ወያኔያዊ አማራነትን አማራ “አማራ ነኝ”

” የአማራነት ስሜት እንዳለባቸው ስለሚታሰብ አማርኛ ተናጋሪ ትግሬዎችን የአማራነት ሰርተፍኬት ሰጭና ነሽ የግፎች መስካሪ ሆነው ወደፊት እንዲመጡና የአማራ ፅንፈኝነትን እንዲያቀነቅኑ በአያሌው ተሰርቷል። በኦርቶዶክስ ሐይማኖት በመምህርነት :በዲያቆንነት: በቀሲስነት ለአማራ የሚቆረቆሩ መስለው የሚንቀሳቀሱ ሰባኪያነ-ወያኔዎች በፍፁም ነውረኝነት ጭምር ተላብሰው የአማራውን ፖለቲካ ለመዘወር ጥረት አድርገዋል። እያደረጉም ነው”

ዛሬም በፅኑ የማምንበት ስለሆነ ነው!!! Tomas jajaw

ወያኔን ከአራት ኪሎ ወደመቀሌ እንዲመሽግ ወይም እንዲያፈገፍግ ልንለው እንችላለን የኦሮ-ማራ ጥምረት የአንበሳውን ድርሻ ስለመውሰዱ ለጥያቄ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ለአመታት የተከማቸው የጥያቄዎች ሁሉ ድምር ጥያቄ እና የግፍ ፅዋው ሞልቶ መፍሰሱን ተከትሎ ወያኔን ለማውረድ በአይን ጥቅሻ የተፈጠረው መግባባት፥ የተቀጣጠለው የሕዝብ አመፅ እንዳይቀለበስ ግለቱን ጠብቆ ይሄድ ዘንድ፥ የኦሮ-ማራ ቅንጅት ግሩም ነበር።
በአማራ ክልል “የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው” በሚል ጎንደር ላይ የተሰማው ዘመን ተሻጋሪ በፍም እሳት መሃል የወጣ ድምፅ እንዲሁም የኦሮሞ ወጣቶች የጣናን የእንቦጭ አረም ለመንቀል ያሳዩት ዘመቻ፤ በታሪክ ድርሳናት በቀጣዩ ትውልድ ባለብዙ መልክ ትርጉም የሚሰጠው ነው።

ለአመታት በወያኔ የተዘራው የጥላቻና የመከፋፈል ፍሬ ያፈራል ሲባል የአንድነት የወንድማማችነት የመተባበር መንፈስ መሬት ነክቶ እንዲታይ የሆነበት ወቅት ነበር።
ለዛም ነበር የሕወሓት ሰዎች አይናቸው ደም ለብሶ በቁጣ እየተንተከተኩ ኦሮ-ማራን አንዴ “ያልተቀደሰ ጋብቻ ሌላ ጊዜ ደግሞ “እሳትና ጭድ” ሆነው ሳለ እንዴት በአንድነት ቆመው ልናያቸው እንችላለን በሚል መረን በለቀቀ የጥላቻ ንግግር በአደባባይ መናገራቸው ክፉ ሕልማቸው ምን ድረስ እንደነበረና አደጋ ላይ እንደወደቀ ምልክት የሰጡበት ነበር።

እንደሕዝብ አማራ እና ኦሮሞ እርስ በርሳቸው በሰይፍ ለማጫረስ የተደከመበት የአመታት መንግስታዊ ስፖንሰርነትን የሁለቱ ኤሊቶች እጅ ለእጅ ተያይዘው አንድ ነን ከሚል አፋዊ ንግግር ባለፈ ገቢራዊ ምላሽ ማሳየታቸው የወያኔን ወሽመጥ የቆረጠ ነው። የኦሮ-ማራ ጥምረት ለወያኔ የራስ ምታት የእግር እሳት ነው። በስልጣን ለመቆየትም ሆነ ወደስልጣን ለመመለስ ወይም ሐገር ለማፍረስ ኦሮሞ እና አማራን ማጋጨት የወያኔ የሕልውናው መሰረት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ወያኔም ወደመቀሌ ከመሸገ ወይም ከአፈገፈገ በኋላ ትኩረት ሰጥቶ የሰራው ስራ ይኼን ነው።

