ራዴፓ- ትህነግ በራያ አከባቢው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው

– በተለያዩ አከባቢዎች ምሽግ እየቆፈረ : ወደ አላማጣ ከተማም በተናጠል እየሆኑ ሰርጎ በመግባት ላይ መሆናቸውን ….

ትህነግ ተቀጥቅጦና ከስሮ እንዳስረከበው በተገለጸበት በአላማጣ ዙሪያ ኩንኩፍቱና አቅራቢ በሚገኙ አከባቢዎች ታጣቂዎቹ በብዛት መታየታቸውና ወደ አላማጣ ከተማም በተናጠል ሰርገው በመግባት ላይ መሆናቸውን መረጃ እንዳለው ጠቅሶ የራያ ዴሞክራሲያ ፓርቲ ራዴፖ ጽ/ቤት የስጋት መልዕክት ማስተላለፉ ተሰማ። ትህነግ እንኳን ጦርነት ለመክፈት ሰርጎ ገብ አሰማርቶ ለማጥቃት የሚያስችል ብቃትና አቅም ባይኖረውም መንግስት በጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግ ዜናውን የሰሙ አመልክተዋል።

ሰሞኑን የህወሀት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል “የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ላይ ብዙ ጉድለቶች አሉ” በሚል የኢትዮጵያን መንግስት ከሰው መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ትህነግ አራተኛውን ዙር ጦርነት ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት በራያ ማህበረሰብ ዘንድ መኖሩን ነው የፓርቲውን ጽህፈት ቤት ጠቅሶ አንከር ሚዲያ የዘገበው።

አንዳንድ የጦርነት ዝግጅቶች የሚመስሉ እንቅስቃሴዎች መታየታቸውን በመጥቀስ ትህነግ በሰላም ስምምነቱ ሂደት ላይ አደጋ መደቀኑን ነው የራዴፓ አመራሮች አጠንክረው እየገለጹ ያሉት።

ትህነግ ህገወጥ ነው ተብሎ በኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ በተደረገውና በፕሪቶሪያው ስምምነትም እንዲፈርስ በፊርማ ያረጋገጠውን ክልላዊ መንግስቱን በማስቀጠል 11 አባላት ያሉት የተደራዳሪ ልዑካንን ሹመት ማጽደቁ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ትህነግ እሁድ ዕለት ስላካሄደው የምክር ቤት ስብስበባና የዶ/ር ደብረጺዮን ውንጀላ ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ “ለሰላም አማራጭ ስምምነቱ ሁሉም ወገኖች እኩል ሊሰሩ ይገባል” በሚል መንግስት ጥቅል ማሳሰቢያ መስጠቱ አይዘነጋም።

ራዴፓ ያስተላለፈውን ስጋት ይፋ ማድረጉን ያደነቁና ለጸጥታ ክፍሉ ቅርብ የሆኑ ” ትህነግ ካሁን በሁዋላ ሁከት እንጂ ጦርነት የመክፈት አቅምም ሆነ ችሎታ እንዲሁም የህዝብ ድጋፍ አይኖረውም” ይላሉ። አያይዘውም ከየአቅጣጫው የሚደርሱ የስጋት መልዕክቶች ጠቀሜታቸው የጎላ እንደሆነ አክለው፣ መንግስት ባሉት የጸጥታ መዋቅሮቹ ሁሉ ለአፍታም እንደማይተኛ፣ ይበጀኛል ብሎ ጦርነት ከመረጠ ትህነግ የሚያውቀውን የመከላከያ ክንድ በፍጥነትና በአጭር ሰዓታት እንደሚቀምስ፣ የሚወርበትንም ምት እንደማይቋቋም ስለሚያውቀው ብዙም ስጋት እንደሌለ አመልክተዋል። ከሁሉም በላይ ለትግራይ ህዝብ የሚበጀው፣ ለትግራይ ጎረቤት ክልሎችና አገራችን የሚጠቅመው ሰላም በመሆኑ ትህነግ ዳግም አያብዳል ብለው እንደማያስቡ አምረውበታል። ምን አልባትም የፖለቲካ ስልጣኑንን የሚያጣበት አማራጭ ሰፊ በመሆኑ ከዚያ ጭንቀት በመነጨ እንደሚወራጭ ግን መገመት እንደማያዳግት አመልክተዋል።

See also  ሳይርቅ በቅርቡ፣ሳይደርቅ በርጥቡ! ይሻላል።

Leave a Reply