ፖሊስ አፋልጉኝ ሲል የሚጠረጥራቸውን ተፈላጊዎች ፎቶ በተነ፤ ሕዝብ ተባበር

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ያሉበትን የሚያውቅ መረጃ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ፖሊስ ጥሪ አቀረበ


መንግስት ለጀመረው የፀረ-ሙስና ትግል ስኬታማነት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አስተላለፈ።

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ መሰረት፥

1ኛ ሀቢባ ኡመር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ
2ኛ ተስፋዬ ግርማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ
3ኛ በቃሉ ፀደቀ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር ባለሙያ
4ኛ ጭምዴሳ ፉለአ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ባለሙያ እንዲሁም
5ኛ ልኡል ተረፈ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው እየሰሩ በነበረበት ወቅት ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው የመንግስት እና የህዝብ መሬት እንዲመዘበር በማድረጋቸው በተጠረጠሩበት ወንጀል በህግ ይፈለጋሉ።

እነዚህ ግለሰቦች ያሉበትን የሚያውቅ ወይም መረጃ ያለው ማንኛውም ግለሰብ በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም አዲስ አበባ ፖሊስ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 991፣ 0111110111 እና 0111568311 መረጃ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል።

See also  የእነ መስከረም አበራ መዝገብ ወደ ሽብር ክስ ተቀየረ፤ ጠበቃ መቃወሚያ አቅርቧል

Leave a Reply