የኦሮ-ማራ ጥምረት ወያኔን ከአራት ኪሎ ለመንቀል ያስቻለ ሕዝባዊ ተሳትፎ የተደረገበት አስደናቂ ስኬታማ ድል የተመዘገበበት ኦፕሬሽን ነው።

የኦሮ-ማራን ጥምረት የሕወሓትን ተፈጥሯዊ ስሪት ካለመረዳት ለኢትዮጵያ ፖለቲካ እንግዳ ከመሆን ወይም ከወያኔ ጋር ጥቅም-ነክ ግንኙነት የነበራቸው በተልዕኮ የተሰማሩ ሰዎች እንቅስቃሴው እንዳያድግ በጊዜ ይቋረጥ ዘንድ መንቀሳቀሳቸው ለወያኔ የፈጠሩት ጉልበት የሚናቅ አይደለም።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለወያኔ በሚያደርጉት ድጋፍ ወይም በወያኔ በኩል ለኦነግ በሚደረግ ድጋፍ ብቻ የሚሳካ አለመሆኑ የተሸፈነ አይደለም። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ደግሞ ቅድሚያ የኦሮ-ማራን ጥምረት ማፍረስ ከዛም አማራው “አማራ ነኝ” ኦሮሞውም “ኦሮሞ ነኝ” ብሎ ጫፍና ጫፍ ይዞ እንዲቆም ማድረግ መቻል አለበት።

ታዲያ የኦሮ-ማራ ጥምረት ለማፍረስ አንደኛውን ወገን “በስልጣን ሽኩቻ ወይም በተረኝነት ስም” ሌላኛውን ወገን ደግሞ “የነፍጠኛው የአሃዳዊው ስርዓት እየተመለሰ ነው” በሚል ጎራ እንዲፈጠር በማድረግ፤ በሂደት ደግሞ ሁሉም ወገኖች(ማለትም የአማራም ሆነ የኦሮሞ ሕዝብ ) ትግላቸው እንደተጠለፈ እና የአብይ አስተዳደር ለነገ ጭምር ተስፋ ያላዘለ በማስመሰል በሕዝባዊ አመፅ ተደግፎ ወያኔ በነፍጥ በተመራ ጦርነት አገር ለማፍረስ በተጠና መንገድ በሐሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በከፍተኛ በጀት በተመረጡ ሰዎች ቀደም ተብሎ ጀምሮ ስራዎችን ለመስራት ተሞክሯል።

See also  ዘመቻ ምዕራፍ ሁለት ሊጀመር ነው፤ ትህነግ ተቆርጦ የተሰፋ ቪዲዮ አሰራጨ፤ " ደጋፊዎቹን ለማጽናናት ነው" ተብሏል

ወያኔ ለ27 ዓመት ያህል ፈላጭ ቆራጭ መንግስት ሆኖ መቆየቱ ከለውጡ በኋላም ሐገር የማተራመስ እድሎችን አልዘጋበትም። በኢትዮጵያ የለውጥ ታሪክ የወያኔን ለየት የሚያደርገው እስከሙሉ ቁመናና አቅሙ ከማዕከል ወደዳር መገፋቱ ነው። በዚህም እስከ ቀበሌ ድረስ የነበረውን ኔትወርክ በመጠቀም በሚያገኘው መረጃ መሰረት( በተለይ በአማራ በኩል ትግሬ አለመሆኑ እንጅ ከወያኔ በላይ “አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይም ሞት” በሚለው አስተሳሰብና ተያያዥ የወያኔ ስልጠናዎችን በየጊዜው ሲንቆረቆርባቸው የነበሩና አዕምሯቸው ከዚህ ውጭ መመልከት እንዳይችል ተደፍኖባቸው የቀሩት ሰዎች ባለመቀየራቸው) መቀሌ ተቀምጦም በቀላሉ አጀንዳውን በእነሱ በኩልም ለማስፈፀም ነገሮችን በሙሉ አልጋ በአልጋ አድርጎለታል።

