መንግስት ል ዑካን ከላከ በህይዋላ በማላዊ 245 አስረኞች በምህረት አንዲፈቱ ተውሰነ፤ ስድስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በሚደረግ ህገወጥ ጉዞ ኢትዮጵያን ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 30 ሰዎች በሰሜናዊ ማላዊ በጅምላ ተቀብረው መገኘታቸውን የማላዊ መንግስት ከሳምንታት በፊት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው ልኳል ።

ቡድኑ ከታህሳስ 02 ቀን እስከ 08 ቀን 2015 ዓ.ም. በማላዊ በነበረው ቆይታ ከሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከማላዊ ፖሊስ አገልግሎት፣ ከማላዊ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዲፓርትመንት ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል ።

የውጭ ጉዳይ አጣሪ ቡድን ከማላዊ መንግሥት ኃላፊዎች ጋር በጅምላ የተቀበሩት ሰዎች ምርመራ ሂደት ያለበት ደረጃ ፣ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ተጠያቂ በሚሆኑበት ጉዳይ ፣ በእስር ላይ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዝርዝር መረጃ ማግኘት በሚቻልበት እና ከእስር ተፈተው ወደ አገራቸው መመለስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያደረጉት ውይይት ውጤታማ ሆኖ ተጠናቋል።

በውይይቱም በመላው ማላዊ በእስር ላይ የሚገኙ 245 ኢትዮጵያውያን ሁሉም በይቅርታ ተፈተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል። እስረኞቹን የሚመለከት መረጃ ለልዑካን ቡድኑ እንደተሰጠ ተገልጿል።

በቀጣይም እስረኞቹን ወደ አገር ቤት የመመለሱን ስራ ከማላዊ የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት መግባባት ላይ መደረሱ ታውቋል።

ኢትዮጵያዊን ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩት እና በጅምላ ተቀብረው የተገኙ ሟቾችን በሚመለከት ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ የማላዊ መንግሰት እስካሁን ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውሎ ጉዳያቸው በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየታየ መሆኑም ታውቋል።

ቀሪ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በመያዝ ለህግ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት እያተደረገ እንደሚገኝም ተገልጿል። ቡድኑ በማላዊ ቆይታው ሞቾች የተቀበሩባቸውን የመቃብር ስፍራዎች ጭምር መጎብኘቱ ታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጣሪ ቡድን በማላዊ የነበረውን ቆይታ በማጠናቀቅ ወደ ዛምቢያ አምርቷል። ቡድኑ በዛምቢያም ባለፈው ሳምንት ከመዲናዋ ሉሳካ ወጣ ባለ ስፍራ ኢትዮጵያዊን ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 27 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ሁኔታውን የሚመረምር ይሆናል።

የህገወጥ የሰዎች ዝውውር አሳሳቢ በመሆኑና ችግሩን ለመከላከልየሁሉም አካለት የተቀናጀ ጥረት አስፈላጊነት ነው።(ኢ.ፕ.ድ)

See also  አረብ ኤምሬትስ ኢትዮጵያን ላይ የጣለችውን የጉዞ እገዳን ልታነሳ ነው

Leave a Reply