ይህ ምስል ኢትዮጵያ ነው። በከፊል ጥቂቱ ነው። ይህ ታላቅ የአርሶ አደሮቻችን፣ የጥቂት ቀና አሳቢ መሪዎችና ሃላፊዎች ተግባር ግን ዜና አይደለም። ለዜና አይበቃም። ዜና ከሆነ ገቢ ይቆማል።

ዛሬ ኢትዮጵያ 9.5 ሚሊዮን ሕሳናትን በቀን ሁለቴ የምትመግብ ብቸኛ የአፍሪካ አገር ናት። ከዓመታት በፊት በፊት ተማሪዎች በርሃብ ክፍል ውስጥ ይወድቁ ነበር። ዛሬ ያ የለም። ይህ ዜና አይደለም። ምክንያቱም ገቢ ይቆማል።

ትናንት ስንዴ በገፍ እየተገዛ ይገባ ነበር። ዛሬ ግን ያ ቆሟል። ኢትዮጵያ ስንዴና ፍራፍሬ በገፍ ወደ ውጭ ለመላክ እየተንደረደረች ነው። ይህ ዜና አይደለም። ከሆነ ገቢ ይቆማል።

ኢትዮጵያ በክፍለአገራት በቀን እስከ አራት መቶ ሺህ ዳቦና ዱቄት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች እየገነባች ነው። ይህን ሁሉ የምታደርገው በጥቂት ቀና አሳቢ ዜጎችና በውስኝ መሪዎቿ ጥረት ከሌቦች ጋር በሚደረግ ፍልሚያ ውስጥ ሆና ነው። ይህ ዜና አይደለም። ከሆነ ገቢ ይቆማል።

Leave a Reply