ከአማራውም ከኦሮሞውም እንደፈለኩ manipulate ለማድረግ ይቀሉኛል ያላቸውን አቅም የሌላቸውን፤ ‘መረጃ ይዤባቸዋለሁ’ የሚላቸውንና ‘የፌደራሊስት ሃይሎች’ የሚላቸውን፤ እንዲሁም ቅጥረኞችን በማሰማራት ወደ በኋላ ደግሞ ከለውጡ ጋር የመቀጠል እድል የሌላቸውን፤ የተጠያቂነት ስጋት ያለባቸውን ሰዎች ወደፊት እንዲመጡና በተለያዬ መንገድ በገፅታ ግንባታ ስማቸውን በመሸጥ የጥፋት አጀንዳውን በእነሱ በኩል ወደሕዝብ ለማስረፅ ተሞክሯል። አሁንም የቆመ አይደለም። ከእነዚህ ማንነታቸው ከሚታወቁ አማራና ኦሮሞ ውስጥ ከተመረጡት (አውቀውትም ሳያውቁትም) ከሆኑ ሰዎች ጋር አጀንዳ የሚመጋገቡ ማንነታቸውን ደብቀው በጭንብል ያልሆኑትን ማንነት ሆነው የሚያስጨፍሩ በቀድሞው የደህንነት ሹም ጌታቸው አሰፋ የተበተኑ በሺ የሚቆጠሩ ሰልጣኞችም ይገኙበታል።

የኦሮ-ማራን ጥምረት ለማፈራረስ ከአክሱም ዩኒቨርስቲ ብቻ ኦሮሞኛ ቋንቋ ሰልጥነው የወጡ ከ2000 በላይ የሚሆኑ ወያኔዎች በኦሮሞ በኩል ስምሪት በመውሰድ ለውጡን ወይም የአብይን አስተዳደር “የአሃዳዊ የነፍጠኛ ስርዓት እንደሆነና እሱን ለማፅናት እየሰራ ስለመሆኑ” የዘወትር አጀንዳቸው አድርገው የኦሮሞን ሕዝብ ከአብይ አህመድ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአማራው ጋር እንዲጋጭ በስፋት ቀስቅሰውበታል። የኦሮሞን ሕዝብ ቋንቋን መሰረት አድርጎ በተከለለው ክልል ያገኘውን ጥቅም ጭምር አብይ አህመድ ሊነጥቀው የመጣ የጥፋት መሲህ ነውና ኦሮሞ ሆይ ተነስ እያሉ የእልቂት ጥሪ አቅርበውለታል። ይህን አጀንዳ የሕወሓት ስራ አስፈፃሚዎች ሳይቀር ወደአደባባይ ወጥተው ውግንናቸው ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር ስለመሆኑና ለኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ጭምር እንደሚታገሉ በDW በ TMH ሚዲያዎቹ በኩል ለማስመሰልና የኦሮሞ ሕዝብ ለአመፅ እንዲነሳሳ ቅስቀሳ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያን ለማፍረስ አማራው ቅድሚያ አማራ ነኝ ብሎ መቆም እንዳለበት በወያኔ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚታመንበት ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩት በደቡብ ክልል የሚገኙት ብሔሮችና በሌሎችም ክልሎች ያሉ ሕዝቦች በአማራ ላይ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው። እነዚህ ኢትዮጵያኒስት ኤሊቶች በአማራው ላይ ተስፋ መቁረጥ የሚችሉት አማራው አማራ ነኝ ብሎ በሁሉም ዘንድ እንደጠላት እንዲታይ የሚያደርግና በራሱ አንድ ሆኖ መቆም የማይችል የተዳከመ ሐይል ሆኖ የሚያሳየውን ‘ወያኔያዊ አማራነትን’ ማቀንቀን ከተቻለ ብቻ ነው።

