የሽሬ አስማትነት፤የሽሬ ሽረት!!

ሽሬ አስማት ናት። ሽረትም ናት። ስንት ዓመት ወደሁዋላ? መቼ ነበር የማሽመድመድና የመሽመድመድ ታሪክ? አማቱ ያለው እዛ ላይ ነው። … “ጉድ ነው” አሉ ሰውየው! ባለህበት ለቆምክ ትናንትም ዘመን ነው። አዕምሮ ካልበረረ ችግር ነው። እንኳን የሽሬን አስማትነት ሚስትህን፣ ባልን እስከመርሳት ያደርሳል። ያበደው ወደሁዋላ ተወረወረ። የሽሬን አስማትነት ሲያሰላ፣ አስማቷ የገፈትረው ለገሰ አስፋው ፊቱ ላይ ተደነቀረበት። ቀበሌ 08፣ ከዮሃንስ ቤተክርስቲያን በታች “አበው” ግቢ፣ ጋቢ ለብሶ ዞሮበት ሲነከላወስ አጥር በሌለው ግቢ ውስጥ ሲያዝ አይቷል። ሽሬ በትህነግ እጅ እንድትወድቅ ሲደረግ ሻዕቢያ ተዋናይ ነበር። ታሪክ … ያብደው ንዴትም ሳቅም ቀላቀለበት። ታዲያ ዛሬ ላይ የሆነውን ስታስብ ሽሬ አስማት አትሆንብህም? ዘር ቀፍድዶህ ተዓምር ማየት ለተሳነህ …. ያበደው ዝምታን መረጠ። በሽሬ ግን “አለ ገና ..” የሚል ነጠላ ዜማ አለ።

አበሻ ሆናችሁ በነጮች በዓለ እዛው አበሺኛው ሰፈር ሆናችሁ ለምታሽቋልጡም፣ ይቅርታ አንድ ከትህነግ አድናቂ የተሰማ “ትንቢተ ዘገዳዳ” የተሰኘ ምኞት ላስቀድም። “አታምጣው ስል አምጥቶ ከመረው አለ … አሰልጣኝ …..

እንዲህ ይላል “ትግራይ ነጻ ከወጣች በሁዋላ የአፍሪካ ህብረት አባል አገር አትሆንም። የአውሮፓ ህብረት አባል በመሆን የደቡብ ቀይ ባህር የመጀመሪያዋ አገር ትሆናለች። ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራዊያንንም ያካትታል። እኛ ጸሃይ ያጠቆረን ነጭ ነን” ይህኔ ነው … አሉ ተሙኔ!! ” ግባ በለው …” ማለት…። የምኞት ሳተላይት ማምጠቅ … የሚገርመው እኮ ይህን አምኖ የሚቦርቀው እንጂ ላይሰፋ የሚቀደደው አይደለም። ላይክ ሼር …. “እኔ ነኝ …ያላችሁ እስኪ …” … “ሸማኔ ደወራ ሲሰለቸው ምን ይዘፍናል” ትላለች ቦሰና መስለ አድርጋ ” ይሄ ሌላ ያ ሌላ ” ብላ ትሸረድዳለች።

ያበደው ሰላምታውን ያቀርባል። እዛም እዚህም ላላችሁ መልካም ገና!! ቦሰና የዛሬ ሙዷ ሃይለኛ ነው። ከወገብ በታች አገለግሎት መስጠት አቁማ ዳግም “ዘግጁ” ስትሆን ጉዳዩ እስኪፈጸም ያገናትራታል። ብቸና ሄዳ የሰማቸው ታሪክ ታወሳት። “ብቸና የተፈጠረችው አንድ የበቁ ሼካ እንደ ምንጣፍ አጥጥፈው በትከሻቸው ይዘዋት መጡና አነጠፏት። ከዛ ብቸና ብቸናን ሆነች …”

