ወሰለተች ብሎ ሚስቱን ገድሎ ከ፩፫ኛ ፎቅ የተከሰከሰው ዳኛ

በትናትናለው ዕለት በአዲስ አበባ እራሱን ከ 13 ፎቅ ወርውሮ የገደለው ዳኛ ከጎንደር ዩንቨርስቲ በህግ ትምህርት በማዕረግ የተመረቀ ነበር ።

በ30ዎቹ እድሜ መጨረሻ የሚገኘው ባሌ ጎባ ተወልዶ ያደገው ዳኛ ትንሳኤ በላይነህ ከስድስት ወር በላይ አብራ የኖረችው የፍቅር አጋሩን የገቢዎች ሰራተኛ ዙፋንን በፌስ ቡክ ገፁ የጠቀሳቸው የሙያ አጋሮቹ እና ጓደኞቹ ከዙፋን ጋር ወሰለቱ በማለት እሷን ገድሎ እራሱን መገናኘ ከሚገኘው የዳኞች መኖሪያ ቤቱ ፎቅ ወርውሮ ትናንት ምሽት 1: 45 አካባቢ ማጥፋቱ ይታወሳል።

ፊደል ፖስት በደረሰው መረጃ ዙፋን የተባለችው አጋሩ እሷም የባሌ ጎባ ተወላጅ ስትሆን ሟች ትንሳኤም በፌዴራል ደረጃ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ያገለግል ነበር።

ከፎቅ ከወደቀ በኋላ ሰውነቱ እንደተበታተነም ታውቋል።
ትንሳኤ ከዛሬ 11 ዓመት ከጎንደር ዩንቨርስቲ በህግ ትምህርት በማዕረግ የተመረቀ ነበር።

ዛሬ ቀን 6:00 ሰዓት ከዳኞች መኖሪያ አስከሬን ሽኝት ይደረግለታል።
Via: ፊደል ፖስት

See also  ደብረጽዮንና ጌታቸውን ጨምሮ 37 ተከሳሾች በመገናኛ ብዙሃን ጥሪ እንዲደረግላቸው ታዘዘ

Leave a Reply