ቤት ዘግቶ አሳት በመለኮስ ሶስት ሰዎችን አቃጥሎ የገደለው እድሜ ልክ ተቀጣ

በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጀንጁቃ ቀበሌ ሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 2፤00 ሰዓት ላይ ጌታሁን የተባለ ግለሰብ ካልተያዙ ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ሶስት የግል ተበዳዩችን አንድ ቤት ውስጥ በማስገባት ቤቱን በላያቸው ላይ በመቆለፍ ከውጪ ቤቱ ላይ ቤንዝል በማርከፍከፍ ግለሰቦቹ ከነቤቱ ተቃጥለው ህይወታቸው እንዲያፍ ያደርጋል።

ፖሊስም ወንጀሉ የተፈፀመበት ስፍራ ደርሶ ተጎጂዎችን ማንነት በማይለይበት ሁኔታ ቃጠሎ እንደደረሰባቸው ይመለከታል፤ ግሰለቦቹ ከአከባቢው ተሰውረው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተከሳሹን በቁጥጥር ስር ያውላል።

በተጨማሪም ተከሳሹ ሌሎች ካልተያዙ ግብርአበሮቹ ጋር በመሆን በወረዳው መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ፣ም በግምት ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት አንደኛ ተከሳሽ በያዘው ጦር መሳሪያ የግል ተበዳይን ሁለት ቦታ ተኩሶ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድጉ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ዐቃቤ ህግ በመሰረተው ክስ መሰረት ተከሳሽ ስንታየሁ ጌታሁን ጥፋተኝነቱ በመረጋገጡ በሰባቱም ክሶች በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። Via wasu telegram page

See also  ሁለት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኢንስፔክተሮች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ

Leave a Reply