በፖለቲካ ዓለም መዋሸት እውቂያ የተሰጠው ግልቢያ ነው። ወደ እኛ አገር ሲመጣ ግን “ዝም ብሎ መቀደድ ነው” ሞራል የሚባል ነገር የለም። በቃ ” ለደፈረ” መልካም የኑሮ አጋጣሚ ነው። እያሳረዱ ” ሂሳብ አወራዳለሁ እናንተ ሙቱ” የሚል “አማራጭ ነኝ” ባይ…. ሰምተናል። አይተናል። በጠጡን በየመድረኩ ሲረጭ የነበረ፣ መኩን ቀይሮ ፎቅ አለበት ስለኖረ ” ተንታኝ ነኝ” ብሎ ስንቱን ይነዳል? … ቦሰና እንዲህ አይነቶቹን ስታይ ” ውታፍ” ትላቸዋለች። ያብደው ደግሞ “የተወተፈላቸው” ይላና ያግለዋል።

ብሄር … ያበደው ይቅርታ ጠየቀ። ብሄር ላይ በተሰቀለ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋናይ መሆን “እንደ ተንታኙ ወዶ መደፈር ነው”፤ በያበደው በእብድ አረዳድ የብሄር ፖለቲካ ውስጥ መነከር የሚያቃጥል ቃሪያ ሰበር አድርጎ በራስ ፊንጢጣ ቀርቆ እየጮሁ መኖር ያህል ነው። ቦሰና ” የጭንቅላት እከክ” ትለዋለች። ደጎል ደግሞ ” ኮተታሞች” ይላቸዋል። አዎ ውሻ እናቱ ላይ ከመንጠልጠሉ ውጭ ኩሩ እንሳሳ ነው። እንደ ድመት አሳዳሪዎን፣ ወዳጁን፣ ቤተሰቡን አይበላም። አይክድም። ከሃጂዎች “ውሻ” ሲሉና ሲሳደቡ፣ ደጎል እግሩን አንስቶ ይሸናል። ምን ያድርግ!! የብሄር ልክፍት … ይቅር!!

See also  ያ - ሰፈር በሽሮ የሚፈተጉ በከሎች ? ዘይት ብርቅ ነው?

ወደ ሽሬ … ተመልከቱ። ደርግ ሽሬን በከርሳሞች ተከድቶ ሲያስረክብ በቀጣይ ያደረገው ነገር ቢኖር ሙሉ ትግራይን ለቆ መውጣት ነበር። የሚያውቁ እንደሚሉት “ሽሬ ተያዘ ነገር አበቃ ነው” የዛኔ የዛሬ ሶስት አስርት ዓመታት … ሽሬ ትህነግ እጅ ስትወድቅ መሃንዲሱ ሻዕቢያ ነበር። አዋላጁ ሻዕቢያ ነበር። አስኮማሪው ሻዕቢያ ነበር። አስፈጻሚዎቹ ደግሞ ከርሳሞች ነበሩ። እናም ሽሬ ገቢ ስትሆን ትህነግ አራት ኪሎ የመግባት ዕቅዱን ማስላት ጀመረ። ተሳካለት!! ሽሬ አሻረችው።

ዛሬ ምን ሆነ? ልክ ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ጥምር ጦር … በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት ” ጥምር ጦር ቢባል ያበደው ይወዳል” ሽሬን ሲይዝ የተሳትፎው መጠን ባይታወቅም ሻዕቢያ ነበር። ያበደው ዘለለ። ተቁነጠነጠ … “ልብ ያለህ አስተውል፤ ጆሮ ያለህ ስማ፤ አንጎል ያለህ አስላ፤ ሽሬ ስትያዝ ዓለም ጮኸ። የሚዲያ ማሽኖቹ “አለቀ፣ ነገር ተበላሽ፣ ድረሱ … ኡ ኡ ኡ ኡ …..” ሲሉ አስተጋቡ። ሽሬን ሲያስርክቡ ተሽመደመዱ። ሽሬ መተሬ ሆነችባቸው። መተሬ የተደበቀ የሚነቅል መድሃኒት። ቆርቾ!!