See also  ዐቢይ አሕመድ አዲስ ዓመትን ከሠራዊቱ ጋር ለማክበር ማይጠብሪ ግንባር ገቡ

ወያኔያዊ አማራነትን አማራ “አማራ ነኝ” ብሎ እንዲያቀነቅን ደግሞ ወያኔ በ27 አመት የመንግስትነት ቆይታው በየቦታው የቀበራቸውን timing bombs ለመጠቀም ተሞክሯል። በግፍና በብሶት አማራው “አማራ ነኝ” ምርጫውና ብቸኛ የመዳኛ መንገድ መስሎ እንዲታየው በአንፃሩ የኢትዮጵያዊነትን ማዕቀፍን የመጠቃቱ ምንጭ አድርጎ እንዲቆጥረው ለማሳየት ተሞክሯል። ታዲያ አማራው ከግፍ ብዛት በብሶት አማራ ነኝ ብሎ እንዲቆም ግፎችንና መከራዎችን ወደሕዝቡ ለማድረስና ለማስረፅ ለአማራ የሚታገሉ የሚመስሉ የሚዲያ ብልጫን መውሰድ ግድ ይለው

ስለነበር ለዚህ ደግሞ ተመራጩና ቀላሉ ማህበራዊ ሚዲያ ነውና እሱን ባሳማራቸው የራሱ ሰዎችና ቅጥረኞች በኩል በመቆጣጠር (disinformation, misinformation )የሆኑ መረጃዎችን በማሰራጨት ወጣቱን በጥላቻ እንዲሞላና እንዲቆጣ ለማድረግ ሞክሯል።

ለአማራ ሕዝብ ሕልውና እና ሁለንተናዊ ጥቅም የሚታገሉ የሚመስሉ ነገር ግን በወያኔ ሰዎች የሚመራ በርካታ የዩትዩብ ሚዲያዎችን ከፍቷል። ቅጥረኛ አማራዎችን ደግሞ በተለያዬ መንገድ የ ዩትዮብ ሚዲያ እንዲኖራቸው ወይም እንዲከፍቱ አድርጎ አጀንዳውን ለመሸጥ የሞከረና አሁንም እየሰራበት የሚገኝ ሲሆነ በአማራ ስሞች ደግሞ ለምሳሌ እንደ ጀግና በሚቆጠሩ ወይም በሚታዩ ሰዎች ስምና ፎቶዎች፣ በታሪካዊ ቦታዎች ስምና ፎቶዎች፣ በከተሞች ስምና ፎቶዎች፣ እልፍ ዘ-ጊዮኖችን እንዲሁም ሌሎች ስሞችን በመጠቀም በሺ የሚቆጠሩ ፔጆችን እና ፌክ አካውንቶችን ከፍቶ የሶሻል ሚዲያውን በመቆጣጠር አማራው የሚጠፋበትን ከሌላው ብሔር የሚነጠልበትን “አማራነትን” እንዲያቀነቅን በተቀናጀ መንገድ ትልቅ የጥፋት ስራ ተሰርቶበታል።

አማራ ነኝ የሚለው ሃይል እንዲል የሚፈለገው ወደስልጣን የወጣውን አብይ አህመድን የኦሮሞን ተረኛ ሃይል ስለመሆኑ የሚያሳዩ ወይም የሚመስሉ ነገሮችን ብቻ ነጋ ጠባ ነቅሶ በማውጣትና ያንኑ ጉዳይ ደጋግሞ በማጉላት ኦሮሞ አማራን ሊውጠው ስለመሆኑ ስጋት መፍጠር የዘወትርና ብቸኛው አጀንዳው ማድረግ ነው። በዚህ በኩል የጠላት ጥረት በተወሰነ መልኩ አልተሳካም ማለት አይቻልም። ይህ ሃይል ከመጀመሪያው ጀምሮ ወያኔን ስትራቴጂክ አጋር በማድረጎ የተነሳ ሲሆን(ሞተሩ ወያኔ ስለሆነ) አንዴ ኦሮሙማን ሌላ ጊዜ አብይ አህመድን ሌላ ጊዜ ደግሞ ብልፅግናን ለአማራ ሕዝብ እንደዋና ጠላት የሚቆጥርና ሌሎች ብሔሮችንም ሊባሉ የማይገባቸውን ነውረኛ ነገሮችን እላፊ ሄዶ የሚናገርና አማራው ከማንም ብሔር ጋር በወዳጅነት እንዳይቀጥል በተጠናና በታቀደ መንገድ ሲሰራ የቆዬ ራሱንም ልክ እንደ የአማራ ፅንፈኛ ቁጠሩኝ የሚል የአማራ እዳ ነው።

