የወንዶች የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ይፋ ተደረገ

የአሜሪካ ተመራማሪዎች የወንዶች የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ይፋ አደረጉ፡፡

ወንዶች ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ከፈለጉ ኮንዶም መጠቀም ወይም በህክምና ሙያተኞች የታገዘ ቀዶ ህክምና ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የተለመደው ግን ሴቶች የተለያዩ የወሊድ መቆጣጠርያዎችን መውሰዳቸው ነው፡፡

በቅርቡ ይፋ በተደረገ ጥናት ወሊድን ለመቆጣጠር ከሴቶችም በተጨማሪ ወንዶች ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚያስችላቸው መድሃኒት ተገኝቷል፡፡ ጥናቱን ያካሄዱት በአሜሪካ የሰሜን ካሮሊና ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ናቸው፡፡

በጥናቱ ይፋ የተደረገው አማራጭ የወንዶች የወሊድ መቆጣጠርያ ‹‹ኢፒ- 055›› ይባላል፡፡ ወሊድን ለመቆጣጠር ወንዶች የሚወስዱት እንክብል ነው፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንዶችን የዘር ፍሬ ፍጥነት በማዘግየት ጽንስ እንዳይፈጠር የሚያደርግ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በሰዎች ላይ እስካሁን ባይሞከርም በዝንጀሮዎች ላይ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ታውቋል:: መድኃኒቱ ምንም አይነት የጎንዩሽ ጉዳት እንደማያስከትል ተረጋግጧል፡፡ በሰዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ተጨማሪ ምርምሮች እየተደረጉ ነው፡፡

ምንጭ፡- ሳይንስ ኒውስ (አብመድ) በሀይሉ ማሞ

See also  ከ “አበቃ አከተመላቸው” በኋላ …

Leave a Reply