“በላይክ መጠን ብዛት ብር እንከፍላለን” ኢትዮ ቲክቶክ

ኢንፎቴክ ሶፍትዌር ሶሉሽን ከየትም ዴሊቨሪ ጋር በጋራ በመሆን ኢትዮቲክቶክ የተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ አደረጉ። ኢትዮቲክቶክ አሜሪካን ሀገር በሚገኝ ኢንፎቴክ ሶፍትዌር ሶሉሽን እና በየትም ዴሊቨሪ አማካኝነት የተሰራ ሲሆን በዛሬው እለትም ሁለቱ ተቋማት በቀጣይነት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ኢትዮቲክቶክ ለኢትዮጵያዊያን እንዲስማማ ተደርጎ በኢትዮጵያዊያን የበለፀገ መተግበሪያ ነው ያሉት የኢንፎቴክ ሶፍትዌር ሶሉሽን ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ቀዳማይ ሙሉዓለም ከባህል እና ወግ ጋር የሚጋጩ ቪዲዮዎችን የሚቆጣጠር ስርዓት መዘርጋቱን ገልፇል።

አፕሊኬሽኑ ከ1 ወር በኋላ በፕሌይስቶር እና አፕስቶር ላይ እንደሚለቀቅ የገለፁት የየትም ዴሊቨሪ ስራ አስኪያጅ አቶ መንሱር ጀማል ናቸው አቶ መንሱር አክለውም ኢትዮቲክቶክ በላይክ መጠን ለቪዲዮ ባለቤቶች ገንዘብ እንደሚከፍል ገልፀው ከሶስት ወር በኋላ ቀጥታ ስርጭት (live) እንደሚጀምሩም ተናግሯል።

See also  ቱርክ - 296 ሰዓታት በፍርስራሽ ውስጥ

Leave a Reply