የጸረ ሙስናው ውይም የሌበነቱ ትግል ፍሬ እንዲያፈራ ሚዲያዎች ጉልህ ሚና እንዳላቸው ጥርጥር የለውም። ሚዲያ በአገር ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም ከማራመድ ውጪ ሌብነት ላይ ለመዝመት ፈቅድ መጠበቅም አይገባውም። ሰሞኑንን መንግስት ለምርመራ የጋዜጠናነት ስራ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ስራውን ሙያዊ ለማድረግ ከመርዳቱ ውጪ በኢትዮጵያ ሌብነት ብዙም ምርመራ እንደማያስፈልገው በርካቶች ይስማማሉ።

ቀናቸው ያለፉ ቁሶችን በርካሽ እየገዙ፣ ዳግም በማሸግና እሽግ ወረቀት በመቀየር ሃብት የሰበሰቡት እነማን እንደሆኑ፣ ማን ዕውቅና እንደሚሰጣቸው በተደጋጋሚ ተመልክቷል። ጥቆማ ተሰጥቷል። ዛሬ ሪል እስቴት ዙሪያ የተሳተፉ ማፍያዎች እንዴትና እንደምን ሃብታቸውን እንደሰበሰቡ አዲስ አበባ ያሉ ሚዲያዎች ያውቃሉ። ስጋቱ ሁሉም በሚባል ደረጃ ሚዲያዎቹ በሙስና በሚጠረጠሩት ድርጅቶች በማስታወቂያ ስም የሚቀለቡ መሆናቸው ነው።

አንድ ሚዲያ ላይ ይሰራ የነበረ የስራ ባልደረባችንን ጠይቀነው ” እገሌማ የገቢያችን ምንጭ ነው አትንኩት” እንባል ነበር። “ሲነኩም ማስታወቂያ እንደሚያቆሙ በግልጽ ይነግሩን ነበር” ሲኡል ትስስሩ የጠና መሆኑንን ይናገራል።

ከማስታወቂያ ባለፈ በሌብነት የተዘፈቁ ባለልጣናት ከሚመሩት ድርጅት ምርት ወይም አገልግሎት ወይም መሬት በመስጠት አፍ እንደሚያዘጉ ማስረጃና መረጃ ያላቸው አሉ። በዚህና መሰል ግንኙነቶች የባለስልታናትን ስም ማንሳት ከቶውንም እንደማይታሰብ በጓሮ ባለሙያዎቹ አለቆቻቸውን ሲያሙ መስማት የተለመደ ነው።

ከሁሉም በላይ ትልቁ ችግር አንዳንድ ሃብታም ተብዬዎች የሚዲያ ባለቤት መሆናቸውና ሌብነታቸውን በብሄር ሽፋን መስጠታቸው ነው። ስፖንሰር በሚያደርጉት ሚዲያና ራሳቸው እንዳቋቋሙት በሚታሙበት ሚዲያ ማስታወቂያ የሚያሰሩ፣ ድጋፍ የሚያሰባስቡና በዘራቸው የሚሰለፍላቸው ያሰባሰቡ መሆናቸው የሌብነት ዘመቻው ሌላ ፈተና ነው።


አዲስ አበባ ረክሳለች! – የሌቦች ውሎ

ግብረሰዶም የሚያስፋፉ በየሆቴሉ ድሆችን በማደን ማበላሸት ከጀመሩ ቆይተዋል። አሁን አሁን በየጎዳናው ታዳጊዎችን በማታለል ህሊና የሚያስት ኬሚካልና እጽ በመጠቀም ህሊናቸውንና አካላቸውን መስበር ተለምዷል። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው በዚህ የግብረሰዶም ወረራ ውስጥ ተጠቃሚ በመሆን ወንድሞቻቸውን የሚደልሉ መበራከታቸው ነው።

ህጻናትን ለወሲብ የሚያቀርቡ ነፍሰ በላዎች ኢኮኖሚያቸው አድጎ ባለ


የራሳቸው ወይም በተዘዋዋሪ የሚነዱት ሚዲያ ያላቸው በርካቶች ሲነኩ፣ የነካቸው ላይ ስም የማጥፋት ዘመቻ ያስከፍታሉ። ክብረ ነክ ስድብና ውርጅብኝ በማዝነብ ያሸማቅቃሉ። ቤተሰብና ዘር ማንዘር ስለማይቀራቸው አካሄዳቸው አስደንጋጭ ነው።

