ስብሐት ነጋ የፌደራል ፖሊስን ከሰሱ፤ “ለስብሃትም የምትሆን ኢትዮጵያ እየተሰራች ነው”

“አቶ ስብሐት ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል  በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለሁ” ሲሉ ለፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ክሱን ያቀረቡት  በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት ነው። ክሱን የሰሙ የስብሃት ነጻ ሰው ሆኖ መንግስትን ለመክሰስ መብቃት ለሳቸውም የምትሆን ኢትዮጵያ እየተሰራች ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ አመልክተዋል። ስብሃት ነጋ በምህረት ተለቀቁ እንጂ ክሳቸው ሙሉ በሙሉ አለመነሳቱ ይታወሳል።

አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል።

በዚህ በቀረበ ክስ ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረዝ መልኩ ፍርድ ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉና አቶ ስብሐትን ከኤርፖርት እንዲመለሱ ማድረጉ የህግ አግባብ የሌለው ነው ሲል  ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ አቅርቧል።

የአቶ ስብሐት ነጋ ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ ፖሊስ መልስ ባለማቅረቡ ምክንያት መልስ የመስጠት መብቱ እንዲታለፍ ብይን ሰቷል። በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለፊታችን ሮቡ ህዳር 28 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በትግራይ ክልል ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ በፌደራል መንግሥቱ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩት የህወሓት  አመራሮች ማለትም የድርጅቱ መስራች የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ እና እህታቸው ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እና አቶ ኪሮስ ሐጎስ በምህረት እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ከስር መፈታታቸው ይታወሳል። ሲል ታሪኩ አዱኛ ይዘገባው ዜና ያስረዳል።

የአቶ ስብሃትን የክስ ዜና የሰሙ ” ኢትዮጵያ እንደ ስብሃት ነጋ ላሉትም የምትሆን አገር ሆና መሰራቷ ማሳያ ነው” ሲሉ በዜናው መገረማቸውን አመልክተዋል። በሽብር ወንጀልና በአገር ክህደት ከተመደበው ትህነግ አብራክ የወጡት አቶ ስብሃት ሰሜን ዕዝ ሲታረድ መቀለ ነበሩ። በጦርነቱ ላይ ያላቸው ሚና ግልጽ ባይነገርም “ህገመንግስቱን መልሰን እናቆማለን” ሲሉ መንግስት የመቀየር አቅጣጫ ሲሰጡና “የፊደራል ሃይሎች” በሚል ትህነግ ያቋቋመው ቡድን ምስረታውን ሲያጠናቅቅ በነበረው ፌሽታ ላይ ሲያሸበሽቡና ደስታቸውን ሲገልጹ ነበሩ። እሳቸው የመሰረቱት ትህነግ መንግስት በነበረበት ወቅት በፕሮግራም ነድፎ ሲፈጽምና እሳቸውም ሲያስፈጽሙ ከነበረው ጋር ተዳምሮ ህዝብ በእሳቸው ላይ ጥላቻ እንደነበረበት የሚታወስም ነው። ሁሉም አልፎ እሳቸው በምርኮ በቃሬዛ ሸክምና በመከላከያ ድጋፍ አዲስ አበባ የገቡት ስብሃት ክስል ለመስረት መብቃታቸው ምንም ይሁን ምን ዴሞክራሲን ለሚያፈቅሩ ሁሉ ታላቅ ዜና መሆኑ ተሰምቷል።

See also  Tigray rebels tortured and killed civilians in renewed fighting, survivors claim

Leave a Reply