ከኮንደሚኒዬም ቤቶች ዕጣ ማጭበርበር ክስ በቀረበባቸው ላይ ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማሰማት ጀመረ

በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ከኮንደሚኒዬም ቤቶች ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ ክስ ባቀረበባቸው 11 ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ማሰማት ተጀመረ፡፡

በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ላይ ከኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ ማጭበርበር ወንጀል ጋር ተያይዞ ክስ ከቀረበባቸው 11 ተከሳሾች መካከል 1ኛ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ፣ 2ኛ አቶ አብርሃም ሰርሜሎ፣ 3ኛ አቶ ኩምሳ ቶላ፣ 4ኛ አቶ መብራቱ ኪ/ማርያም፣ 5ኛ አቶ ስጦታው ግዛቸው፣ 6ኛ አቶ ባዩልኝ ረታ፣ 7ኛ አቶ ሚኪያስ ቶሌራ፣ 8ኛ አቶ አሚ አምባዬ፣ 9ኛ አቶ ዮናስ ወ/ጊዮርጊስ የተባሉት 9 ተከሳሾች ከማረሚያ ቤት በችሎት የተገኙ ሲሆን፣ የተቀሩት ፍርድ ቤት ባልቀረቡት 2 ተከሳሾች ማለትም 10ኛአቶ ዘካርያስ አየለ እና 11ኛ ወ/ሮ ኤደን ካሳሁን በአድራሻቸው ተፈልገው ያልተገኙ በመሆኑና እንዲቀርቡ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሂደቱን ጠብቀው ስላልቀረቡ በችሎቱ ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 3ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት የወሰነ ሲሆን፣ ዐቃቤ ህግም ምስክሮችን አቅርቦ ማሰማት ጀምሯል፡፡

ሀምሌ 01 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶች እድለኞችን በፍትሃዊ የሎተሪ እጣ በሲስተም ለመለየት ተብሎ ከወጣው የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የወጣበትን ሲስተምን የማልማት፣ እጣ የማውጣት እና የኮንደሚኒየም ቤት የቁጠባ ተመዝጋቢዎችን የዳታ ቅብብሎሽ ሂደትን በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት ሊከላከሉት፣ ሊጠብቁት እና የጥራት ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለውጤት ማብቃት ሲገባቸው ከግለሰቦች ጋር በጥቅም በመመሳጠር የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ ስልጣናቸውን ወይም ሃላፊነታቸውን ተጠቅመው ያልቆጠቡት በዕጣው እንዲካተቱ አድርገዋል ተብለው በ11 ተከሳሾች ላይ የእያንዳንዳቸው የተሳትፎ ደረጃ ተጠቅሶ በዓቃቢ ሕግ ሶስት ክሶች ቀርቦባቸው ተከሳሾች በተከሰሱበት ክስ ላይ ከህዳር 21 እስከ ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን ለመስማት እና ፍርድ ቤት ባልቀረቡት 10ኛ እና 11ኛ ተከሳሽ ላይ በጋዜጣ ጥሪ እንዲተላለፍላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

See also  በአዲስ አበባና ሸገር ከተማ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ

ይህ ዜና የክርክር ሂደትን ለመሳወቅ የቀረበ ሲሆን ተከሳሾች ከፍርድ በፊት እንደ ንጹህ የመገመት መብት መርህን ያከብራል።

Leave a Reply