ለዚህም እንደምሳሌ የሚቀርቡት በግንባር ቀደም ተቅላይ ሚኒስትር አብይ ናቸው። አብይ ትህነግ ላይ ገመድ እያጠበቁ ሲሄዱ ተለይተው የሚዲያ ዘመቻ ተከፍቶባቸው እንደነበር፣ በመድር ላይ ያለውን ስድብ ቀን በቀን በመቀባበል ያወርዱባቸው እንደነበር በማስታወስ ሃሳባቸውን የሚሰጡ ” እገሌ የሚባል ባልስልታን ሊነሳ ነው፣. ሊታሰር ነው። እሱ ከተነካ ለሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጁ” የሚል የዘር ጥሪ ሲያስተላልፉ የነበሩ፣ በዚህም ሌባ ባለስልታንን ያዳኑ እንደነበሩ ይናገራሉ።

የዘር ፖለቲካ ያጨቀያት ኢትዮጵያ ሌብነትን ለመዋጋት የጀመረቸው ዘመቻ ከስልጣና በላይ ሰፊ የስነ ልቦናና የመንፈስ ዝግጅት እንደሚያስፈልገው የብዙዎች እምነት ነው። አብይ አህመድ ስለ ሌቦች ሲናገሩ ” የሚሰሩትን በማሸማቀቅ እንዳይሰሩና ለቀው እንዲሄዱ የማድረግ አቅም አላቸው” ሲሉ በገሃድ ሰሞኑንን መናገራቸው ይታወሳል።

በኢትዮጵያ እንደ አሸን የፈላው የዩቲዩብ ሚዲያ እንዲህ ያለውን የመንግስትን ጥሪ ወደሁዋላ ትቶ በንቶ ፈንቶ ጊዜውን የሚያጠፋው አንድም ከትቋቋመለት ዓላማ አንጻር ሲሆን፣ ሌላው ለላይክና ሰብስክራይብ ሲባል ቅራቅንቦ አሳብ ላይ ማተኮሩ እንደሆነ ስለሚዲያዎች ያጠኑ ተናግረዋል። መንግስት የሚደጉማቸውና በደህንነት ተቋሙ ስር ያሉት ሚዲያዎችም ቢሆን አቅም፣ ቁርጠኛነትና የጥራት ችግር ያለባቸው፣ ራሳቸውም ምርመራ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ሰፊ ምልክት አለ።

አንዳንድ የዩቲዩብ ሚዲያዎች ደግሞ ያለ በቂ መረጃና ማስረጃ የሌሎች ወገኖችን ሳያደምጡ ስም በማቆሸሽ መልኩ ተደጋጋሚና አሰልቺ ውንጀላዎችን ሲያሰሙና ሲያሳዩ ይታያል። የሚይዙት ጉዳይ ሃቅ ቢኖረውም በስሜት እንጂ በዕውቀት የተደገፈ ባለመሆኑ ግድፈት የበዛበት አጉል ጩኸት እንደሚሆን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

መንግስት ሌብነት ላይ ህግና ስርዓት ጥብቀህ ውቀጥ ባለበት ወቅት፣ መረጃ መስጠት ግድ በሆነበት አግባብ ሚዲያዎች ለድሃው ህዝብ ያላቸውን ወገናዊነት የሚያሳዩበት ትልቁና ውዱ ጊዜ በመሆኑ ከድብታቸው ሊነቁ ይገባል።

ከሁሉም በላይ ግን በፖለቲካ ልዩ ግብና ዓላም፣ በዘር ትብታብ፣ እንዲሁም በተመርማሪዎች በሚደገፉ ሚዲያዎችና የሚመረመሩትን ለመከላከል ታስበው የተቋቋሙ ሚዲያዎች፣ ከላይ በመግቢያው እንደተባለው ዓይነት ሚዲያዎች ይዞ ዘመቻው ከሚዲያ ተሳትፎ አንጻር ይሳካል? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ራሳቸው ሚዲያዎቹ ሙሉ በሙሉም ባይሆን ነጻ ናቸው? ብለው ለሚጠይቁ ምላሹ ምንድን ነው? እንዲህ ባሉት ጉዳዮችም ዙሪያ መስራት ግድ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ

Leave a Reply