በጥናት የተረጋገጡ 10 ሰምተው ያማያውቋቸው የፕላኔታችን ምርጡ መጠጥ የአርንጓዴ ሻይ ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች

  1. አረንጓዴ ሻይ ካቲቺንስ (Catechins) በተሰኘ ንጥረ ነገር በእጅጉ በመበልፀጉ የተነሳ በዓለም ላይ ካሉት ሕፀዋት ጋር ሲነፃጸር ከፍተኛ የመድኃኒት ይዘት ያለው በመሆኑ የሴል (ሕዋስ) ሞትን በመከላከል ሰዎች በካንሰር እንዳይጠቁ ጋሻ ሆኖ ይከላከላል፡፡
  2. አረንጓዴ ሻይ የአእምሮ የዕለት ተግባር በተሻለ ብቃት እንዲወጣት ያግዛል እንዲሁም ፈጣን ያደርጎታል፡፡ አረንጓዴ ሻይ አእምሮዎትን ከማንቃት (Awake) ከማድረግ በላይ ፈጣን (Smarter) ያድርጎታል፡፡ ከቡና ጋር ሲነፃጸር አረንጓዴ ሻይ አነስተኛ ካፊን ያለው ቢሆንም የያዘው አሚኖአሲድ ኤል-ቲያኒን ከካፊን በተሻለ የአእምሮ ንቃትና ቅልጥፍናን በእጥፉ ይጨምራል፡፡
  3. አረንጓዴ ሻይ የስብን መቃጠል በመጨመር የአካል ብቃትን ያሻሽላል፡፡ ለዚህ እማኝ የሚሆኑት በየትኛውም ስብን የማቃጠል ይዘት ባላቸው ምግብዎች ውስጥ የአንጓዴ ሻይ ነጥረገሮች በውስጡ መያዛቸው ነው፡፡
  4. አረንጓዴ ሻይ ፀረ- ወክሳጅ ባህሪ ስላለው በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ቆሻሻዎችና መርዛማ ነገሮችን በማስወገድ በአንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች እንዳንጠቃ ይከላከላል ለምሳሌ የጡት፣ የፕሮስቴትና የኮሌሬክታል ካንሰሮች ይጠቀሳሉ፡፡
  5. አረንጓዴ ሻይ በእርጅና ጊዜ የሚከሰቱትን የመርሳትና የፓርኪንሰን በሽታዎች እንዳይዙን የአእምሮአችንን ጤና ይጠብቃል፡፡
  6. አረንጓዴ ሻይ በአፋችን ውስጥ የሚገኘውን አደገኛ ባክቴሪያ ስትሬፕቶከክስ ሙታንስ በመግደል የጥርሳችንን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር መጥፎ የአፍ ጠረንንና የድድ መድማትን ይከላከላል፡፡
  7. በሁለተኛ ዓይነት የስኳር ሕመም እንዳንያዝ ይረዳናል፡፡ በሕመሙ ለተያዙ ሰዎችም የስኳር መጠናቸውን በአስገራሚ ሁኔታ በመቀነስ ጤናቸው እንዲጠበቅ በማድረግ ተመራጭ መጠጥ ሆኗል፡፡
  8. በልብ በሽታ የመጠቃት አደጋን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡ በአመጋገብና በተለያዩ ችግሮች በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረውን የደም ቅባት ወይም ኮሌስትሮል መጠንን በእጅጉ በመቀነስ ዓለማችንን በስጋት ላይ የጣለውና በገዳይነቱ አቻ ላአጣው የልብ በሽታ ታላቅ መፍትሔ ሆኗል፡፡
  9. አረንጓዴ ሻይ ሌላው ትልቁ ጥቅሙ የሰውነታችንን ክብደት መቀነስ መቻሉ ነው፡፡ በተለይ በሆዳችን አካባቢ ያለውን ስብ በማቃጠል ስኳርን ጨምሮ ለተለያዩ በሽታዎች እንዳንጋለጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመስክሮለታል፡፡ በተለይ ያለልክ ለወፈሩ ሰዎች ፍትሁን መድኃኒት ሆኗል፡፡
  10. ረጅም ዕድሜ ለመኖር አረንጓዴ ሻይ ዛሬ ዛሬ ተፈላጊነቱ ጨምሯል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሰውን ልጅ ዕድሜ የሚያሳጥሩ በሽታዎችን በመካላከል የተፈጥሮ በበሽታ የመከላከል አቅማችን ከየትኛውም የሕፀዋት ውጤት በተሻለ በመጨመሩ (Boost) በማድረጉ ነው፡፡
information_science_and_technology

Leave a Reply