በኦሮሚያ ክልል ለውጡን ተከትሎ በተወሰዱ የጽንፈኛነት ተግባራቶች ሳቢያ ተግባራዊ የኢንቨስትመንት ፍላጎት መቀነሱ፣ በተቃራኒው አልማራ ክልል ላይ አልሚዎች መብዛታቸው ተሰማ። አማራ ክልል የሚቀርበው የኢንቨስትመንት ጥያቄና ተግባራዊ እንቅስቃሴው ግን ችግር አለበት ተብሏል። አየር በአየር ንግዱ ጦፏል።

ቀደም ሲል በኦሮሚያ በከፍተኛ ደረጃ የኢንቨስትመንት ጥያቄና ተግባራዊ ምላሽ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ አልሚዎች ከስጋት የተነሳ ፊታቸውን ወደ አማራ ክልል ማምራታቸው ነው የተሰማው። ዜናውን በዳታና መረጃ ለማስደገፍ ገና መሆኑንን የሚናገሩ እንዳሉት እነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ይህን ጉዳይ ሊያስቡበት ይገባል። እያደር ክልሉ ላይ ጫና ማድረሱ አይቀርም።

በርካቶች ከስጋት በመነጨ በኦሮሚያ ኢንቨትመንታቸው ደስታ እንደማይሰማቸው የሚገልጹ እንዳሉት ይህ ስሜት ግን በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚታይ እንዳልሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉ ገልጸዋል። መንግስትና አብዛኛው ኦሮሞ ” ዓላማው አልገባንም፣ ምን እንደሚፈልግ አይታወቅም፣ አመራሩም ገሃድ አይደለም” የሚሉት ሸኔ እየፈጸመ ያለው ድርጊት ለስጋቱ ምንጭ ሲሆን፣ አሁን አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይህ ሃይል በብልጽግና ኦሮሚያ ውስጥም ድጋፍና ከለላ አለው። በዚሁ መነሻ በርካታ ባለሃብቶች ከስጋታቸው ብዛት ማስተካከያ ካልተደረገ ምን አልባትም በሂደት ስጋት ካለባቸው የክልሉ አካባቢዎች ሊለቁ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ የዞን አመራር ቸግሩ ይህን ያህል እንደሚወራው ባይሆንም ስጋት መኖሩን አመልክተው፣ በቅርቡ በክልሉ የማጽዳት ማዕበል እንደሚኖር ጥቆማ ሰጥተዋል።

በሌላ ዜና ከ103 በላይ ባለሀብትች በቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግ ስምምነታቸውን እንዳሳዩ የአማራ ክልል ማስ ሚዲያ ይፋ አድርጓል። መንግስትም ሆነ ክልሎች ለአግሮ ኢንደስትሪ ዘርፉ ልዩ ድጋፍ እንደሚሰጥ ይፋ ማድረጉንና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ቤት ለመተካት በያዘው ዕቅድ መነሻነት ክልሉ በአንድ ጀንበር ይህን ያህል ባለሃብቶች ማግኘቱ ትልቅ ዜና ሆኗል።

ባለሀብቶችን ግንባታው ሙሉ በሙሉ ወደተጠናቀቀው ቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማስገባት ዓላማ ያደረገ የኢንቨስትመንት ፎረም በባህዳር መካሄዱን ተከትሎ ይፋ የሆነው ዜና አነቃቂ ከመሆኑም በላይ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የትገፋው ክልል በዚህ ደረጃ በቅርብ ዓመታት ከለውጡ በሁዋላ መነቃቃቱ ይበል የሚያሰኝ መሆኑም እየገለጸ ነው።

የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ በርካታ ባለስልታናትና አልሚዎች የተባሉ በተገኙበት በዚህ መድረክ ባለሀብቶች ከኃይል አቅርቦት፣ ከሲሚንቶና ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጋር ጥያቄዎች አንስተው በሚመለከታቸው ክፍሎች ምላሽና ማብራሪያ አግኝተዋል።በተለይ ከኃይል አቅርቦት ጋር ለተነሣው ጥያቄ ከፌደራል መብራት ኃይል የመጡ ኃላፊ ለሰብስቴሽን ግንባታ በጀት ተመድቦ፣ጨረታ ተለይቶ ፣ የግንባታ ማቴሪያሎች ወደብ የደረሱ ስለሆነ ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ግንባታው ተጠናቆ በቂ ኃይል እንደሚቀርብ ዋስትና ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ወደ ፓርኩ ገብተው ለማልማት ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶች ፍላጎታቸውን እንዲገልፁ በቀረበው ጥያቄ መሠረት ከ103 በለይ ባለሀብቶች ፍላጎት እንዳላቸው በቃል ኪዳን ፎርሙ አረጋግጠው መድረኩ ግቡን ባሣካ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ሚዲያ አመልክቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል ሰፋፊና ግዙፍ ፋብሪካዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውና መመረቃቸው የሚገልጹ ዜናዎች በተደጋጋሚ መሰማታቸው የሚታወስ ነው። በዚሁ መጠን ደግሞ ቀደም ሲል ኦሮሚያ ክልል ይደረግ እንደነበረው በጨበጣ መሬት እየወሰዱ መነገድ አማራ ክልል ላይ በስፋት እየታየ ነው። ዘርዝሩን በሪፖርት እንመለስበታለን።

Leave a Reply