አማርኛ ተናጋሪው ወያኔና የግብር ልጆቹ የሳይበር ሰራዊት ኦሮ-ማራን ለማፍረስ የተረኝነትና የኦሮሞን ‘ዋጭና ሰልቃጭነትን’ ለማሳየት ያነጣጠሩት አዲስ አበባን ከዲሞግራፊ የለውጥ ጉዳዮች፣ ከስራ ቅጥር ከበዓላት አከባበር ጋር በማገናኘት፤ ወለጋን፣ከሚሴን፣አጣዬን፣ቤንሻንጉልን መሬት ላይ ተልዕኮ በተሰጣቸው በሳተላይት ድርጅቶቹ በኩል በንፁሃን ላይ የተጠና ኦፕሬሽን በማድረግ የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ በማካሄድ መጭውን ጊዜ አጨልሞ ለማሳየትና እየመጣ ያለውን የአደጋ አስፈሪነት እወቁልኝ ለማለት ሞክሯል። ይህ ሃይል ከመርዶ ነጋሪነት ጥሩንባ ይዞ የእልቂት ጥሪ ከመንፋት ወይም ሐዘን ከማወጅ ያለፈ በሰነድም ሆነ መሬት ወርዶ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ ለማስቆም በመፍትሄው ዙሪያ የሕይወት መንገድ ለመቀየስ ጥሪ ቢደረግለት የውሃ ሽታ ሆኖ የሚቀር ነው። የጠላት ዋና ግቡ አማራው የማይድንበትን ወያኔያዊ “አማራነትን” ተፈጥሮ ማየት ነው። በአጭሩ አማራ ነኝ እያለ ከሌሎች ብሔሮች የሚነጥለውን ግብር እንዲዋረስ የሚያደርገውን አማራነትን ማስቀንቀን ነው። ሶሻል ሚዲያው ላይ ‘አማራ ነኝ’ እንደሚለው ሃይል ለአማራ መከፋፈል የእርስ በርስ ሽኩቻ ተጠያቂ የሚሆን አካል በፍፁም አልነበረም: ሊኖር እንደማይችል ሊታወቅም ይገባል። የተዳከመ እንጅ ጠንካራ ተቋም እንዲገነባ የማይፈቀድለት እንዲሁ ሁሌም የሚብሰከሰክ፣ የሚቆዝም፣ የሚያለቃቅስ፣ እርስ በራሱ የማይደማመጥ፣ የማይከባበር ለወያኔ ስጋት የማይሆን ሁሉንም እንደጠላት መቁጠርንና ወዳጅ ማጣትን እንደ ስትራቴጅ የሚቆጥር ጥርስ የሌለው የተቅበዘበዘ አማራን ተፈጥሮ ማየት ታሳቢ ያደረገ የጠላት አላማ ነው።

See also  አሸባሪው ህወሐት ታዳጊዎች ዕጽ እንዲወስዱ እንደሚያደርጋቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጡ

