- ቆላ ተንቤን የወረድን እኛ ነን። የሞትን የቆሰልነው እኛ ነን። ለህዝቡ ከኛ ውጪ የሚቆረቆር የለም
የትህነግ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፂዮን በትግራይ ቲቪ ቀርበው “ውጪ ሆነው የትግራይን ህዝብ መከራና እፎይታ የማይፈልጉትን የትግራይ ህዝብ ሊሰማቸው አይገባም” ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ። ይህ ያሉት የሰላም አማራጭ ስምምነቱን አስመልክተው ማብራሪያ የተባለውን ሲሰጡ ነው። ቆላ ተንቤን የገባን፣ የቆስለን፣ የሞትን እኛ ነን። የትግራይ ህዝብ ከኛ ሌላ ተቆርቋሪ የለውም” ሲሉ ተደምጠዋል። መልዕክቱም የሰላም ስምምነቱን ለሚቃወሙ በውጭ አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መሆኑ ታውቋል።
“ውጪ ሆነው የትግራይ ህዝብ መከራ እፎይታ የማይፈልጉትን የትግራይ ህዝብ ሊሰማቸው አይገባም። የታገልንለት እኛ ነን። ቆላ ተንቤን የወረድን እኛ ነን። የሞትን የቆሰልነው እኛ ነን። ለህዝቡ ከኛ ውጪ የሚቆረቆር የለም። ህዝባችንን ወክለን መከራውን የቀመስነው እኛ ነን። ህዝቡ ሰላም እንደሚፈልግም የምናውቀው እኛው ነን። ስለዚህ የማይረባ ወሬ የሚያወሩትን ህዝቡ መስማት የለበትም” ማለታቸውን ግግራቸውን ወደ አማርኛ የመለሱ ገልጸዋል።
በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ በኢሆንም ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ተብለው በጥሬ ትርጉም ከተመለከቱት ውስጥ “ወደ ትግል ያስገባን ዋናው ጉዳይ ህገመንግስቱ ይከበር በሚል ነበረ። አሁን በስምምነቱ ህገመንግስቱ የሚከበርበትን ስምምነት በማድረጋችን ትልቅ ድል ነው” ማለታቸው ተመልክቷል። ይሁን እንጂ በስምምነቱ ትህነግ ህግ ጥሶ ምርጫ ማድረጉን አምኗል። የባይቶና የህግ ክፍል ሃላፊ ለርዕዮት የዩቲዩብ ገጽ ” አዎ እኛም ህግ ጥሰናል” ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም “ይህ ስምምነት ሰላም የሚያወርድ ነው። ሰላም ከወረደ የህዝብ ስቃይ ይቀራል። የህዝቡ ህልውና ይረጋገጣል። ሰላም የማይፈልግ የለም። ሰላም የማይፈልግ ሰውን ፕሮፓጋንዳ የትግራይ ህዝብ በውጪም በውስጥ የሚያወራውን የትግራይ ህዝብ መስማት የለበትም። ያሳለፍነውን ስቃይ እናውቃለን። በሰላም ስምምነቱ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ወደ ቦታው ከመለስን አላማችንን አሳክተናል ማለት ነው” ብለዋል። የትኛው የህገመንግስቱ ክፍል እንደተቀየረ፣ ወይም በትግራይ ላይ ለውጡን ተከትሎ ህገመንግስቱን በጣሰ መልኩ ምን እነድተፈጸመ በደፈናው ከመነገሩ ውጭ በዝርዝር ሲቀርብ አይሰማም። ከሁሉም ወገኖች ቃለ መጠየቅ የሚያደርጉ ወገኖች አድማጭ እንጂ ሙያዊ ጠያቂዎች፣ ወይም ሞጋቾች ባለመሆናቸው ህዝብ የጠራ መረጃ ማግነት አልቻለም። ይህ ችግር በፌደራል መነግስት ሚዲያዎችም ላይ የሚታይ ነው። ነጥቦቹ ከስር ቀርበዋል።

“ውጪ ሆነው የትግራይ ህዝብ መከራ እፎይታ የማይፈልጉትን የትግራይ ህዝብ ሊሰማቸው አይገባም። የታገልንለት እኛ ነን። ቆላ ተንቤን የወረድን እኛ ነን። የሞትን የቆሰልነው እኛ ነን። ለህዝቡ ከኛ ውጪ የሚቆረቆር የለም። ህዝባችንን ወክለን መከራውን የቀመስነው እኛ ነን። ህዝቡ ሰላም እንደሚፈልግም የምናውቀው እኛው ነን። ስለዚህ የማይረባ ወሬ የሚያወሩትን ህዝቡ መስማት የለበትም” ማለታቸውን ግግራቸውን ወደ አማርኛ የመለሱ ገልጸዋል።
- ከዚህ ቀደም ተኩስ አቁም በተናጥል ነበረ። አሁን በአለም ፊት፣ በታዛቢ ሀገራት ፊት ነው የፈረምነው። ታዛቢ አለ፣ ምስክር አለ። የጣሰ አካል እርምጃ ይወሰድበታል። ይህ ስምምነት ለህዝባችን ህልውና መከበር ፋይዳ ሰላለው ነው የፈረምነው። አፈፃፀሙን እኛ ብቻ ሳይሆን ያደራደሩን አካላት እየተከታተሉት ነው።
- ስምምነቱ በአፈፃፀም ደረጃ በጎ ጅማሬ አለ። እርዳታ ምግብና መድሃኒት መግባት ጀምሯል። አገልግሎት ለህዝብ ለመልቀቅ ጅምር እንቅስቃሴዎች አሉ። በዚህ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ቃሉን እያከበረ ነው።
(ከታች ይቀጥላል)
- ትጥቅ መፍታትን በተመለከተ የውጪ አካላት መውጣትን ታሳቢ በማድረግ የሚፈፀም እንደሚሆን አጠቃላይ መግባባት አለ። የህዝቡን ደህንነት አሳልፈን እንደማንሰጥ ልታምኑን ይገባል። የውጪ አካላት መውጣትን ተከትሎ በተመሳሳይ መልኩ ከባባድ መሳሪያዎችን እናስረክባለን። የትግራይ ህዝብ ህልውና ደህንነቱ የሚጠበቅ ከሆነ ትጥቁ አያስፈልግም። ያሉ የፖለቲካ ልዩነቶችን በመነጋገር የምንፈታው ይሆናል።
- የትግረይ ህዝብ አለምን ያስደመመ ፅናት አሳይቶ ለማንነቱና ለመብቱ ታግሎአል። ይህ ትግል በታሪክ የሚታወስ አኩሪ ትግል ነው። በውጪም በውስጥም ታግሏል። ለሰላምም ደግሞ ከኛ ጋ እንዲቆም፣ እንዲደግፈን፣ አብረን ለህዝብ ደህንነት እነድንቆም በአክብሮት እንጠይቃለን።
- የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ተኩስ ቆሞአል። በዚያው እንዲቀጥል ነው ፍላጎታችን። የጎደለ ነገር ካለ ላሸማገሉን አካላት እናሳውቃለን። ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ የአለም ሀገራት በሳተላይት እየተከታተሉን ነው። ስለዚህ ለስምምነቱ ተገዢ እንሆናለን። ተመሳሳዩን ከኢትዮጵያ መንግስት እንጠብቃለን። እስካሁን አፈፃፀሙ ላይ ችግር አላየንም።