ኢትዮጵያና ኤርትራ ተስማሙ፤ ትህነግ ለኤርትራ ስጋት እንዳይሆን ቀድሞ ትጥቅ ይፈታል

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ትህነግን አስመልክቶ ከስምምነት መድረሳቸውና በመካከላቸው የገነቡት መረዳዳት በነበረበት እንደሚቀጥል ተሰማ። ትህነግ ለኤርትራ ስጋት መሆን በማይችልበት መልኩ ስራዎች መሰራታቸው ተሰማ። በናይሮቢው ስምምነት መጨረሻ ይህን የሚያጠነክር መረጃ ይፋ ሆኗል።

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ የትህነግ አመራሮች “ወራሪ” የሚሉትን የአማራ ሃይልና የትግራይን አካባቢዎች ይዟል በሚል የሚከሱት የኤርትራ ሰራዊት ለቀው እንዲወጡ በጥቅል ከመጠየቅ ውጪ ስም ዘርዝረው ቦታዎቹን አይጠቅሱም።

የትህነግ አመራሮችና ራሱ ድርጅቱ እንደ አቋም የያዘው የኢትዮጵያንና የኤርትራን መንግስት ማቃቃር እንደሆነ በስፋት ቢገለጽም ሁለቱ መንግስታት ሁሉንም ጉዳይ በስምምነት ለማራመድ አቋም መያዝቸውን ኢትዮ 12 ሰምታለች። ኤርትራ በግልጽ የያዝቸው አቋም ትህነግ ዳግም መሳሪያ እንዳይስወነጭፍና በጥቅሉ ስጋት እንዳይሆን፣ ስጋት የሚሆን ከሆነ ግን በቅርብ ረቀት ሆኖ መመከት የሚል ነበር።

በዚሁ መመዘኛ መንግስት በሁለተኛው የናይሮቢ ስምምነት ሲጓተት የቆየው መሳሪያ የማስፈታት ተግባር ቀነ ገደብ ተቆርጦለትና ተቆጣጣሪ ተመድቦለት ተግባራዊ እንደሚሆን ይፋ ሆኗል። ትህነግ ታጣቂዎቹ መከላከያ በሚወስንላቸው ስፍራ የታጠቁትን የማይፈቀድ መሳሪያ እየፈቱ እንዲያስቀምጡ ስምምነት ተደርሷል። አንድ ክልል ምሊኖረው ከሚገባው በላይ መሳሪያና ትጥቅ እንደማይኖረው ይፋ ሆኗል። ይህ ማለት ትህነግ በሚሊሻና ፖሊስ ደረጃ ከተማ ለመጠበቅ በሚታጠቀው ትጥቅ ለኤርትራ ስጋት አይሆንም። ድንበር ላይ የሚሰፍረው መከላከያ ሰራዊት በመሆኑ ከኤርትራ ሰውራዊት ጋር ህብረት ሊመሰርቱ ይችላሉ። ኢትዮጵያና ኤርትራ የመከላከያና የደህነነት ውል ስላላቸው በዚህ ውላቸው መሰረት አብሮ ለመስራት ክልሎች መከላከል አይችሉም። ህጉም አይፈቅድላቸውም።

የመንግሥት ወኪሎች፣ የትህነግ አመራሮች፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የኢጋድና የአፍሪካ ኅብረት የባለሙያዎች ቡድን ያጣመረው (ጥምር ግብረሃይል) ቡድን በጋራ የሰላም ስምምነቱን አካሄድ ይቆጣጠራሉ። መንግሥትና ትህነግ የደረሱትን የሰላም ውል የአፈጻጸም ስምምነት ሊተገበር ግድ ሆኗል። ይህን ስምምነት የሚጥስ ተግባር ከተፈጸመ በየአፍሪካ የባለሙያዎች ቡድን አማካይነት ሪፖርት ይሆናል። ሪፖርቱን ተንተርሶ ማስተካከያ ይደረጋል። አሜሪካ ስምምነቱን በሚያፈርሱ ሃይሎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደማታቅማማ ማስታወቋ ይታወሳል።

በዚሁ የሰላም አማራጭ ስምምነት መሠረት የትህነግ አንጋቾች ትጥቅ የማስፈታት ሂደት ተጠናቆ ዳግም የትህነግ አንጋቾች የጦር መሳሪያም ሆነ ማናቸውንም ተተኳሽ እንደማይዙ፣ ያልተፈቀ የጦር መሳሪያ ዝውውር እንደማያከናውኑ ይረጋገጣል። የትህነግ ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ የሚፈቱት ትጥቅ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ለይቶ በሚያዘጋጃቸው ቦታዎች ስለመከናወኑ ማረጋገጥ ደግሞ የጥምር ሃይሉ ሃላፊነት ይሆናል። በውይይቱ ወቅት ማህበራዊ አገልግሎቶችን ጨምሮ የስንዴ፣ የዱቄትና የመድሃኒት እርዳታ አሁን ካለው በላይ እንዲቀርብ የሚስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት መደረጉና አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል።

See also  ዜና መገልበጥ - አዲሱ የማተራመሻ ስልት

ይህ ሲሆን ትህነግ ለአፋር፣ ለአማራም ሆነ ለኤርትራ ስጋት የመሆን እድሉ ያከትማል። ኢትዮ12 የሰማችው ዜና በትግራይ አጎራባች ክልሎችና ኤርትራ ዘንድ ያለው ስጋት ትህነግ ቀደም ሲል ያደርገው እንደነበር በየትኛውም ሰዓት ወረራ ይፈጽማል የሚል ነው። ይህ እንዳይሆን መከላከያ ስራውን እንደሚሰራና በስምምነቱ መሰረት በትግራይ ውስጥ ልክ እንደ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ አፋር፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ ወዘተ … ያልተፈቀደ መሳሪያ በትህነግ እጅ ዳግም እንዲገባ አይደረግም።

“ትህነግ መሳሪያ ሲቀብር ነበር” በሚል ሲቀርብ ለነበረ ክስ ” የብረት ዘር ያለበትን ቦታ ሁሉ የሚጠቁም ዘመናዊ መሳሪያ ስላለ። ከመከላከያ ሊደበቅ እንደማይችል፣ በድሮን በሚነሱ ምስሎችም በመታገዝ ስለሚሰራ እንዲህ ያለው ነገር ውጤት አይመጣም። ከተደረግም ትርፉ ድካም ብቻ ነው” ሲሉ ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ አስታውቀዋል።

መንግስት መቀለን እንዲረከብ ተወላጆቹ መተየቃቸውንና፣ በመቀለ በፓትሮል የተደገፈ ዘረፋ መካሄዱን ተከትሎ መንግስት ቀደም ሲል ይሆናል ያለውን እርምጃ እንደሚወስድ መግለጹ ይታወሳል።ጵ አሁን እንደተሰማው ከሆነ የመንግስት ሃይል በቅርቡ መቀለን በሰላማዊ መንገድ ይቆጣጠራል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና የትግራይ ህዝብ ከውዳጅ ጎረቤቶቹና ከጠቅላላው ህዝብ ጋር ወደ ቀድሞ መተማመን የተመላበት ግንኙነቱ እንዲመለስ የህዝብ ለህዝብ መድረኮች ለማካሄድ፣ ይህም መድረክ በትግራይም እንደሚከናወን ዕቅድ መኖሩ ተሰምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “የተጀመረው ሰላም ወደ አስተማማኝ ደረጃ አድጓል” ሲሉ ሰሞኑንን መናገራቸው ይታወሳል።

bew

Leave a Reply