እንደፈረንጅ የግሪጎርያኑን የቀን መቁጠሪያ የሚጠቀሙት የኤርትራ ፕሬዚዳንት በዚሁ “በነጮች አዲስ ዓመት” ተብሎ በሚጠራው ቀን ስም ” [ትህነግ] ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” አይነት ንግግር አሰምተዋል። ስጋት እንደሌለ ማስታወቃቸው እንደሆነ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ጥምር ጦር ሽሬን መቆጣጠሩን ተከትሎ ትህነግ የወሰደውና እንዲወስድ የተመከረው ምክር ከደርግ ጋር እንደሚመሳሰል ተጠቆመ።
“ቢሆንም ቅሉ፣ የሁን እንጂ” በሚሉ መገጣጠሚያዎች አጅቦ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ “ትንኮሳንና ጸብ አጫሪዎችን” ሲሉ በደፈናው አስታውቀው ሰራዊታቸው እንዳስተነፈሰ መናገራቸውን ቀድሞ የዘገበው ቢቢሲ ነው።
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግን) በስም መጥራት ያልፈጉት ኢሳያስ ፀብ ጫሪና ተንኳሽ ሃይል መሆኑን ጠቅሰው አሁን ግን ነገሮች መቀየራቸውን አመልክተዋል። ጦራቸውን አመስግነው ” አኩሪ ተግባር ፈጽሟል አስታግሶታል” ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ
“በሕዝቡ የሚሞቅ እቅፍ ውስጥ ያለው የኤርትራ መከላከያ ኃይል ወረራ ለመፈጸም ይፍጨረጨር የነበረን ኃይል በፀረ-ማጥቃት አስታግሷል። በዚህም ኩራቴ ገደብ የለሽ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጦራቸውን አሞግሰዋል። የት የት ግንባር ድል እንደፈጸመ ግን አላብራሩም። ቢቢሲም አልገለጸም።
በተጠናቀቀው የነጮቹ ዓመት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ያሉ ኤርትራውያን “ንቁ ሆነው በጽኑ አቋም የሚያኮራ ትግል አድርገዋል” በሚል ለሁሉም ምስጋና ያሉት ኢሳያስ “ወረራ ለመፈጸም ሲፍጨረጨር” የነበረው ሃይል አደብ እንዲገዛ መደረጉን ገልጸዋል። ስም ባይጠሩም ትህነግን ለማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። እሳቸው ግን በስም መጥቀስ እንኳን ያልፈለጉበት ምክንያት አልተብራራም።
አቶ ጌታቸው ረዳ ባህር ዳር አየር ማረፊያ ላይ ሮኬት መወንጨፉን፣ ወደ ኤርትራምና ጎንደርም በተመሳሳይ መከናወኑን ሲናገሩ ሃይላቸው ጥቃቱን እንደሚቀጥል፣ የፊደራል መንግስት የጦር አውሮፕላኖች እንደሚመቱና የሮኬት ጥቃቱ እንደሚቀጥል አስታውቀው ነበር። ኤርትራም ይህን ተከትሎ “ትህነግ የደህንነቴ ስጋት ነው” በማለት በስም ባልተተቀሱ ቦታዎች ሃይሏን አሰማርታ ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ሰራዊቱም በንብረት ማውደምና በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሲከሰስ ነበር።
በአሜሪካና መዕራባዊያን ጫና የምትደቆሰው ኤርትራ በሚቀጥለው ዓመትም ተመሳሳይ ጫና ሊደርስባት እንደሚችል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አመልክተዋል። እነዚሁ ሃይላት በተደጋጋሚ ማዕቀብና ተቃውሞ በማሰማት ኤርትራን ሲኮንኑ ነበር። አሁን ላይ የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ መውጣቱ በውጭ ሚዲያዎች በይፋ እየተነገረም ቢሆን እነዚሁ አገራት ጫናቸውን እንደቀተሉ ነው።
- እጅግ ግዙፍ የበረዶ ግግር ተገምሶ ስፍራውን በመልቀቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አስግቷልየለንደንን መጠነ-ሥፋት ከ2 እጥፍ በላይ የሚሆን የዓለማችን ትልቁ የበረዶ ግግር ተገምሶ እየሄደ ነው ተባለ፡፡ የበረዶ ግግሩ በፈረንጆቹ 1986 ላይ ከአንታርክቲክ ባሕር ዳርቻ ተቆርሶ በዌድል ባሕር አካባቢ የቆየ ሲሆን፥ ከመጠኑ ግዝፈት አንጻርም ‘የበረዶ ደሴት’ የሚል ስያሜን ይዞ በአካባቢው ከ30 አመታት በላይ ቆይታ አድርጓል። የበረዶ ግግሩ ‘የለንደን’ መጠነ ሥፋት ከሁለት እጥፍ በላይ … Read moreContinue Reading
- በጎብኝዎች የተወደዱ ምርጥ ሀገራትየተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ አንዱ የቱሪዝም መረጃዎችን ይፋ ማድረግ ነው፡፡ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ላይ ወቅታዊ ትንታኔዎችን ይሰጣል፡፡ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም የቱሪስት ፍሰት መረጃን ያወጣል፡፡ ተቋሙ በያዝነው የፈረንጆች 2023፤ ከጥር እስከ ሐምሌ ያለውን የሀገራትን የቱሪዝም ፍሰት እ.ኤ.አ.ከ 2019 ጋር በማነጻጸር ይፋ አድርጓል፡፡ ቀዳሚዎቹ ሀገራት … Read moreContinue Reading
- የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጂቢ ኒውስ በተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ በጋዜጠኛነት ተቀጠሩጆንሰን በቴሌቪዥን ጣቢያው የፕሮግራም አቅራቢ፣ አዘጋጅና ተንታኝ ይሆናሉ። በቀጣይ ዓመት የአሜሪካና የዩኬ ምርጫ በመዘገብ “ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ” ተብሏል። “የእንግሊዝን ኃይል የሚያሳይ መሰናዶ” ያቀርባሉም ብሏል ጂኒ ኒውስ። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዩች ምልከታቸውን ለማጋራት ቃል ገብተዋል። በዴይሊ ሜይል ላይም አምደኛ የሆኑት ቦሪስ ጆንሰን ሥራቸውን በአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ። ቦሪስ ጆንሰን በኤክስ ገጻቸው ላይ … Read moreContinue Reading