  ለተጠቃሚዎች ማሠራጨት ይጀምራል። ይሁንና ደንበኞች የተሠጣቸውን ኮታ በትራንስፖርትና በሌሎች ምክንያቶች  በወቅቱ ካለማንሣት ጋር በተያየዘ “ፊቤላ ምርት አቁሟል” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ትክክል ያልሆነና ፋብሪካው በየእለቱ የሚያከናውነውን የስራ እንቅስቃሴ የማይገልፅ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ደንበኞች ኮታቸውን ፈጥነው ያለማንሣት በፊቤላ የምርት እንቅስቃሴ ላይ የፈጠረው መስተጓጎል የለም። መንግስት በተመጣጣኝ ዋጋ በሊትር ከ95 እስከ 100 ብር ድረስ ለዜጎች እንዳዲደርስ በተመነው ዋጋ መሠረት ከነገ ጀምሮ 20 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ማከፋፈል ይጀምራል።  የፋብሪካውን  ስራ አስፈጻሚ ሀሣብ ባልተገባ መንገድ በመተርጎም የቀረበው ሀሣብ ፊቤላን የማይገልፅ መሆኑን በድጋሜ ለመግለጽ እንወዳለን ።

በላይነህ ክንዴ ግሩፕ

See also  የትህነግ ተዋጊዎች ማገገሚያ ሙሉ በሙሉ ወደመ፤ ትህነግ "አልተሳካም" ብሏል

Leave a Reply