ዜናው “ሃይሌ ታገተ” አይደለም። “ሃይሌ አገተ” ነው። ያገተውም ለተወሰኑ ሰዓታት በሃሰት ተጥምቆ፣ በሃስት ተቀድቶ፣ በሃሰት ሲቸረቸር የነበረውን ዜና ነው ያገተው። “ብስራት ሬዲዬ የዘገበው ሀሰተኛ ነው” የማለት ያህል ሃይሌ “እኔ ላይ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ” በማለት የደራውን ወሬ አግቶታል። –

አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የመክና አደጋ ደረሰበት የሚለውን ዜና “የማይበገሩ እግሮች፣ ሮጬ ላሯሩጣቸው” በሚለው የተሰረቀ ግጥም አጅበው ለዩቲዩብ ዜና ሲተውኑ የነበሩ በሙሉ በሃይሌ ማስተባበያ ድካማቸው አልተሳካም። በቅ ወሬ እንዲህ ነው!! ነገ አንዱ የሞቀው ተነስቶ አብይ አህመድ አገር ለቀው ወጡ ብሎ ላለማራጋቡ ማስረጃ የለም። መተማመናም የለም። ሚዲያና ሚዲያተኞች … የሆኑባት አገር። አል አይን ሃይሌ ጠይቆ የጻፈው ይኸው። ሃይሌ ቢያንስ ለቤተሰቦችህ ሟርቱ በወሬ ይለፍልህ።

አንጋፋው የኢትዮጵያ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የትራፊክ አደጋ እንዳልደረሰበት ተናገረ። አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት ሚዲያዎች እየዘገቡ ሲሆን አትሌቱ ለአል ዓይን አማርኛው ክፍል በሰጠው ቃል ሀሰት ነው እኔ ላይ የትራፊክ አደጋ አልደረሰም ብሏል።

ኃይሌ ፤ ” ያለንበት ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው፣ ሌላም ነገር ቢሆን እንዲህ ነው የውሸት መረጃ የሚሰራጨው ” ብሏል። ዛሬ ጠዋት ላይ ” ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ” በተሰኘው ሬድዮ ጣቢያ ከሚሰራጨው ” አውቶሞቲቭ ” የሬድዮ ፕሮግራም ጋር በስልክ ተደውሎልኝ ስለፍጥነት መገደቢያ ወይም ስፒድ ብሬከር ችግር መሆኑን አስተያየት ሰጥቼ ነበር ያለው ኃይሌ ፤ ” ይህ ማለት ግን ዛሬ በእኔ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶብኛል ማለት አይደለም ” ሲል ተናግሯል።

አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ፤ በተሰራጨው ሀሰተኛ ዘገባ ምክንያት ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ አሳስቧቸው እጅግ ብዙ የስልክ ጥሪዎች እያደረሱኝ ነው ሲል ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጠው ቃል ተናግሯል።

Leave a Reply