በሽረ አዲስ ተስፋ፤ ሕዝብ በነጻነት ስለቀጣዩ ዕጣው አየመከረ ነው

እኚህ እናት ፊት የሚነበበው ተስፋ ብዙ ነገር ያሳያል። እኚህ እናት ጊንጭ ውስጥ ያለው ሊፈነዳ የደረሰ ፈገታ የማስመሰልና የካድሬ አይነት አይደለም። እኚህ እናት ከዚህ ተስፋቸው በሁዋላ ለጦርነት ምንም ዓይነት ቦታ እንደሌላቸው መረዳት ቀላል ነው። ይህን ዜና ያቀናበርው የመንግስት ሚዲያ ቢሆንም፣ ከሽሬና ከተለያዩ አካባቢዎች መከላከያ በገባባቸው ሁሉ ሕዝብ ተደራጅቷል። የሚነገረውና የሆነው የተለያየ ሆኖ አግኝቶታል። ቀሪው መቀለ ነው። ጥያቄው በስፋት ስላላ ጉዳይ ትህነግ የሚተላው የሰላም መንገድ እስከወዲያኛው እንደሚሸኘው ነው።

• የተሻለ የጸጥታ ሁኔታ ተፈጥሯል

• ሰበአዊ ድጋፍ ያለ ገደብ እየገባ ነው

• የተረጋጋ የግብይት ስርአት ተፈጥሯል

• መሰረተ ልማቶች ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል

በሽረ እንዳስላሰ ከተማ ከስምምነቱ ወዲህ የተሻለ የጸጥታ ሁኔታ መፈጠሩን፣ ሰበአዊ ድጋፍ ያለ ገደብ እየገባ መሆኑን፣ የተረጋጋ የግብይት ስርአት መፈጠሩንና መሰረተ ልማቶች ወደ አገልግሎት መመለሳቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።

የሽረ ከተማ ነዋሪ አቶ ገብረመድህን ገብረክርስቶስ በስፍራው ላሉት የኢፕድ ዘጋቢዎች እንደገለጹት፣ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ካሁን ቀደም በከተማዋ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ነበር። የፌዴራል መንግስት አካባቢውን ከተቆጣጠረና የሰላም ስምምነቱ ከተፈጸመ ወዲህ የጸጥታው ሁኔታ በተሻለ ሁኔታ ላይ በመሆኑ ህዝቡ የሰላም አየር እየተነፈሰ ነው።
አሁን ሰላምን በተግባር አይተናል ያሉት እቶ ገብረመድህን፣ የሰላም አየሩ ለመላው የትግራይ ህዝብ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተናግረዋል። የህዝቡ ፍላጐት ሰላሙ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ማስቻል እንደሆነም ጠቁመዋል።

አቶ ገብረመድህን እንደሚሉት፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ባንክ፣ ስልክ፣ ውሃ የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶች ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል። ህዝቡ ከፌዴራል መንግስት ጐን ቆሞ ሰላሙ ቀጣይ ስለሚሆንበት ሁኔታም በነጻነት እየመከረ ይገኛል።

ህዝቡ ይበጀኛል ብሎ የተቀበለውን ሰላም አንዳንዶች ለመቀልበስ ቢያስቡም፤ ሰላሙ እውን እንዲሆን የትግራይ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ እንደሆነ አቶ ገብረመድህን አረጋግጠዋል።

ወይዘሮ ግዴይ መዝገበ በበኩላቸው፣ ሰለሙ ከጨለማ ወደ ብርሀን አምጥቶናል። ለሁለት አመታት ዘልቆ የቆየው ግጭት በርዶ ሰላም በመምጣቱ ለትግራይ እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ብርሃንን የፈነጠቀ ነው ብለዋል።

See also  ጠ/ ሚ ዐቢይ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡት ቃለ መጠይቅ በጥሞና ወቅት እንዳይተላለፍ ሲል የመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን አሳሰበ

በአካባቢው የትራንስፖርት ሁኔታ ችግር እንዳለ በመግለጽ፣ መንግስት አግልግሎቱን የማስጀመር ስራን በትኩረት ሊያከናውን እንደሚገባም ወይዘሮ ግደይ አንስተዋል።

በግጭቱ ወቅት ህክምና ማግኘት አስቻጋሪ እንደነበር፣ የተርጋጋ የግብይት ስርአት ባለመኖሩ፣ ጤፍን ጨምሮ ለሎች ሸቀጣሸቀጦች በእጥፍ ሲሸጡ እንደነበርና ህዝቡ የፈለገውን ሸምቶ ለመብላት እንደሚቸገር ጠቅሰው፣ አጠቃላይ ሁኔታዎች ጨለማ እንደነበሩ ያስታውሳሉ። “አሁን ያለው ሁኔታ ብርሀን ነው” ሲሉ ነው የገለጹት።

የፌዴራል መንግስት ሽሬ ከገባ ጀምሮ የተሻለ የጸጥታ ሁኔታ መኖሩን የገለጹት ወይዘሮ ግደይ፤ ከዛ በፊት የተደራጁ ዘራፊዎች ህዝቡን ያስችግሩ እንደነበር ጠቅሰዋል። በአሁን ወቅት ምንም አስጊ ሁኔታ እንደሌለም ነው የተናገሩት።

በሽረ ከተማ የቀበሌ 03 ቡድን መሪ አቶ መርእድ አድማሱ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰላም ስምምነቱ የገባው ቃል አብዛኛው ተፈጻሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተለይ የሰብአዊ ድጋፍ ያለምንም ገደብ በከፍተኛ ቁጥር እየገባ እንዳለና የመጠን ጥያቄ ካልሆነ በቀር ለሁሉም ህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሰብአዊ እርዳታው በመግባቱ ህዝቡን ከረሃብ መታደግ ብቻ ሳይሆን ገበያውም ተረጋግቷል በማለት፣ ለአብነትም 100 ኪሎ ግራም ስንዴ ይሸጥ ከነበረበት ሰባት ሺህ ብር ወደ ሶስት ሺህ ብር ማውረድ እንደተቻለ ገልጸዋል። በተመሳሳይ 100ኪሎ ግራም ጤፍ ከ12ሺ ብር በላይ ይሸጥ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ በአምስት ሺህ ብር እየተሸጠ መሆኑንና የሰላም ስምምነቱ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ከማረጋጋት አኳያ ትልቅ ሚና እንደነበረው አንስተዋል።

ከሁለት አመታት በላይ የተዘጉ እንደ ቴሌ ያሉ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት ወደ ስራ ገብተው ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደቻሉም ተናግረዋል። የመንግስት ቁርጠኝነት ለህዝቡ የሰላም ምንጭ መሆኑን በመጥቀስ፣ ቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት ህዝቡ በመተባበርና በመደጋገፍ ስሜት ከመንግስት ጐን እንዲቆምም ጠይቀዋል።

በአዲሱ ገረመው (ሽረ እንዳስላሰ) ENA

Leave a Reply