የግል ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ፈቃድ ሊመረመር ነው

የትምህርት እና ሰልጠና ባለሥልጣን በኢትዮጵያ ከ360 በላይ የግል ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ፈቃድ ተሰጥቷቸው እንደሚንቀሳቀሱ ገልጿል፡፡

በዘርፉ የሚታዩ በርካታ ጉድለቶች መኖራቸውን መነሻ በማድረግ እነዚህ ተቋማት እንዴት ፈቃድ እንዳገኙ አጣራለሁ ብሏል፡፡ የትምሕርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ይህን ያለው ዋና ዳይሬክተሩ አምባሳድር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የትምህርት ዘርፍ የሩብ ዓመት ግምገማ ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡

ዳይሬክተሩ በማብራሪያቸው፣ የግል ከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ላይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንደሚታዩ እና ከመስመር የወጡ አካሄዶችን ሥርዓት ማስያዝ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ተቋማቱ ላይ ታይተዋል ከተባሉ ችግሮች መካከልም ለድግሪ ሰርተፍኬት የሚያበቃ ት/ት ላልወሰዱ ሰዎች ደግሪ ከመስጠት ጀምሮ ሀሰተኛ ድግሪ እስከ መሸጥ የደረሰ ውስብስብ ችግር እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

ባለ ሥልጣኑ ይሄን ሥራ ለማጠናቀቅ ለነባርና እና ለአዲስ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማንኛውንም ዓይነት አዲስ ፈቃድ መስጠት ከህዳር 30/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጫለሁ ብሏል፡፡

አዲስ ማለዳ

See also  በተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ የማታለል ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ዋሉ

Leave a Reply