ሌላው ደግሞ አማራው “አማራ ነኝ” እንዲል በራሱ በወያኔ እንደ አንደኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ መብት በማይሰጣቸውና መዋቅራዊ ግፍ እንዲፈፀምባቸው በሚያደርጋቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ አማራዎች “የአማራነት ስሜት እንዳለባቸው ስለሚታሰብ አማርኛ ተናጋሪ ትግሬዎችን የአማራነት ሰርተፍኬት ሰጭና ነሽ የግፎች መስካሪ ሆነው ወደፊት እንዲመጡና የአማራ ፅንፈኝነትን እንዲያቀነቅኑ በአያሌው ተሰርቷል። በኦርቶዶክስ ሐይማኖት በመምህርነት :በዲያቆንነት: በቀሲስነት ለአማራ የሚቆረቆሩ መስለው የሚንቀሳቀሱ ሰባኪያነ-ወያኔዎች በፍፁም ነውረኝነት ጭምር ተላብሰው የአማራውን ፖለቲካ ለመዘወር ጥረት አድርገዋል። እያደረጉም ነው። በሌሎች ክልሎች ተወለድን የሚሉ እነዚህ ሚዲያ ላይ በአማራዎች ላይ ተፈፀሙ በሚባሉ ጥቃቶች ላይ የሚያስተላልፉት መልዕክትና የሚይዙት አቋም የጥቃቱ ፈፃሚዎች ከሚባሉት ቢብስ እንጅ ያነሰ አይደለም። አንድ ለአማራ ተቆርቋሪ ነኝ ሊል የሚችል የእዛ አካባቢ ተወላጅ ችግሩን እንደሰማ ተጨማሪ እልቂት እንዲደርስ የሚያደርገው ጥሪ ስሜቱን መቆጣጠር ስላልቻለ ነው ብለን እንለፈው ቢባል እንኳን ‘ ከ ዓመት እስከ ዓመት በየጊዜው በእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍን (ወገኖቹን በእሳት መሃል አስቀምጦ) እንዴት እንደተቆርቋሪነት ሊቆጥር ይችላል?!’ የሚል ጥያቄ የሚጭር ነው። ደግሞ በጎ ተሳትፎ አለማሳየታቸው ብቻ አይደለም እኮ የሰዎቹን አማርኛ ተናጋሪ ትግሬዎች ናቸው የሚያስብለኝ። እንስከን :ለአማራ ጠላት የሚያበዛ ወዳጅ የሚያሳጣ አላስፈላጊ ንግግር አናድርግ የሚሉትን አርቆ-አሳቢ ትክክለኛ ተቆርቋሪ ወገኖችን በብአዴንነት ለመክሰስ ወይም እንደ አድርባይ ለመቁጠር ሞራል የሌላቸው የጃስ በለው አቀንቃኝ መሆናቸውም ጭምር ነው። በወያኔ ተልዕኮ ከተሰጠው ሰው በስተቀር እንደአማራ ምንም አይነት መሬት የነካ ዝግጅት በሌለበት ሁኔታ፤ መናገር ወይም መፃፍ ስለተቻለ ብቻ ቤተሰቦቹ በቀጣዩ ቀን ቀድሞ በተደራጀና በተዘጋጀ የጥፋት ሃይል ያልቁ ዘንድ ቅስቀሳ ሊያደርግ የሚያስችል የሞራል ልዕልና ሊኖረው የሚችል ተቆርቋሪ አለ ብዬ አላስብም።
ከንፍሮ ጥሬ ግፍ ያንገበገባቸው አማራዎች የተሳሳተው መስመር ስለመከተላቸው ያልገመገሙ ስለመኖራቸው መስካሪ አያሻም። የሚታወቁና ልካቸውም የተለየ ነው።
አማራውን በሁሉም ነገር ድንኳን አስጥሎ ንፍሮ አስቀቅሎ ነጠላ አስዘቅዝቆ የሚያስለቅሰው ወያኔና የግብር ልጆቹ እንጅ ለአማራው የሚቆረቆሩ ትክክለኛ የአማራ ልጆች ድምፅ አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። የሚጮኸው ድምፁ የአገር አፍራሾቹ ወያኔና የግብር ልጆቹ ነው‼️

የፅሑፉ አላማ ችግሮች የሉም ከሚል ወያኔያዊ ትርጉም አሰጣጥ ፈፅሞ የራቀ ነው‼️

Leave a Reply