ስርዓት የለቀቁ የሃይማኖት ሚዲያዎች በህግ ሊቀጡ ነው

ሀላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችን በሚያስተላልፉ የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ላይ በህጉ መሰረት እርምጃ እንደሚወስድ ባለስልጣኑ አስታወቀ

የዜጎችን ሰላምና አብሮነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉና ሀላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችን በሚያስተላልፉ የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ላይ በህጉ መሰረት እርምጃ እንደሚወስድ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፤ የመገናኛ ብዙሃን ተሰራጭቶ የዜጎችን ሰላምና አብሮነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉና ሀላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችን በሚያስተላልፉ የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ላይ በህጉ መሰረት እርምጃ ይወሰዳል፡፡

ባለስልጣን የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ክትትል ክፍል ግኝቶችና ከዜጎችና ከተቋማት የደረሱት ቅሬታዎችና ጥቆማዎች እንዳመለከቱት፤ የተወሰኑ የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚጠበቅባቸው ህጋዊ፣ ማህበራዊና ሙያዊ ስነምግባር ያፈነገጡ መልዕክቶችን እንደሚተላለፍባቸው ተስተውሏል ነው ያለው ባለስልጣኑ፡፡

የዜጎችን የመቻቻልና አብሮ የመኖር ዕሴት የሚሸረሽሩ ሁከትና ግጭትን የሚጋብዙና በግለሰቦችና በማህበረሰቦች ላይ አካላዊ ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሱ ንግግሮች ተሰራጭቶባቸዋል ሲልም ነው ያስታወቁው፡፡

ከተቋቋሙበት መርህና አላማ በረቃረነ አኳሃን በተለያዩ የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን የሚፈፀሙ ህጋዊና ሙያዊ የስነምግበናር ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙም ባላስልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።

ባለስልጣኑ ከሰሞኑ በተወሰኑ የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ላይ የቀረቡለትን ቅሬታዎች ከህግና ከሙያ ስነምግባር አንፃር መርምሮ እንደ አስፈላጊነቱ ውጤቱን ለፍትህ አካላት እንደሚያቀርብም አስታውቋል፡፡

የሀይማኖት መገናኛ ብዙሃን ሶስት መሰረታዊ መርሆችን አክብረው እንዲሰሩ ይጠበቃል ያለው ባለስልጣኑ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም ፡-

1 ሀይማኖታዊ አስተምህሯቸውን ለተከታዮቻቸው ሲያስተምሩ የሌሎችን ሀይማኖትና ዕምነት አክብረው እንዲያስተምሩ፤

2 ከተቋቋሙለት ሀይማኖታዊ ጉዳይ ውጪ ሌሎች ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጉዳዮች በመገናኛ ብዙሃኑ እንዳያስተላልፉ እና

3 ከጥላቻ በዜጎች መካከል አብሮ መኖርን ከሚያውክ በማንኛውም አግባብ ሁከትና ግጭ ሊቀሰቅስ ከሚችል በዜጎች ላይ ስነልቦናዊም ሆነ አካላዊ ጥቃት እንዲደርስ ከሚያነሳሳ ንግግር እና ከመሰል አሉታዊ መልዕክቶቸ ታቅበው እንዲሰሩ ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡

(ኢ.ፕ.ድ)

See also  ከነገ ጀምሮ 450 በርሜል ነዳጅ የሙከራ ምርት ማምረት እንደሚጀመር አብይ አህመድ ይፋ አደረጉ

Leave a Reply