የብልጽግና ማዕ/ኮ መምከር መጀመሩ ተሰማ

ገዢው ፓርቲ ብልጽግና አራት ቀን እንደሚፈጅ የተነገረለትን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጀመረ። ይህ ስብስባ መንግስት በሌብነት ላይ በገሃድ ዘመቻ መጀመሩን ካስታወቀና ከትህነግ ጋር የሰላም አማራጭ ስምምነት ከፈጸመ በሁዋላ የመጀመሪያ እንደሆነ ተመልክቷል። ስብሰባው በተለይም ሌብነትን አስመልክቶ ጥብቅ ውይይት እንደሚደረግ ይገመታል።

የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የሚካሄደው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ እንደሆነ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መናገራቸውን ሚዲያው አስታውቋል። ስብሰባው እንደሚካሄድ የጠቆመው ይኸው ሚዲያ ሶስት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ጥሪ እንደደረሳቸው ነገረውት እንደሆነ አመልክቷል። ይሁን እንጂ ዝርዝር የውይይት አጀንዳዎ ወሬውን የነነገሩት ምንጮች እንዳልነገሩት ገልጿል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ ምንጭ፤ የስብሰባው ዋና ትኩረት “ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች” ናቸው ብለዋል። የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ኢትዮጵያ ኢንሳደር” ለፓርቲው የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ ጥያቄ ብታቀርብም፤ “በራሳችን ሚዲያ እንገልጻለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የገዢው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለመጨረሻ ጊዜ ስብሰባውን ያካሄደው ከአምስት ወራት በፊት በሰኔ 2014 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነትን በሰላም ለመፍታት መንግስት ሊተገብረው ስላቀደው “አማራጭ” በተመለከተ መወያየታቸው ተገልጾ ነበር። 

የሰኔው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በሰጡት መግለጫ፤ ገዢው ፓርቲ ጦርነቱን ለመቋጨት “ሰላማዊ አማራጮችን” ለመከተል ውሳኔ ማሳለፉን ማስታወቃቸው ይታወሳል።  

See also  "ዝናብ አትገድቡ ተብለን በቀረብንበት መድረክ 'ድል ተገኘ ' ብሎ መፈንጠዝ ነገሩ እንዳልገባን አመላካች ነው"

Leave a Reply