ሚስጢር አድሮ ይዘረዘራል። ፍንጭ ደግሞ ዛሬ ይሰጣል። ይቅርታ ያበደው እንደ ደብሪ ” ፍንጭጩን ይዘን” አላለም። ወደፊት ይከተባል። “ተራራውን ያንቀጠቀጠ” የተባለለት የትህነግ ዘፈን ምን በላው? በአንዴ እንዴት ተፍረከረከ? ያ ሁሉ ” ከአብይ ጋር በየትኛውም መድረክ መነጋገር….” ጸያፍ እንደሆነ ሲነግሩን የነበሩ ” ያላችሁትን በሙሉ፣ የምትፈልጉትን ሁሉ፣ በቃ ህገወጥ ነን …” ምናምን ማለት …. ሽሬ ላይ ማጂክ አለ። ሽሬ ላይ ደቀን ነበር፣ ሽሬ ላይ ደመቅን። የዛኔ ኢሳያስ ነበሩ። አሁንም አሉ… ፓለቲካ እንዲህ ነው። ሚስጥሩን በፍንጭ ልጀምር …ልመስጥር… ኢሳያስ ጥንቀቅ በሉ። ምትክዎትን አሳዩ … ያብደው በዚህ ጉዳይ አይቃዥም!! ፌልትስ ማን አሜሪካ ሄዶ ” ሰዎቹ አገራቸውን ይወዳሉ” ሲል ኢትዮጵያዊያንን በወያኔ ሂሳብ ማፍረስ እንደማይቻል ገሃድ ሲያደርጉ ነው ጨዋታውን ለመቀየር የታቀደው። እርስዎን መቀየር፣ ማስቀየር፣ ማስወገድ ወይም …..

ያብደው ተረጋጋ። ደሙን አበረደ። ሚስጥሩን አሰላው። መተረና ለዛሬ እንዲህ አለ። ” ጦርነቱ አላበቃም”!! አዎ ጦርነት ብዙ ፈርጅ አለው። ፈረንጅ ሲያጨበጭብ መጠንቀቅ ነው። ጦርነቱ አለማብቃቱን ለማረጋገጥ ይህን እንካችሁ።

ትህነግ “የሰላም ያላህ፣ ቅድሚያ ተኩስ ይቁም፣ ይብቃ…” ብሎ ሲለመን እምቢ ያለውን ያህል ሲወተውት፣ ሲያጓራ … ልብ በሉ በትህነግ የ”ድረሱልኝ” ጣር ውስጥ “የኤርትራ ጦር” የሚል ቀጭን ሳል ወይም ትክትክ አትጠፋም ነበር። ፕሪቶሪያ የሰላም አማራጭ ሲፈረም ያላነሳውን የኤርትራን ስም ” ተኩሱ ሲቆም” አነሳው። የአድሃኖም ልጅ ሳይቀሩ ” አጎቴ ተገደለ” አሉ። ወዳጆቻቸው ሚዲያዎችም ኤርትራን እየጠሩ ይጨፍሩ ገቡ። ኤርትራ ….. !!

See also  ምእራብ ሸዋ በቅሎ ወለደች

ነገሩ ወዲህ ነው። ጌታቸው ረዳ ” ፋሺስት” እያለ በየቀኑ ሲዘልፋቸው ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ” ለትህነግ ስትሉ ሻዕቢያን ውጉልን” አሉ። ይህ ግልጽ “እናባላችሁ” የሚል ዘመቻ ድንገት ሲያመልጥ ነው። ጌቾ ይህቺን ቢሞቱ አይደግሟትም። አንዴ አምልጧቸዋል። አዲስ አበባና ጌቾ … እንዴት ተነፋፍቀው ይሁን? ጌቾ ወመቴ ናቸው። አንቱ የሚባሉ ወመቴ፣ ማታ ማታ ባለቀለም … አሃሃሃ .. ወራጅ አለ!

ጦርነቱ ቆሟል የምትሉ ተሳስታችኋል። አሁን ጦርነቱ ሁለት ነው። አንደኛው አብይ አህመድንና ኢሳያስን ማጣላት። ኢትዮጵያንና ኤርትራን ማቃቃር። ተዋንያኖቹ አውሮፓ ህብረትና አሜሪካ ሲሆኑ ትህነግ ሽብልቅ ነው። ሌላው ጦርነት ደግሞ በሽሬ የተጀመረውን ጨዋታ አበርትቶ ትህነግን ፖለቲካዊ ሞት መግደል ነው። ወይም ፖለቲካዊ ሞት ማከናነብ። ይህ ደግሞ የሚሆነው በመንግስትና በገባቸው የትግራይ ተወላጆች በኩል ነው። የቱ ይቅደም? ያበደው ይጠይቃል። ጨዋታውን ሁለቱም ወገኖች ያውቁታል። ይህ ጨዋታ ላይደገም እንዲያበቃ ሩጫው ደርቷል።

