የኢፌዴሪ መከላከያ ታህሣሥ 6 ቀን 2015 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር እና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ በምታበረክተው ጉልህ አስተዋጽኦ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ታላቅ ስም እና ዝና ያላት በአበርክቶዋ ፊት የምትቀመጥ ሀገር ናት።

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይል በኮሪያና በኮንጎ ያደረጋቸው አኩሪ የሰላም ማስከበር ተግባራት ዓለም አቀፍ እዉቅናን ከመስጠቱም በላይ አሁን ላይ ላለዉ የሰላም አስከባሪ ሃይል መሰረት የጣለ ነዉ፡፡

በሩዋንዳ፣ በብሩንዲ እንዲሁም በላይቤሪያ ተሰማርቶ የነበረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ባሳየው መልካም ስነ-ምግባር እና ተልእኮውን በብቃት በመወጣቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡በተመሳሳይ አሁንም በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ኢትዮጵያ ሚናዋን በብቃት እየተወጣች ትገኛለች፡፡

ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ በአፍሪካም ይሁን ከአፍሪካ ውጪ ባላት መልካም ዝና የተነሳ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት እና ተወዳጅነትን ያተረፈች በምትሰማራበት ቀጠና የጎላ አስተዋጽኦ የምታበረክት አበርክቶዋም በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል በተለይም በተቀባይ ሀገር ዜጎች ዘንድ ታላቅ ከብር እና ስም የሚሰጠዉ በእንዲሁ አይደለም፡፡የተረጋጋ ቀጠናዊ ሰላም እንዲኖር ለህይወቱ ሳይሰስት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ለተፈጥሮአዊ እና ሰዉ ሰራሽ መሰናክል ሳይንበረከክ ግጭቱን ወደ ሰላም ለመመለስ የሚያደርገዉ የቀን ከሌሊት ጥረት ቅድሚያ ትኩረቱ ነዉ፡፡
ምንጊዜም ለተልዕኮዉ ስኬት ቅድሚያ የሚሰጠዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከኮሪያ እስከ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዉ የተሰጠዉን ማንኛዉንም ግዳጅ በድል እና በህዝባዊነት መንፈስ ከመፈፀሙ ዉጪ በአቤቱታ የሚገለፅ አንድም የስራ አፈፃፀም ክፍተት አላሰየም፡፡ለዚህም ነዉ እንግዲህ ኢትዮጵያ ከራሷ ሰላም ባለፈ ለአለም ህዝብ ሰላም ጉልህ ድርሻ ካላቸዉ ሀገራት መካከል ቅድሚያ የተሰጣት፡፡

በኮሪያ ልሳነ-ምድር ከ1943-1945 ዓ.ም ከክቡር ዘበኛ እና ከጦር ሰራዊቱ የተወጣጣ ሰራዊት በማዘጋጀት ኢትዮጵያ ቀድመዉ የሰላም ምላሽ ከሰጡ ሀገራት መካከል አንዷ ሆናለች፡፡በዚህም ለሶስት ተከታታይ ዙሮች በነበረዉ የሰላም ማስከበር ቆይታ የኢትዮጵያ ሰራዊት በተባበሩት መንግስት የሰላም አስከባሪ ሃይል በፈፀመዉ ተልዕኮ የደቡብ ኮሪያን ፕሬዘዳንታዊ ጦር ክፍል ከፍተኛ ሚዳይ እና ሪቫን ተሸልሟል፡፡በዚህ የሰላም ማሰከበር ተልዕኮ ላይ ኢትዮጵያ በጦርነት የተማረከ እና የጠፋ ወታደር የሌላት ብቸኛ ሀገር ለመሆን በቅታለች፡፡

See also  ዕውቅና የተሰጣቸው ቋንቋዎች የፌዴራል የስራ ቋንቋ ሆነው እንዲያገለግሉ ዝግጅት እየተደረገ ነው

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለኮንጎ ሰላም ዕዉን መሆን አለም አቀፍ ጥሪን ተቀብለዉ ከ1952-1955 ዓ.ም ለተልዕኮዉ ከተሰማሩ ሀገራት መካከልም አንዷ ለመሆን ችላለች፡፡እንደ ቃኘዉ ሻለቆች ሁሉ የኮንጎ ጠቅል ብርጌዶችም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የኮንጎን ሉዓላዊ መንግስት እና ህዝብ በመከላከል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ምክር ቤት የጋራ ደህንነት እና ሰላም ታሪክ ዉስጥ አስደናቂ የሆነ አለም አቀፍ የሰላም ተልዕኳቸዉን ፈፅመዋል፡፡
ይቀጥላል………

ዉብሸት ቸኮል ENDF FACEBOOK

Leave a Reply