ዝም ብሎ መነዳት ነውር ነው። አሁን ጥይት ቆመ እንጂ ሴራው እየተመረተ ነው። ሴራው በየቀኑ የሚረጨው ነው። ሴራው ማተራመስ ነው። እስካሁን ከተከፈላቸው በተጨማሪ አዳዲስ ክሊፖች መልካቸውን እየቀየሩ ይመጣሉ። እስከዛ ትህነግ አድብቶ ይጠግባል። አሜሪካ የነደፈችው ስትራቴጂ ይህ ነው። ትህነግ አድብቶ ወይም ” አሜባ” ሆኖ እንዲቆይ።

አሜባ የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር አንጀት ውስጥ ቤት ሰርቶ ይኖራል። ከሆድ ዕቃህ ወስዶ ያከማቸውን እየበላ ክፉ ቀን በራስህ አንጀት ውስጥ ተመሽጎ ያሳልፋል። ክፉ ቀኑ ሲያልፍ ቁርጠት ይለቅብሃል። የዛኔ ቦሰና እንደምታደርገው ፌጦ ድቆሳ … ነጭ ሽንኩርት ፍልቀቃ፣ ሚጥሚጣ ፣ መተሬ … ሽሬን ይዞ የትህነግን ቋንጃ የቆረጠው ሃይል አዲግራትን ሲጠጋ … በኤርትራ በኩል ገብቶ የበረሃውን መግቢአያና መሸሻ ላንቃ የሸፈንው ሃይል አንድ ላይ ሲናበቡ … አሜሪካ “በቃ ፈርሙ። አይሆንም” አለች። … “አድብቶ መነሳት” የሚባለው የነጮች ስልት ተዘጋጀ። አሁን ሩጫው አብይንና ኢሳያስን ማናከስ ነው። ይህ እንዲሆን የምትለፋ ሁሉ አስብ!! አስሉ። አማራና አፋር ክልል የሆነውን ገምግሙ። ኢሳያስ እስካሉ ትህነግ አይቀናውም። ትህነግ አድብቶ እንዲነሳ ኢትዮጵያና አስመራ መቧቀስ አለባቸው። ኤርትራ እያሉ እንዲያለቅሱ የተመደቡ የዚህ የድብታ ፖለቲካ ቅጥረኞች ናቸው። ያበደው “ዋ” ያላል።

ያብደው ከፋው። ትህነግ በዚህ ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ ጠላት የሆነው ለምንድን ነው? ኢትዮጵያ ፣ ልጆቿ፣ ምድሯ፣ … ምን በድለውት ይሆን? እድሜ ልኩን የሚያሴርባት፣ ሲፈልግ እንደ ክርታስ እንዲበጣጥሳት አድርጎ የሰፋት ምን አግድላበት ይሆን፣ በጋራስ ምን በድለነው ይሆን? ትህነግ … ያበደው አዘነ። እንደ ሌላ ጊዜው ምራቁ ግን አፉን አልሞላውም። አልተፋም። ውስጡ ተስበረ። ወዳጆቹን፣ ባልደረቦቹን፣ ጓደኞቹን አሰባቸው … “አይቼሽ ነው ባይኔ ወይስ በቴሌቪዥን …” ድንገት አፉን ሞላው …

See also  [የሽግግር መንግስት] ሊቋቋም ነው !!

ድንገት “ዘራፍ” ብሎ ተነሳ። ቁልቁል ቸርችልን እየወረደ የሰማዕታት ሃውልት ጋር ደረሰ። ጥቁር አንበሳ!! አረፍ አለና የካራማራውን ድል … ሞቀው። “የምን መሰበር” ሲል ተስፈነጠረ። ወደ ቀድሞ መከላከያ ቢሮ አመራ። ምርጥ ጀነራሎች ባንዲራ ለብሰው ያለፉበት … “ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስን ጠይቁ” ብሎ አለፈው። “ያ – አዘጥዛጭ ስንት ተወትፎለት ይሆን የዳዊት ሻንቅላ የሆነው” ስትል ቦሰና …. ባቻ እዛ ውስጥ አሜሪካ ነበረች። የሾመችብንም እሷ ናት … አሁንም “አድፍጦ መቀመጥ” የሚለውን “የድንገት አጥፍተሕ አጥፋ” ሰልታኞች ላለማሰማራቷ ማስተማመኛ የለም። …. ባቻ ሴራ የምትሸርበው እሷ ናት። አሜሪካ!! ያበደው በጀግኖቹ ኮራ። “አሻግረህ በለው..” ታወሰው። ካልሆነ አይቀርም። በሴራ አንሞትም… ከገባችሁ ጨዋታው ይህ ነው!! ሻእቢያ ትናትም ዛሬም አለ። ዛሬ ወዳጅ ነው። ለዚያውም የክፉ ቀን። ያበደው …. ተሽኮረመመ!! አምላኩን አመሰገነ። ” አንለያይም” ዘፈነ!!

ዛሬ ቦሰና ዳግም አገልግሎት የምትጀምርበት ቀን ነው። ትግራይ ስታበራ እሷ አጥፍታ ነበር። ያበደው ሳቀ። ድንገት ሞቀው። ቦሰና “አከሲ …” እያለች ከናጠችው ከራርሟል። ገንፎ ይጠብቀዋል። ገንፎ ምልክት ነው። የመውረጃ ሳይሆን የመውጫ። ቤት ያልችሁ ግቡ። እንደ ቦሰና የሰው ማኛ ያላችሁ ተከየፉ። ቦሰና ጭድ ናት። …. ተጋግለናል። ተሳፍተናል። “አከሲ…” ሳይጀመር ተሸበለልኩ። ሰላም፣ ሻሎም ….. ሽሬ መስበሪያና መሰበሪያ!! አማት!!

  • የበርሊን ማራቶን ባለማዕረግ ትግስት እነ ዱቤ ጂሎ ቢሳተፉ ታዝረከርካቸው ነበር
    በማራቶን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሻል እጅግ የሚደነቅና ያልተለመደ ነው። ባለሙያዎቹ ወይም አሰልጣኞቹ የሮጠችበትን ፍጥነት በሰዓትና ርቀት ከፋፍለው ቢያቀርቡት ምን አልባትም ወንዶችን የሚገዳደር ፍጥነት ተጠቅማ ሮጣለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቴክኒክ ዳይሬክተርና የአትሌቶች ኮሚሽን ሰብሳቢ የነበሩት የዛሬው የተከበሩ ዱቤ ጅሎ አይነቱን ሯጮችን አዝረክርኮ ማሸነፍ የሚያስችላትን ሃይል አሳይታለች። የበርሊና ባለ ማዕረግ ትዕግስት!! ተግስት … Read moreContinue Reading
  • ህዩዋ..ህዩዋ
    ህዩዋ..ህዩዋ ህንግጫ-የኮንታ_ብሔር_ዘመን_መለወጫ!! የኮንታ ብሔር በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለየ መልኩ የሚገለጽባቸው በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ታሪካዊ እና ባሕላዊ ቅርሶች ባለቤት ነው። ብሔሩ ካሉት በርካታ የማይዳሰሱ ሀብቶች መካከል አንዱ የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል-ህንግጫ አንዱ ነው፡፡ ህንግጫ በብሄሩ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የብሔሩ ማንነት … Read moreContinue Reading
  • ዝንጀሮዎች ለኒው ደልሂ የቡድን 20 ጉባዔ ስጋት ሆነዋል
    የህንድ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ከ10 ቀናት በኋላ የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባን ለማስተናገድ ጉባዔው በዝንጀሮዎች እንዳይረበሽ እየተዘጋጀች ነው። ከተማዋ እንግዶቿን ለመቀበል እያደረገችው ባለው ሽር ጉድ ውስጥ ለአንድ ጉዳይ የተለየ ትኩረት ሰጥታለች፤ ዝንጀሮዎችን ከመሰብሰቢያ አዳራሽ የማራቅ ዘመቻ። በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች አስፈሪ የዝንጀሮ ምስሎች እና ቅርጾችን እያስቀመጠች ሲሆን፥ የእንስሳት ድምጽን የሚያስመስሉ … Read moreContinue Reading

Leave a Reply